Get Mystery Box with random crypto!

ያቺን አንዲት ፍሬ የት እንደዘራህ ረስተህ ሊሆን ይችላል፡፡ ግና ከቀናት ቆይታ በኋላ ዝናብ ያበቅላ | ABX

ያቺን አንዲት ፍሬ የት እንደዘራህ ረስተህ ሊሆን ይችላል፡፡ ግና ከቀናት ቆይታ በኋላ ዝናብ ያበቅላትና ቦታዉን  ይጠቁምሃል፡፡ ሁሌም በየትኛዉም ሁኔታና አካባቢ ላይ፤ እንዲሁም ለማንኛዉም ሰው መልካምን መዝራት ቢቆይም ፍሬ አለው፡፡ ስለሆነም ሰዎች “መልካሙ” ብለው እስኪያውቁህ ድረስ በመልካምነትና መልካምን በመዝራት ታወቅ፡፡
ግዴለህም ሳታመነታ ቦታ ሳትመርጥ ዝራ፡፡ መልካምነት የትም ብትዘራው ይበቅላል፡፡ ያ ዘር መቼ እና የት ፍሬ አፍርቶ እንደሚጠብቅህ አታውቅምና፡፡ የተቸገሩትን መርዳት፣ ለተጨነቁት መፍትሄ ብትጠቁም ምንዳዉን በዚሁ ምድር ላይ ታያለህ፤ አሊያም ወደፊት ቀድሞህ በአኺራህ የሚጠብቅህ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡

ወዳጆቼ የምድር ላይ ዕድሜያችን ከምናስበው በላይ አጭር ናት፡፡ ከቶ የአንድንም ሰው ደስታ አትስረቁ፤ የአንድንም ሰው ተስፋ አትንጠቁ፡፡


http://t.me/MuhammedSeidABX