Get Mystery Box with random crypto!

ABX

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX A
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedseidabx
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.70K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 05:52:38 ጌታዬ ሆይ

ወደ መልካም ምራን፣
መልካምን አናግረን፣
መልካም አሰማን፣
መልካም አሠራን፣
ከመልካሞች አውለን፣
ከመልካሞች አድርገን፣

ሰባሐል ኸይር

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.4K views02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:27:23 ከእዝነቱ የተነሳ ስህተት የሆነዉን መስመር በመረጥክ ጊዜ ሁሉ ጣልቃ እየገባ ያሰናክልሃል።

አሁንም እዝነትህን የኔ ጌታ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.6K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:00:18 አውቃለሁ ያ ረብ...
መታዘዜ ምንም አይጠቅምህም፣
ባንተ ማመፄም ቅንጣት አይጎዳህም።

ግና ጌታዬ ሆይ!
አንተን መታዘዝን ወፍቀኝ።
ባንተ ከማመፅ ጠብቀኝ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.1K viewsedited  17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 12:11:48 ሰው ሁለት ጽዋ ታቅፎ ይኖራል፤ ባንዱ የመረረ ጭላጭ፡ በሌላው ጥዑም አርኪ ፈሳሽ
በየትኛው ጊዜ፤ በየቱ ፈረቃ፤ ከምኑ ዋንጫ ውሰጥ እንደሚጎነጭ፤ ሲዋትት፤ ሲረበሽ
ይነጉዳል፤ ይፈሳል፤ ቀን ውሎ፤ ቀን ሲመሽ፤
ሆኖም፤
ላታህዘን ነውና የጀሊሉ አማን(ና)
ኮሶ ስትጠጣ፤ አምርረህ፤ ተክዘህ፤ አትርሳ፤ ሌላውን
ከሃላሉ ወይን ከሆነልህ፤ ፍርቃው፤ ፈንድቀህ ያለልክ፤ አትጣ መላውን!
ይልቅ፤
በተራ ነውና፤ የዱኒያ፤ ፍጥራዋ
ሳትባክን፤በርትተህ፤ ትጋ ለኋላዋ!

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.0K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:41:15 አል-ከሪሙ
አላህ (ሱ.ወ) ከውሃና ከአፈር በመፍጠር እኛን የሰው ልጆችን ክብር ሰጥቶናል፡፡ ውሃና አፈር በፍጥረተ-ዓለሙ ውስጥ የሚገኙ እጅግ ንፁህ የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡ ይህም ፅዱና ንፁህ ፍጡር መሆናችንን ያመለክታል፡፡ ስለሆነም በሀጢአትና በመናፍቅነት ራሳችንን አንነጅስ፣ ራሳችንን አናዋርድ፡፡ እኛ የጠራን ፍጡር ነን፡፡ የቁርአን እናት ፈቲሓ እንደሆነችው ሁሉ እኛም የፍጥረተ-ዓለሙ ቁንጮ ነን፡፡ ….
እኛ በምድር ላይ የአላህ ምትኮች ነንና ከርካሽ ነገሮችና ከርካሽ ስሜቶች ከፍ ማለት ይኖርብናል፡፡ ያከበረንን አላህ ማክበር ይኖርብናል፡፡ ራሳችንን የማክበር ሰሜት ውስጣችንን የፈጠረውን አምላክ ልናከብር ይገባል፡፡
በስህተት ላይ በምንወድቅበት ጊዜ ራሳችንን እንንቃለን፡፡ ትላልቅ ወንጀሎች ትላልቅ የተባሉበት ምክንያት እነርሱ እኛን በማዋረዱ ረገድ ትልቅ ስለሆኑ ነው ይባላል፡፡
እኛ የቸሩ፣ የተከበረው ጌታ ባሮች ነንና ራሳችንን አናዋርድ፡፡ በሀጢአት፣ በንፍቅና በውሸት ራሳችንን አናዋርድ፡፡ አንድም ሰው ሀጢኣታችንን ባያውቅ እንኳ ራሳችን በራሳችን ላይ የምንመሰክረው ይብቃ፡፡ ራሳችን ራሳችንን የምንታዘበው ይብቃን፡፡ በሌሎች እይታ ውስጥ ገብተን ከመዋረድ እንጠንቀቅ፡፡ ሁሌ እየተሸማቀቁ ከመኖርና መጠቋቆሚያ ከመሆን እንራቅ፡፡ ሰላም አይኖረንምና፡፡ ኃጢኣተኛ እንደሌባ ነው፤ጩኸት ሁሉ ወደርሱ ይመስለዋል፡፡

"ቢስሚከ ነሕያ" ከተሠኘው መጽሐፍ የተወሰደ
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል፡፡

ዶ/ር ዐምር ኻሊድ እንዳዘጋጀው
ሙሐመድ ሰዒድ ABX እንደተረጎመው


https://t.me/NejashiPP
1.9K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:02:43 መጀመሪያ አካባቢ እንደ ቆንጆ መድኃኒት ተጠቀሙብን። ጊዜው ሲገፋና አማራጭ ሲያገኙ እክስፓይርድ ሆነዋል ብለው ጣሉን።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.9K views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:00:05 ረሱላችን (ሰ.ዐ.ወ.) ከዕለት ጉርስ የሚተርፍ ነገር ካላቸው እቤታቸው አያሳድሩም ነበር፡፡ አውጥተው ይሠጣሉ፤ ወስደው ይመፀውታሉ፣ ለችግረኞች ያከፋፍላሉ፡፡
.
የሚነገርም ሆነ የሚፖሰት መልካም ነገር ካጋጠማችሁ፣ ካያችሁ፣ ከሠማችሁ … እቤታችሁ አታስቀምጡ፡፡ በእጃችሁ አታቆዩ፡፡ ጊዜው ጥሩ ቃላትን የተራብንበት ነው፡፡ ርሃብ አጎሳቁሎናልና አሁንም አሁንም ሣትሠለቹ አጉርሱን፡፡ ጠምቶናልና ቀዝቃዛ ውሃ ሁኑን። ሰው በእንጀራ ብቻ ነው የሚኖረው ያላችሁ ማነው??

ሰው ሆኖ ዱንያ ያላቆሰለችው ማን አለ? በመልካም ንግግር የሰውን ህመም ዳብሱ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.1K views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 06:42:53 ዝምብለህ መልካም ዝራ ይበቅላል። የዘራህበት ቦታ ቢጠፋህ እንኳ አንድ ቀን ፍሬው ከፍ ብሎ እዚህ እኮ ነው የዘራኸኝ ይልሃል። ስለሆነም ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ለፍጡራን ሁሉ መልካምን ዝራ። ዉጤቱን አየህ አላየህ፣ ተጠቀምክ አልተጠቀምክ ዝራ። የት፣ መቼ እና እንዴት እንደማታገኘው ባታውቅም ዝራ።
መልካም ነገር መብቀሉም ለሌሎች መትረፉም አይቀርም። ዛሬ በዱንያ ይሁን ነገ በአኺራ ምርጥ ዉጤቱን ታገኛለህ። ሰዉን ለማስደስት ኑር ትደስታለህ። ስጥም ታገኛለህ። የማንንም ደስታ አትስረቅ፣ የማንንም ቀልብ አትስበር። ዕድሜያችን አጭር ነው ወዳጆቼ። መልካም አሻራ ግን ቀሪ ነው።

ሰባሐል ኸይር!

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.3K views03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 17:46:45 አንዲት በዐይኗ የማታይ ድመት ወደ ቤትህ የተጠጋች እንደሆነ እሷን መቀለብ ግዴታ አለብህ ይላሉ አንዳንድ የሙስሊም ሊቃውንት ።

ኢስላም ለማንኛዉም ነፍስ ላለው ፍጡር ሁሉ እዘኑ ብሏል።

https://t.me/NejashiPP
2.0K views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 17:46:02 ከቻልክ
መልካም ነገር ሁሉ የሚገባበት በር ሁን፣
ካልሆነ ብርሃን የሚገባበት መስኮት ሁን፣
ካልቻልክ የደከማቸው የሚደገፉበት ግድግዳ ሁን።

የአላህ እዝነትና ሰላም መልካም ነገርን ሁሉ ባስተማሩን ነቢይ ላይ ይስፈን።

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.0K viewsedited  14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ