Get Mystery Box with random crypto!

ABX

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX A
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedseidabx
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.70K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 65

2021-01-26 07:03:02 የዒልም ዘካው ዒልምን ማስተላለፍ ነው፡፡ ያወቁትን ነገር ለሌሎች ማካፈል ግድ ነው፡፡ ዉድ ወዳጆቼ … በዚህ ገጽ የቀሰማችሁት አዲስ ዕውቀትና መረጃ ሊኖር ይችላል ፡፡ ስለሆነም ከቀሰሙትና ከተዋወሱት ዕውቀት ዘካ ማውጣት ግዴታ ነው፡፡
ኢብኑ ሐባን አል-ቡስቲ ከዕውቀት አንፃር ስለሚጠበቀው ግዴታ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ

‹አንድ ሰው የተወሰነ ዕውቀት ከተሠጠው ለማስተላለፉ ሊሰስት አይገባም፡፡ የመጀመሪያው የዒልም በረከት ማስተላለፍ ነው፡፡ መሬት ሥር የሚገኝ ዉሃ ካልፈለቀ፣ ምድር ዉስጥ የተቀበረ ወርቅ ካልወጣ፣ ጥልቅ ባህር ዉስጥ ያለ ዕንቁ ወጥቶ ጥቅም ካልዋለ እንደማይጠቅም ሁሉ እንዲሁም አንድ ዕውቀት ያለውና ዕወቀትን የሚሰስት ሰው ካላስተላለፈው በስተቀር ፈፅሞ ሊጠቀም አይችልም፡፡›

ሰባሐል ኸይር

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.4K views04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-25 15:19:29 በየቀኑ ባጠፋም ተስፋ ቆርጬ ከመንገድህ ከምርቅ እየወደቅኩም እየተነሳሁም ብሆን መንገድ ዉስጥ ብቆይ ይሻለኛል ።
ያ ረብ ...

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.5K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-24 09:39:01

1.7K views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-23 09:56:34 ማስታወሻ
ስለ ጥሪ
***
ማነው በቀደምለታ አንድ ወዳጃችን በሆነ ጉዳይ ጥሪ ነበረው፡፡ ከታዋቂዎችና ሀብታም ሰዎች በዛ ያሉትን፤ ከመካከለኞቹና ከድሆቹ ደግሞ በቁጥር አነስ ያሉትን ጠራ፡፡ ጥሪው ላይ በብዛት የተገኙት ግን የኋለኞቹ ነበሩ፡፡ የፊተኞቹ ግን ትሁት ከሆኑት አንድ ሁለቱ በስተቀር ሁሉም ሊያስብል በሚችል መልኩ ቀሩ፡፡

ደዕዋዎች፣ ሰርጎች፣ ለቅሶዎች … መለኪያቸዉና ደረጃቸው የታዋቂ ሰዎች መገኘት ሆኗል፡፡
አንዳንዴ ጥሪያችን ላይ ምን ዓይነት ከባባድ ሰዎች እንደተገኙ ለማሳየት ብለን ብቻ ድሆችን አልፈን ሀብታሞችን እንጋብዛለን፡፡ እነርሱም አይገኙልንም እኛም ብዙ ጊዜ አይሳካልንም፡፡ ድግሦች የፉክክር መድረክ ከሆኑ ቆዩ፡፡

የምግብ ድግስ ጥሪ ላይ ጉዳዩ በአብዛኛው የሚመለከተው ድሃዉን ነው፡፡ በፍትህ ዓለም ለሌለው ይሠጣል እንጂ ላለው አይጨመርለትም፡፡ ድሃ ተትቶ ሀብታም የሚጠራበት ሰርግ ምን ይከፋ! ይላሉ ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ.፡፡

ከሁሉ በፊት በጥሪህ ላይ ንያህን አሳምር፤ ሰዉን ሳይሆን የአላህን ዉዴታ የምታገኝበትን መንገድ ፈልግ፤ አላህ ከወደደህ ሰው ይወድሃል፡፡ ታይታንና ዝናን እርሳ፡፡ ምንም ድሃ ቢሆኑም የጠዋት ጓደኞችህን አትርሳ፡፡ ጥሪህን ከጎረቤትና ከዘመድ ጀምር፡፡ የዑለሞችን፣ የሽማግሌዎችንና የቅን ሰዎችን ዱዓ ፈልግ፡፡ ድሆችን ብትጠራ በልተው ይደሠታሉ፤ ዑለሞችን ብታጋብዝ ከጌታህ እዝነትንና በረከትን ይለምኑልሃል፡፡

አንተ ደግሞ ወዳጄ ሆይ! ከጥሪ በመቅረት “እኔ በቀላሉ የምገኝ ሰው አይደለሁም፣ ስታንዳርዴ ከፍ ያለ ነው” የሚል ስሜት ያለው መልዕክት ለሌሎች አታስተላልፍ፤ በማሕበራዊው ሕይወት ዉስጥ ባለመሳተፍ ዋጋህንና ደረጃህን አትቆልል፤ እየተመቸህም ኦ እሱ ቢዚ ነው አይገኝም አይመቸዉም አታስብል፡፡

ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ.) የዓለማችን ታላቁ ሰው ከመሆናቸው ጋር ብዙ ወዳጆቻቸው ተራ ሰዎች ነበሩ፡፡ ለሰዎች ጥሪም ከባድ ቦታ ይሠጡ ነበር፡፡ የድሃዉንም የሀብታሙንም፣ የባሪያዉንም የሠራተኛዉንም ጥሪ ተቀብለው ይገኙ ነበር፡፡ “በወንድም ጥሪ ላይ መገኘት ወንድምህ ባንተ ላይ ካለው መብት አንዱ ነው” ብለዋልም እርሣቸው፡፡

በርሣቸው ላይ የአላህ እዝነትና ሰላም ይስፈን፡፡


http://t.me/MuhammedSeidABX
2.0K viewsedited  06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-23 06:29:35 አላህ ሆይ
* ከትንሹ ሞት በኋላ ሕይወት ስለሠጠኸን እናመሰግንሃለን፡፡
* ተጨማሪ ወዳንተ የመመለስ ዕድል ስለሠጠኸን እናመሰግንሃለን፡፡
* ኖረን ኖረን መሞታችን አይቀርም፤ መመለሻችንም ወዳንተው ነው፡፡

አምላኬ ሆይ!
* ካንተ ተነጥለው የሚኖሩት ኑሮ የሰቀቀን መሆኑን አውቃለሁ፡፡
* ሁሌም በሀሳብም ሆነ በተግባር ካንተ ጋር ከተሳሰሩት አድርገኝ፡፡
* አንተን ማውሳትን ሱሴ አድርግልንሷኝ፣
* ሥምህ ከምላሴ ፣ ልቅናህ ከልቦናዬ አይነጠል፡፡
* ዘወትር እንመሰግንህ ዘንድ አንቃኝ፣

ጌታዬ ሆይ
* ከሚዘናጉት፣ ከሚጃጃሉትና ጊዜያቸዉን በከንቱ ከሚያጠፉት አታድርገን፡፡
* ኸይርህን አትንፈገኝ፣ ሲትርህን አታንሳብኝ፣ ካነሳኸኝ በኋላ አትጣለኝ።
* ያ ረብ ካንተ ዉጭ የሌላ ባርያ አታድርገኝ ፡፡


ወዳጆቼ! የጠዋት ዱዓ ጉልበት አለዉና ወደ አምላካችሁ ተንፍሱ፡፡ የጠዋት አዝካሮችን በማድረግም ቀናችሁን አስዉቡ፡፡

ሰባሐል ኸይር


 http://t.me/MuhammedSeidABX
4.0K views03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-21 06:23:00 እባክዎ ወዳጆች የ ዩቱዩብ ቻናሉን ለሌሎች ያካፍሉ ያስተዋውቁ።
ሰብስክራይብ ያድርጉ
1.8K views03:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-21 06:21:32

1.8K views03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-21 06:16:28 ሰዎች እንደ መጽሐፍ ናቸው -

* አንዳንዶቹ ግልጽ ናቸው፤ ምንም የሚደብቁት ነገር የላቸዉም፤ ርዕሳቸዉን በማየት ዉስጣቸዉን ታያለህ፡፡

* አንዳንዶች ደግሞ ሽፋናቸው ሳቢ ነው፤ ግና ዉስጣቸው ቁምነገር የሌለው ይሆናል፡፡

* አንዳንዶች ደብዛዛና ቀዝቃዛ ናቸው፤ ስትቀርባቸው ፍካታቸው ይገለጣል፣ መዓዛቸው ያዉዳል፡፡

* ሌሎች ደግሞ ቀላል ናቸው፤ በአንድ ጊዜ ንባብ ትወዳቸዋለህ፣ ትቀርባቸዋለህ፡፡

* አንዳንዶች ደግሞ ከባድ ናቸው፤ ሞክረህ ሞክረህ ትተዋቸዋለህ፡፡

* አንዳንዶች ደግሞ አይገቡህም፤ እስክትረዳቸው ድረስ ደጋግመህ ማንበብ ይኖርብሃል፡፡

አንብቡ! ማንበብ መልካም ነው፡፡

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.6K viewsedited  03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ