Get Mystery Box with random crypto!

የዒልም ዘካው ዒልምን ማስተላለፍ ነው፡፡ ያወቁትን ነገር ለሌሎች ማካፈል ግድ ነው፡፡ ዉድ ወዳጆቼ | ABX

የዒልም ዘካው ዒልምን ማስተላለፍ ነው፡፡ ያወቁትን ነገር ለሌሎች ማካፈል ግድ ነው፡፡ ዉድ ወዳጆቼ … በዚህ ገጽ የቀሰማችሁት አዲስ ዕውቀትና መረጃ ሊኖር ይችላል ፡፡ ስለሆነም ከቀሰሙትና ከተዋወሱት ዕውቀት ዘካ ማውጣት ግዴታ ነው፡፡
ኢብኑ ሐባን አል-ቡስቲ ከዕውቀት አንፃር ስለሚጠበቀው ግዴታ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ

‹አንድ ሰው የተወሰነ ዕውቀት ከተሠጠው ለማስተላለፉ ሊሰስት አይገባም፡፡ የመጀመሪያው የዒልም በረከት ማስተላለፍ ነው፡፡ መሬት ሥር የሚገኝ ዉሃ ካልፈለቀ፣ ምድር ዉስጥ የተቀበረ ወርቅ ካልወጣ፣ ጥልቅ ባህር ዉስጥ ያለ ዕንቁ ወጥቶ ጥቅም ካልዋለ እንደማይጠቅም ሁሉ እንዲሁም አንድ ዕውቀት ያለውና ዕወቀትን የሚሰስት ሰው ካላስተላለፈው በስተቀር ፈፅሞ ሊጠቀም አይችልም፡፡›

ሰባሐል ኸይር

http://t.me/MuhammedSeidABX