Get Mystery Box with random crypto!

አል-ሓሪሥ አል-ሙሓሲቢ እንዲህ ይላል - ‹ ከአላህ ዘንድ በርሱ ላይ የተወረደውን ነገር የማያውቅ | ABX

አል-ሓሪሥ አል-ሙሓሲቢ እንዲህ ይላል -
‹ ከአላህ ዘንድ በርሱ ላይ የተወረደውን ነገር የማያውቅ ሰው፤ ከርሱ ዘንድም ወደ አላህ ሊሄድ የሚችልን ነገር የማያውቅ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ›

አዎን ... በየቀኑ ጠዋትና ማታ ወዳንተ የሚወርዱትን የአላህ (ሱ.ወ.) ፀጋዎች፣ በይፋም ሆነ በስውር ወዳንተ የሚንቧቡትን ችሮታዎች የማታውቅ ከሆነ ይህ የሚያሳየው የቀልብህ እይታ የተጋረደ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም በመጋረዱ የተነሳ መጥፎን ነገር ከጥሩ ለይቶ ሊያውቅ አይችልም፡፡ ወደ ጀነት የሚያቃርበውንና  ለእሣት የሚዳርገውን ነገር አይለይም፡፡
ከዕውርነት ሁሉ ክፉው የልብ ዕውርነት ነው፡፡ ቀልብ የታወረ እንደሆነ በየጊዜው ወደ ጌታው የሚወጣውን ሥራውን መለየት ይሳነዋል፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡
ይህ መጽሐፍ አንዳንድ ከኛ የተጋረዱና የተደበቁ የአላህ ችሮታዎችን ይገልፅልናል፣ ከፍቶ ያሳየናል፡፡ በዚሁ መነሻነትም ያስተዋልናቸውን ፀጋዎች እናጣጥማለን፡፡ የደረስንባቸውን ችሮታዎች እናመሰግናለን፡፡ ቀልባችንም አላህ ላደረገልህ በጎ ነገር ጥሩ ምላሽ ይኖረዋል፡፡ የአላህን በጎነትም በበጎ ይመልሳል፡፡ እሱ የመረጠለትንም ነገር ከሌላው ነገር ሁሉ ያስበልጣል፡፡

ምንጭ ፦ የሁለት ዓለም ጀነት
ኻሊድ አቡ ሻዲ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ


https://t.me/NejashiPP