Get Mystery Box with random crypto!

ABX

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX A
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedseidabx
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.70K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 61

2021-03-01 17:54:32 ከኛ የሚፈለገው
******,

ከኛ የሚፈለገው የቀልባችን መሰበር እንጂ የሰዉነት መሰበር አይደለም፤ የልብ ማጎንበስ እንጂ የአካል ማጎንበስ አይደለም፣ የነፍስ መታዘዝ እንጂ የጡንቻ መታዘዝ አይደለም፣ የዉስጥ መተናነስ እንጂ የገላ ማስመሰል አይደለም፡፡ 

አላህ (ሱ.ወ.) ቀልባቸዉን ለርሱ ብለው ከሰበሩ ሰዎች ጋር ነው፡፡ በትዕቢትና ጉራ አትለምኑት፡፡ በመመፃደቅና ፉከራ አትጠይቁት፣ በታይታና ጥብረራ አታምልኩት፡፡

ሲደክማችሁ፣ ሲያማችሁ፣ ግራ ሲገባችሁ … ወደማንም ዘንድ ከመሄዳችሁ በፊት ወደሱ ሂዱ፡፡ ለአንድም ሰው ችግራችሁን ከመንገራችሁ በፊት ለሱ ንገሩ፡፡ ለማንም በሽታችሁን ከመግለጣችሁ በፊት እሱ ዘንድ ታከሙ፡፡ ችክ ብላችሁ ለምኑት፤ ከልብ ሆናችሁ ጠይቁት፡፡ ድህነታችሁን፣ ፈላጊነታችሁን፣ አቅመቢስነታችሁን በራሣችሁ ላይ መስክሩ፡፡

እንዲህ እንዲህ በደልከኝ፣ ጣልከኝ ብላችሁ መክሰሱን ተዉና ቀርባችሁ አዋዩት፡፡ ይኸው ሁሉን ትቼ አንተ ጋ መጣሁ በሉት፡፡ እሱን ዉደዱ፣ ለሱ ዉረዱ፣ ለሱ ተዋረዱ፡፡

ደካሞች ናቸዉና ወደ ሰዎች የሚያደርሰዉን በር ሁሉ ዝጉ፣ ወደሱ የሚያስገባዉን በሰፊው ክፈቱ፣ ሳታፍሩና ሳትፈሩ ወደርሱ ግቡ፣ ይኸው ወንጀሌ፣ ይኸው እንከኔ፣ ይኸው ዉርደቴ፣ ይኸው ክፋቴ፣ ይኸው ጥፋቴ በሉት፡፡

አላህ ዘንድ ተናዞ መውጣት ከሁሉ በሽታ መዳን ነው፡፡
አላህ ይጠብቃችሁ ወዳጆቼ!  

ጠቃሚ መስላ ከታየቻችሁ ይህችን ምክር አካፍሉ። ከሚደርሰኝ ምንዳም አንድም ሳይጎድል ተካፈሉ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.8K views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-01 06:27:11 ምርጥ ጓደኞቼ የምላቸው ሱብሒ ላይ የማገኛቸው ናቸው።
ሰባሐል ኸይር ወሰዓዳ


ይህችን ዚክር ሦስት ጊዜ አብረን እንበል ....
ረዲቱ ቢልላሂ ረብበን፣ ወቢል ኢስላሚ ዲነን፣ ወቢሙሐመዲን ነቢየን።

ለትርጉሟ ወደ ኤፍ ቢ ገጼ ጎራ ይበሉ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.5K views03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 17:19:37 የምሥራች!!
መጽሐፍ ማንበብ ፈልገው የመግዢያው ቦታ ርቆታልን? እንግዲያውስ ነጃሺ ማተሚያ ቤት መጽሐፍትን ባሉበት ቦታ ማድረስ መጀመሩን በደስታ ያበስራል፡፡ ስማርት ስልክዎን አውጥትተው ነጃሺ ቡክስቶር የሚለውን አፕልኬሽን ከዚህ ሊንክ https://bit.ly/3r4948i ያውርዱ፡፡ በአማርኛ ፣ በኦሮምኛ፣ በዐረብኛና በሌሎችም የአገራችን ቋንቋዎች ከተጻፉ የተለያዩ መጽሐፍት ይምረጡ፡፡ የሚፈልጉትን ያህል መጽሐፍ ከመረጡ በኋላ የዘንቢሉን ምልክት ይጫኑ፡፡ በፌስ ቡክና ጉግል አካውንት ወይም የስልክ ቁጥርዎን በማስገባት ይመዝገቡና አድራሻዎትን ይሙሉ፡፡ በአማራጭነት ከቀረቡ ባንኮች የሚመቾትን ይምረጡና በሞባይል ባንኪንግ ወይም በአካል ሂደው ብሩን ገቢ በማድረግ ያስገቡበትን ስሊፕ አፕሊኬሽኑ ላይ ሲጭኑ ወይም በ 0945858585 ላይ በቴሌግራም ሲልኩ ትዕዛዝዎ በተሳካ ሁኔታ ይጠናቀቃል ፡፡ አዲስ አበባ ከሆኑ ዕቃውን ሲረከቡ ክፍያ መፈጸም ይችላሉ፡፡
የማድረሻ ዋጋ፡- አዲስ አበባ፡- 50 ብር ብቻ
ሌሎች ከተሞች፡- አፑ ላይ በተቀመጠው የፖስታ ቤት ተመን መሰረት (የፖስታ ሳጥን ቁጥር አያስፈልጎትም)
አፑን ከታች ከተቀመጠው ሊንክ አሁኑኑ ያውርዱና ኑሮዎን ያዘምኑ!
https://bit.ly/3r4948i
ነጃሺ የእውቀት ማዕድ!!
1.6K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 16:07:51

1.4K views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 15:22:36 ሁሌም ጥሩ ማሰብ
**
አላህ (ሱ.ወ.) ሁሌም ስለሱ መልካም ነገር እንድናስብ ይፈልጋል። ‹ተፋኡል› ወይም ‹ሑስነ ዞን› ልንለው እንችላለን።
እይታን ማደፍረስ፣ መጥፎ ማሰብና ማሟረት ነገሮችን ያወሳስባል። ኸይር የለዉም ወዳጄ፡፡
እኛ ሙስሊሞች በአላህ ጉዳይ ላይ የጠራ አቋም ነው ያለን፤ ብዥታ የለብንም። ሁሌም ከፈጠረን ጌታ መልካምን ነገር እንጠብቃለን።
አላህ መልካም ነው። መልካም ነገር ሁሉ ከሱ ነው። መልካም ነገሮችን እንጂ ከሱ አንጠብቅም፣ አንመኝምም። ከጠበቁት ቦታ የሚታጣው ሰው ነው፡፡ “ጠብቁኝ” ብሎ የማይቀረው አላህ ብቻ ነው፡፡ ለዘመናት በዚህ መልኩ ኖሬያለሁ፡፡ ብዙ ነገርም አተረፍኩ። አሁንም በእጄ ካለው ነገር ይልቅ እርሱ ዘንድ ባለው ነገር እተማመናለሁ፡፡

ሕይወታችን ካሰብነው ሐዲድ እየሳተ ያለ ቢመስለንም፤ ነገሮች ወደ አሉታዊነት አዘንብለው ቢታዩንም ሁሌም መልካም ነገርን እናስባለን፤ በጎ በጎውን አሻግረን እናያለን።
ኢንሻአላህ ሁኔታዎች ይለወጣሉ፤ ነገሮች ሳይታሰብ ይቀየራሉ። ከኛ የሚጠበቀው መሮጥ ነው፤ ማርሽ ቀያሪውና ትንፋሽ ጨማሪው አላህ ነው፡፡

ዙርያህ በመከራ ቢከበብም፣ ተጨባጭህ በእሾህ ቢታጠርም፣ መንገድህ የጨለመ ቢመስልም ... ጥሩ ነገርን አስብ። መልካም ነገርን እንጂ ወደ ህሊናህ አታምጣ።

አንዳንዴ ጥሩ ማሰብ ብቻውን ነገሮችን ጥሩ ያደርጋቸዋል። ጥሩም ማሰብ ነፃ ያወጣናል። መልካም ተስፋ እናድርግ። የተስፋን ገመድ ባትደርስበትም ተንጠልጠልበት።

መልካም እያሰቡ መሞት ይሻላል። መልካም ማሰብ፣ ነገሮች ጥሩ ይሆናሉ .. ብሎ ተስፋ ማድረግ ጤናን ይጠብቃል፣ በሕይወት ለመኖር ያግዛል። ወደፊት ለመወርወርና ጠንካራ ሆኖ ለመኖርም ነዳጅ ይሆናል።

እኛ ጋ አሁን ሰዓቱ የዙሁር ነው።
ይህን መጽሐፍ እንድታነቡ ምክሬ ነው።
ባረከላሁ ፊኩም

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.4K views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 12:24:02 የምሥራች!!
መጽሐፍ ማንበብ ፈልገው የመግዢያው ቦታ ርቆታልን? እንግዲያውስ ነጃሺ ማተሚያ ቤት መጽሐፍትን ባሉበት ቦታ ማድረስ መጀመሩን በደስታ ያበስራል፡፡ ስማርት ስልክዎን አውጥትተው ነጃሺ ቡክስቶር የሚለውን አፕልኬሽን ከዚህ ሊንክ https://bit.ly/3r4948i ያውርዱ፡፡ በአማርኛ ፣ በኦሮምኛ፣ በዐረብኛና በሌሎችም የአገራችን ቋንቋዎች ከተጻፉ የተለያዩ መጽሐፍት ይምረጡ፡፡ የሚፈልጉትን ያህል መጽሐፍ ከመረጡ በኋላ የዘንቢሉን ምልክት ይጫኑ፡፡ በፌስ ቡክና ጉግል አካውንት ወይም የስልክ ቁጥርዎን በማስገባት ይመዝገቡና አድራሻዎትን ይሙሉ፡፡ በአማራጭነት ከቀረቡ ባንኮች የሚመቾትን ይምረጡና በሞባይል ባንኪንግ ወይም በአካል ሂደው ብሩን ገቢ በማድረግ ያስገቡበትን ስሊፕ አፕሊኬሽኑ ላይ ሲጭኑ ወይም በ 0945858585 ላይ በቴሌግራም ሲልኩ ትዕዛዝዎ በተሳካ ሁኔታ ይጠናቀቃል ፡፡ አዲስ አበባ ከሆኑ ዕቃውን ሲረከቡ ክፍያ መፈጸም ይችላሉ፡፡
የማድረሻ ዋጋ፡- አዲስ አበባ፡- 50 ብር ብቻ
ሌሎች ከተሞች፡- አፑ ላይ በተቀመጠው የፖስታ ቤት ተመን መሰረት (የፖስታ ሳጥን ቁጥር አያስፈልጎትም)
አፑን ከታች ከተቀመጠው ሊንክ አሁኑኑ ያውርዱና ኑሮዎን ያዘምኑ!
https://bit.ly/3r4948i
ነጃሺ የእውቀት ማዕድ!!
1.3K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 08:15:31 ዱዓቸው
ምንጭ ፡ 500 የነቢዩ ባህርያት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ትርጉም በሙሐመድ ሰዒድ

1.በለሊት የመጨረሻዎቹ ሰዓታት ላይ አማኞች በዱዓእ እንዲበረቱ ያዙ ነበር፡፡
2. ከያንዳንዱ ሶላት በኋላ ዱዓእ እንዲያደርጉም ያበረታቱ ነበር፡፡
3. ምእመናን በሱጁዳቸው ውስጥ በዱዓእ እንዲበራቱ ይጠቁሙ ነበር፡፡
4. እጃቸውን ከፍ አድርገውና ተናንሰው አላህን ይለምናሉ፡፡
5. አንድን ሰው ያስታወሱ እንደሆነ ዱዓእ ያደርጉለታል፡፡
6. አጠቃላይ /ጃሚዕ/ የሆኑ ዱዓኦችን ይጠቀሙ ነበር፡፡
7. ዱዓ ሲያደርጉ ሶስት ሶስት ጊዜ ዱዓእ ያደርጋሉ፡፡
8.ሶስት ሶስት ጊዜ ከአላህ (ሱ.ወ.) ምህረትን ይለምናሉ /ኢስቲግፋር ያደርጋሉ/፡፡
9. በራስ ላይ፣ በልጆች ላይ፣ በአገልጋዮች ላይና በሀብት ንብረት ላይ በመቅሰፍትና በእርግማን ዱዓእ እንዳይደረግ ይከለክሉ ነበር፡፡
10. ሲነጋ አላህን በማውሳት ቀናቸውን ይጀምራሉ፤ ሲመሽም ዱዓእ ያደርጋሉ፡፡
11. ከቤት ሲወጡ ‹ቢስሚላህ ተወከልቱ ዐለላህ ወላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላሂ› ይላሉ፡፡
12. ዝናብ ባዩ ጊዜ ‹አላሁምመ ሰዪበን ናፊዐን ..› በማለት ይደጋግማሉ፡፡
13. የመብረቅ ድምጽ የሰሙ እንደሆን ‹አልላሁምመ ላ ተቅቱልና ቢገዶቢከ› ይሉ ነበር፡፡
14. የምግብ ማዕድ ሲነሳ ‹አልሐምዱ ሊላሂ-ልለዚ አጥዐመና ወሰቃና ወአዋና ወጀዐለና ሙስሊሚን› ይላሉ፡፡
15. ንፋስ በነፈሰ ጊዜ ከያዘችው መልካም ነገር ይለምናሉ፡፡ በውስጧ ካለ መጥፎ ነገርም በአላህ ይጠበቃሉ፡፡
16. በአንድ ነገር ላይ መወሰን የከበዳቸው እንደሆን ‹አላህ ሆይ ምረጥልኝ፡፡›ይላሉ፡፡
17. ከድካም፣ ከስንፍና፣ ከፍርሃት፣ ከመጃጃት፣ ከስስት፣ ከመቃብር ቅጣት አላህ እንዲጠብቃቸው ለምነዋል፡፡
18. አላህን ከማይፈራ ቀልብ፣ ተሰሚነት ከሌለው ዱዓእ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ከማይጠቅም ዕውቀትም በአላህ ተጠብቀዋል፡፡
19. አላህ (ሱ.ወ.) የለገሳቸውን ፀጋ እንዳይወስድባቸው፣ ጤናቸውን እንዳያቃውስባቸው፣ ደንገተኛ ቁጣ እንዳያወርድባቸው ጠብቀኝ ብለዋል፡፡
20. ከድህነት፣ ከውርደት፣ ከክህደት፣ ሰውን ከመበደልና በሰዎችም ከመበደል አላህ እንዲጠብቃቸው ለምነዋል፡፡
21. በዚህች ዓለምም ሆነ በመጨረሻው ዓለም አላህ መልካምን ነገር እንዲሰጣቸው ይለምኑ ነበር፡፡

https://t.me/NejashiPP
1.4K views05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-25 16:19:32 የኢስቲኻራ ሶላት

*,,,,,,****,,

1- የኢስቲኻራ ሶላት ምንድነው ?
በሁለት ነገሮች መካከል መወሰን ሲቸግረንና አጣብቂኝ ዉስጥ ስንገባ በዚህ ጉዳይ ላይ የተሻለዉን እንዲመርጥልን አላህን ለመጠየቅ የምንሰግደው ሶላት ነው።

2- የኢስቲኻራ ሶላት ስንት ረከዓ ነው ሚሰገደው?
ሁለት ረከዓ ነው።

3- የኢስቲኻራ ዱዓ ሶላት ዉስጥ ነው ሚደረገው?
አይደለም ሁለቱ ረከዓ ከተሰገደ በኋላ ነው።

4- ኢስቲኻራን ከአንድ ጊዜ በላይ መስገድ ይቻላል?
አዎ ኢስቲኻራን ደጋግሞ መስገድ ይቻላል።

5- ከሶላቱ በኋላ ልናየው የሚገባ ህልም አለ?
ለኢስቲኻራ ዱዓ የሚወርድልን ወሕይም ሆነ ህልም የለም።

6- ልንመርጠው ስለሚገባ ነገር ለማወቅ ምን ምልክት አለ?
መወሰን ስላለብን ጉዳይ ምልክት ሊኖርም ላይኖርም፣ ዝንባሌ ሊከሰትም ላይከሰትም፣ ነገሩ ሊገሩ ላይገራም ይችላል። ግና የገራልንና ያዘነበልንበት፣ የተነሳሳንለት ነገር ካለ እሱን መምረጥና በዚያ ላይ አላህ ኸይር ያደርገው ዘንድ መልካም ነው።

7- የኢስቲኻራ ሶላትን ምን ምን ጉዳዩችን ለመወሰን ልንሰግድ እንችላለን ?

አምልኳዊ ሳይሆን ዱንያዊ ጉዳዮችን ነው። ለምሳሌ ቤት፣ መኪናና የመሣሠሉትን ስንገዛ፣ ለጋብቻ ተጣማሪን ስንመርጥ ...

8- ኢስቲኻራ ሰግደው ከወሰኑ በኋላ ምን ሥርዓት ያስፈልጋል ?
በዉሳኔ አለመፀፀት፣ ባልሠራሁ ባላደረግኩ ብሎ አለመቆጨት የሆነዉን ሁሉ መውደድ ያስፈልጋል ።
የኢስቲኻራ ሶላት አንድ የአላህ ባርያ በሱ ላይ እውነተኛ መመካትን የምታሳይ ነው። ሙእሚን በዉሳኔዎቹ ዉስጥ አላህን ያስገባል፣ መልካሙን እንዲመርጥለትም ይማፀነዋል። አላህም መልካሙን ይመርጥለታል።


https://t.me/NejashiPP
1.7K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 20:02:49

486 views17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 10:39:22 እንደው ዝምብሎ ይገርመኛል
***
ዘመኑ ወደኋላ ላይመለስ በሚመስል ሁኔታ መልኩን ለዉጧል፡፡ ፍሬዉን እየተወ ለገለባው ዋጋ እየሠጠ በመጓዝ ላይ ያለ ይመስላል፡፡
ወጣቱን መምከር ከብዷል፡፡ ታናሽ ታላቁ መደማመጥ ጠፍቷል፡፡ መቅደም ያለበት ያለመቅደሙ ያሳስባል፡፡

ከዑለሞች በላይ ኡስታዞች ሲከበሩ፣  ከቃሪኦች በላይ ሙንሺዶች ሲደነቁ፣ ከቁምነገረኞች በላይ ቀልደኞች ሲወደሱ፣ ከቁርኣን ሐዲሥ በላይ ልቦለዶች ሲሞገሱ፣ ከዳዒዎች በላይ ዘፋኞች ሲወደዱ፣ ከወላጆች በላይ ጓደኞች ሲደመጡ፣ ከሙሓዶራዎች በላይ ፊልሞች ሲመረጡ፣ ከእውነተኛ ወሬዎች በላይ ሹክሹክታዎች ቦታ ሲያገኙ፣  … እንደው ዝም ብሎ ይገርመኛል፡፡

ነገሮች ወደኋላ ላይመለሱ በዚህ መልኩ ይቀጥላሉ ብዬ አሰብኩ፡፡ አላህ ወደፊት ዕድሜ ከሠጠን እኛም የኛ ባልሆነ ዘመን የምንኖርበት ጊዜ ቅርብ ነው ማለት ነው፡፡ ከአሁኑ “አይ ባባ ምን ነካህ! በቃ አረጀህ … እያሉ ለጆቼ ስስቁብኝ እየታየኝ ብቻዬን እስቃለሁ - እኔ፡፡
ህእ
ሰባሐል ኸይር! ወዳጆቼ፡፡


 http://t.me/MuhammedSeidABX

ጉዳያችሁ ሁሉ ይፈፀም ዘንድ በነብያችሁ ላይ ሶለዋት አዉርዱ።
 
1.2K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ