Get Mystery Box with random crypto!

እንደው ዝምብሎ ይገርመኛል *** ዘመኑ ወደኋላ ላይመለስ በሚመስል ሁኔታ መልኩን ለዉጧል፡፡ ፍሬዉን | ABX

እንደው ዝምብሎ ይገርመኛል
***
ዘመኑ ወደኋላ ላይመለስ በሚመስል ሁኔታ መልኩን ለዉጧል፡፡ ፍሬዉን እየተወ ለገለባው ዋጋ እየሠጠ በመጓዝ ላይ ያለ ይመስላል፡፡
ወጣቱን መምከር ከብዷል፡፡ ታናሽ ታላቁ መደማመጥ ጠፍቷል፡፡ መቅደም ያለበት ያለመቅደሙ ያሳስባል፡፡

ከዑለሞች በላይ ኡስታዞች ሲከበሩ፣  ከቃሪኦች በላይ ሙንሺዶች ሲደነቁ፣ ከቁምነገረኞች በላይ ቀልደኞች ሲወደሱ፣ ከቁርኣን ሐዲሥ በላይ ልቦለዶች ሲሞገሱ፣ ከዳዒዎች በላይ ዘፋኞች ሲወደዱ፣ ከወላጆች በላይ ጓደኞች ሲደመጡ፣ ከሙሓዶራዎች በላይ ፊልሞች ሲመረጡ፣ ከእውነተኛ ወሬዎች በላይ ሹክሹክታዎች ቦታ ሲያገኙ፣  … እንደው ዝም ብሎ ይገርመኛል፡፡

ነገሮች ወደኋላ ላይመለሱ በዚህ መልኩ ይቀጥላሉ ብዬ አሰብኩ፡፡ አላህ ወደፊት ዕድሜ ከሠጠን እኛም የኛ ባልሆነ ዘመን የምንኖርበት ጊዜ ቅርብ ነው ማለት ነው፡፡ ከአሁኑ “አይ ባባ ምን ነካህ! በቃ አረጀህ … እያሉ ለጆቼ ስስቁብኝ እየታየኝ ብቻዬን እስቃለሁ - እኔ፡፡
ህእ
ሰባሐል ኸይር! ወዳጆቼ፡፡


 http://t.me/MuhammedSeidABX

ጉዳያችሁ ሁሉ ይፈፀም ዘንድ በነብያችሁ ላይ ሶለዋት አዉርዱ።