Get Mystery Box with random crypto!

አላህ ሆይ * ከትንሹ ሞት በኋላ ሕይወት ስለሠጠኸን እናመሰግንሃለን፡፡ * ተጨማሪ ወዳንተ የመመ | ABX

አላህ ሆይ
* ከትንሹ ሞት በኋላ ሕይወት ስለሠጠኸን እናመሰግንሃለን፡፡
* ተጨማሪ ወዳንተ የመመለስ ዕድል ስለሠጠኸን እናመሰግንሃለን፡፡
* ኖረን ኖረን መሞታችን አይቀርም፤ መመለሻችንም ወዳንተው ነው፡፡

አምላኬ ሆይ!
* ካንተ ተነጥለው የሚኖሩት ኑሮ የሰቀቀን መሆኑን አውቃለሁ፡፡
* ሁሌም በሀሳብም ሆነ በተግባር ካንተ ጋር ከተሳሰሩት አድርገኝ፡፡
* አንተን ማውሳትን ሱሴ አድርግልንሷኝ፣
* ሥምህ ከምላሴ ፣ ልቅናህ ከልቦናዬ አይነጠል፡፡
* ዘወትር እንመሰግንህ ዘንድ አንቃኝ፣

ጌታዬ ሆይ
* ከሚዘናጉት፣ ከሚጃጃሉትና ጊዜያቸዉን በከንቱ ከሚያጠፉት አታድርገን፡፡
* ኸይርህን አትንፈገኝ፣ ሲትርህን አታንሳብኝ፣ ካነሳኸኝ በኋላ አትጣለኝ።
* ያ ረብ ካንተ ዉጭ የሌላ ባርያ አታድርገኝ ፡፡


ወዳጆቼ! የጠዋት ዱዓ ጉልበት አለዉና ወደ አምላካችሁ ተንፍሱ፡፡ የጠዋት አዝካሮችን በማድረግም ቀናችሁን አስዉቡ፡፡

ሰባሐል ኸይር


 http://t.me/MuhammedSeidABX