Get Mystery Box with random crypto!

ከሐሰን አል-በስሪ ንግግሮች (ረሒመሁላህ/አላህ ይዘንለት 1- አማኝ አውቆ አያጠፋም፡፡ ሌሎች ያጠ | ABX

ከሐሰን አል-በስሪ ንግግሮች (ረሒመሁላህ/አላህ ይዘንለት

1- አማኝ አውቆ አያጠፋም፡፡ ሌሎች ያጠፉበት እንደሆነም ታጋሽ ነው፡፡ አይበድልም፤ የበደሉት እንደሆነም ይቅር ባይ ነው፡፡ አይሰስትም ከስስታሞች አንፃርም ታጋሽ ነው፡፡

2- አንዳንድ ሰዎች አንድም መልካም ነገር ሳይኖራቸው ይህችን ዓለም እስኪለቁ ድረስ አጓጉል ምኞት አዘናጋቸው፡፡ ‹ጀነት እንገባለን በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ አለን፡፡› ይላሉ። ውሸታቸውን ነው በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ቢኖራቸው ኖሮ ሥራቸውን ባሳመሩ ነበር፡፡›

3- አማኝ ዘወትር ራሱን የሚወቅስ ሆኖ እንጂ አታገኘውም፡፡ በንግግሬ በርግጥ ምን አስቤበት ነው? በመመገቤና በመጠጣቴስ ምን ፈልጌበት ነው? ይላል፡፡ ደካማ ሰው ግን ነፍሱ አይወቅሳትም፣ አይቆጣጠራትም፣ አይመረምራትም፡፡ ዝም ብሎ ይኖራል፡፡

4 - አንድ የአላህ ባሪያ የምትመክረው ነፍስ እስካለው ድረስ መልካም ሁኔታ ላይ ነው፡፡ ያኔ ሀሳቡ ሁሉ ስለራሱና ስለ ፍፃሜው አብዝቶ መጨነቅ ይሆናል፡፡

5- ለዚህ ዓይነቱ /ለሞት ቀኑ/ ለሠራ ሰው አላህ ይዘንለት፡፡ እናንተ ዛሬ ላይ  የመቃብር ሰዎች የሆኑ ወንድሞቻችሁ የማይችሉትን ነገር ትችላላችሁ፡፡ ጤናና ትርፍ ጊዜያችሁን የድንጋጤና የምርመራ ቀን ከመምጣቱ በፊት ተጠቀሙበት፡፡

6- የዱንያ ቀን አንዱም አይመጣም እንዲህ ያለ ቢሆን እንጂ፡- ሰዎች ሆይ! እኔ አዲስ ቀን ነኝ፡፡ እኔ በኔ ውስጥ በሚሰራብኝ ነገር መስካሪ ነኝ፡፡ ፀሐይ የጠለቀች እንደሆነ እስከ እለተ ትንሳኤ ድረስ ወደናንተ የማልመለስ ነኝ፡፡

ምንጭ - ምርጥ አባባሎች
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር

https://t.me/NejashiPP