Get Mystery Box with random crypto!

ABX

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX A
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedseidabx
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.70K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-02-02 17:04:46 የጤናማ ቀልብ ምልክት
*** **

ቀልብ ጤንነት ምልቶች መካከል ሰውዬው አንድ ዊርዱ ወይም ከአምልኮ ተግባሩ ባመለጠው ጊዜ፣ ከዚያ አንድ ጥንቁቅ ሰው ገንዘቡ ባመለጠው ጥሩ ባመለጠው ጊዜ ከሚሰማው ሕመም የበለጠ ሕመም እርሱን በዚህ የተነሳ ማግኘቱ ነው፡፡ ልክ የተራበ ሰው ለምግብና ለውሃ እንደሚናፍቀው ሁሉ እርሱም ለአላህ ኺድሚያ ይናፍቃል፡፡ የሕያ ኢብን ሙዓዝ እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹እርሱ ያ አላህን በማገልገል የሚደሰት ሰው፣ ሁሉም ነገሮች እርሱን በማገልገል ይደሰታሉ፡፡ እርሱ ያ ዓይኑ በአላህ ላይ የረጋ ሰው፣ የያንዳንዱ ነገር ዓይኖች ወደርሱ በመመልከት ይረጋሉ፡፡››
የጤናም ቀልብ ባለቤትን የሚያሳስበው ነገር አንድ ብቻ ነው፣ ያም የአላህ ጉዳይ ነው፤ ማለትም ሁሌም በአላህ አምልኮና መታዘዝ ላይ መገኘት፡፡
ሌላው ባለቤቱ ከሰዎች መካከል ከዚያ ለገንዘቡ በብርቱ ንፉግ ከሆነው ሰው በላይ ጊዜው በከንቱ እንዳይባክንበት ሲበዛ ንፉግ መሆኑ ነው፡፡
ወደሶላቱ በሚገባበት ጊዜ የዱንያ ጭንቀቱና ሐሳቡ ሁሉ ይወገዳል። በርሷም ውስጥ ዕረፍትና እርካታን ያገኛል፡፡ ሶላት ለርሱ የዓይን ማረፊያው እና የቀልቡ ደስታ ናት፡፡
ጌታውን ከማውሳት አይቋረጥም ፡፡ እርሱን ከማገልገል ፈጽሞ አይደክምም፡፡ ከርሱ ውጭ ማንንም አይወዳጅም።
ሌላው ባለቤቱ ከሥራው በላይ ስለሥራው ትክክለኛነት ያለው ትኩረት የበለጠ ትልቅ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ በዚያ ውስጥ በኢኽላስ ላይ፣ ምክርን በመለገስ ላይ፣ መልዕክተኛውን በመከተል ላይ፣ በመልካምነት ላይ ጠንቃቃ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህም ጋር በዚያ ውስጥ ያለውን የአላህን ፀጋና የአላህን ሐቅ በመወጣቱ ረገድ ደግሞ ያለበትን ጉድለት በራሱ ላይ ይመሰክራል፡፡
 

ነፍስን ማጥራት
ትርጉም ፣ በአቡ አማን የሕያ
ከነጃሺ ማተሚያ ቤት
በቅርቡ ይታተማል - ኢንሻአላህ

https://t.me/NejashiPP

https://bit.ly/3r4948i
1.4K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-01 22:21:02 የገንዘብ ይሁን የጓደኛ ሪዝቅ ከአላህ ነው። በሆነ ጊዜ አላህ ከሰማይ በእዝነት መልክ ያወርድልሃል። በሕይወትህ ጣልቃ እየገቡ መንገድ የሚያቃኑልህን ሰዎች ድንገት ይልክልሃል። ቀልብህን ይዳብሳሉ፣ ቁስልህን ያክማሉ፣ ቅርበታቸው ሰላም ይሰጥሃል፣ መኖራቸው ፀጋ ነው፣ ድምፃቸው ደስታ ነው፣ ፈገግታቸው ጀነት ነው፣ ምክራቸው ጤና ነው። አላህ ይጠብቅልን።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.8K views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-01 22:17:27 ሳላውቅ ኸይር መስሎኝ ወደ መጥፎ ነገር ስንደረደር ለያዘኝና ለጠበቀኝ አላህ ምስጋና ይገባው።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.7K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-31 20:27:03 አብራሪው ማን እንደሆነ እንኳን ሳናውቅ አውሮፕላን ዉስጥ እንተኛለን፣ ዘዋሪዉን ሳናውቅ መርከብ ዉስጥ ለጥ ብለን እናንቀላፋለን።
ሕይወታችንን ማን እንደሚዘዉረው እያወቅን ተረጋግተን መኖርና መተኛት እንዴት ያቅተናል?።

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.2K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 20:58:54 ብዙ ሙስሊም ቤተሰቦች ልጆቻቸው የቁርኣን ሓፊዝ እንዲሆንላቸው ይመኛሉ። እርግጥ ነው ሓፊዝ መሆን መታደል ነው። በዚህም ሆነ በመጨረሻው ዓለም ለልጅም ይሁን ለወላጅ ትልቅ ክብርን ያጎናጽፋል።
ግና አንድ ሰው ሓፊዝ ነው ሲባል ቁርኣንን መሸምደዱ ብቻ አይደለም ዓላማው፣ ትርጉሙን ማወቅና በአስተምህሮው መኖር፣ ለሌላዉም መልካም አርዓያ መሆን ግድ ነው።

አሁን አሁን በርካታ የሒፍዝ ማዕከላት በየአካባቢው ሲከፈቱ እናያለን። ከዉብ ድምፆች እና ከተጅዊድ ባለፈ እንደ ማኅበረሰብ በተጨባጭ ምን ተጠቅመንባቸው ይሆን?

ከሒፍዝ ማዕከላት ይልቅ የዒልም ማዕከላት ናቸው ይበልጥ የሚያስፈልጉን ብዬ አምናለሁ፡፡ የቁርኣንን ትርጉም እና ክብር ሳያውቁ በልጅነታቸው ቁርኣንን በቃላቸው የሸመደዱ ብዙዎችን አይተናል፤ ባደጉና በጎለመሱ ጊዜ ቁርኣን ሐራምን ከመዳፈር አላገዳቸዉም፡፡ ሳያውቁት እንዴት ሊኖሩት?
'ከባሮቹ መካከል አላህን የሚፈሩት አዋቂዎቹ ናቸው።' ይላል ቁርኣን።

ቁርኣንን መሐፈዝ ብቻዉን የአላህን ፍራቻ አያስገኝም። ዓሊምም አያደርግም። ማወቁና መረዳቱ ግድ ነው። በሶላት ኢማምነት ሸምዳጅ እና የቁርኣን ዕውቀት ያለው ቢቀርቡ ለማሰገድ በላጩ አዋቂው ሰው ነው ይላሉ ዑለሞች።

ወላጆች እንድታስቡበት ለማለት ነው።

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.2K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 06:53:20 ታሞ “በምን ዳንክ” ሲሉት በምን እንደዳነ እንኳን የማያውቅ ብዙ ሰው አለ፡፡ አዎ አንዳንድ ጊዜ እንታመምና እንድናለን፤ ምን እንዳዳነን እንኳን አናውቅም፤ ብቻ ድንገት እንድናለን፡፡
አንዳንድ ጊዜ ልክ እንደ እስረኛ በል ከታሰርክበት የጤና ችግር ተፈታ፣ በል ከአልጋህ ተነስ፣ ... ይልሃል ጀሊሉ።

ምን ይሆን ከበሽታችን የፈወሰን?
ምናልባት በመልካም ትዕግስታችን ድነን ይሆናል፣ በጥሩ ተስፋችን ድነን ይሆናል፣ በንፁህ ተውባችን ምክንያት ድነን ይሆናል፣ በሶደቃችን ድነን ይሆናል ማን ያውቃል፣ አላህ የወደደዉን በመውደዳችን ድነን ይሆናል፣ በከባድ ህመም ዉስጥ ባሳየነው ፈገግታ ምክንያት ድነን ይሆናል፡፡ በማይረባና በማይታሰብ ነገር ድነን ይሆናል፡፡ ብቻ በሆነ ነገር የተነሳ ድነናል፡፡ 
ቃል ይሁን ተግባር መልካም ነገር ይፈዉሳል።
በዳመናም ያለ ዳመና እንደሚያዘንበው ሁሉ እሱ በሰበብም ያለ ሰበብም ያድናል፡፡ 
እሱ አላህ ነው፡፡

ሶባሐል ኸይር።


http://t.me/MuhammedSeidABX
2.2K views03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 18:30:07 በሩቅም ይገኝ በቅርብ በምንወደው ሰው አትፈትነን ያ ረብ።
ሐዘኑን፣ ችግሩን፣ ክስረቱን፣ ህመሙን፣ ስደቱን፣ ዉድቀቱን፣ አታሳየን።

http://t.me/MuhammedSeidABX
792 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 13:00:08 ለፍጡራንን የተለያዩ መልካም ነገሮችን የሚያገራው አላህ ነው፣ እኛ ሀይልም ጉልበትም የለን።

፨ የሱንና ፆሞችን የገራልህ እንደሆነ በማይፆሙት አትሳቅ፣
፨ ኒቃብን የገራልሽ እንደሆነ ሒጃብ የሚለብሱትን አትናቂ፣
፨ ቁርኣን ሒፍዝ የገራልህ እንደሆነ ባላፈዙት አታላግጥ፣
፨ በትምህርት የጎበዝክ እንደሆነ ባልጎበዙት ሙድ አትያዝ፣
፨ ንግድና ዱንያ የገራልህ እንደሆነ ድሆችን አትናቅ፣
፨ የሌሊት ሶላት የገራልህ እንደሆነ የማይሰግዱትን አታሸማቅቅ፣
'ከሌሊት ሶላት ተኝተህ ግና ባለመስገድህ ተፀጽተህ ማደርህ ሰግደህ ከምትመፃደቀው ይመረጣል።' ይላሉ ኢብኑል ቀይም።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.1K viewsedited  10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 06:25:48 ሰው ዝምብሎ ፍጡር አይደለም። መልካም ሥራን እንዲያስቀጥል፣ ዓለምንም በበጎ ሥራዎች ሁሉ እንዲያሳምር ምድርን በፈጠራት አምላክ የተወከለ የተከበረ ፍጡር ነው።
እና እንደው ዝምብለህ አትኑር ...

ሰው ሆይ! አንተ የትልቁ ዱንያ ላይ መብራት ነህ፣ ዕድሜህም እንደ ሻማ ነው፣ ሰዓትና ቀን ባለፈ ቁጥር ይቀልጣል፣ ያልቃልም።
ጨለማን ለማብራት፣ መሃይምነትን ለመግፈፍ፣ እውነትን ለመግለጥ፣ በመልካም ነገር ለመምከር፣ የከፋዉን ለማጽናናት፣ መሰናክልን ለማስወገድ ካልሆነ ዝም ብለህ በሆነው ባልሆነው ነገር ሁሉ ቃልህንም ጉልበትህንም አትፍጅ፣ አትቃጠል፣ አትንደድ፣ አትቅለጥ፡፡
አትባክን ወንድሜዋ፡፡

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.2K views03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-27 18:35:11 እኔ የምልሽ …
***
ግርም ከሚሉኝ የሕወት ታሪኮች መካከል አንዱ የእናታችን የእመት ዓኢሻ ነው፡፡ በስንት ዓመቷ አገባች በሚለው ላይ ዉዝግብ ስላለ ልለፈው፡፡ ግና በ18 ዓመቷ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) ተለዩዋት፡፡ አሥር ዓመት እንኳን ከነቢዩ ጋር አልኖሩም፡፡ 

ዓኢሻ ገና በአፍላ ወጣትነቷ ነበር ያዉም በእጅጉ የምትቀናባቸዉን ተወዳጅ ባለቤቷን ያጣችው፣ ልጅ አልነበራትም፡፡የሚገርመው “ልጅ ይኖረኝ ዘንድ ዱዓ አድርጉልኝ” ብላ ነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ.) ወትዉታለች የሚል ሐዲሥ አልተገኘም፡፡ ልብ በሉልኝ። ከርሣቸው ህልፈት በኋላ 47 ዓመታትን ብቻዋን ነው የኖረችው፡፡ አዎ ብቻዋን። አላህ ለዓኢሻ ልጅ ያልሰጣት ስለሚጠላት ነው የሚል ይኖር ይሆን??
አላህ ምንን ለምን እንደዳደረገ የሚያውቅ ጌታ ነው፣ አንችን ባርያዉን አይጠላም እሺ።

እናታችን ዓኢሻ አላህ ሱ.ወ. ልጅ ስላልሰጣት መፈጠሯን አልጠላችም፣ በአምላኳም አላማረረችም። እምነቷን አልቀየረችም። 'የኔስ ተለየ' አላማረረችም። የሷ ባልሆነው ልጅ 'ኡሙ ዐብደላህ' ተብላ እየተጠራች ሙሉ ሕይወቷን በዒባዳ፣ በዕውቀትና በጂሃድ አሳለፈች፡፡ ትላልቅ ሶሐቦች ከሷ ተምረዋል፣ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ለብዙዎች ታስረዳ ነበር፡፡

ከዚህ ምን እንማራለን መሰለሽ ...
ልጅ ስለጠፋ፣ ትዳር ስለጠፋ፣ ቤት ስለጠፋ፣ መኪና ስለጠፋ … ሕይወት አትቆምም ትቀጥላለች፡፡

ዱንያ የፈተና ምድር ናት፣ እሷ ለማንም ሳታደላ ሁሉንም ትፈትናለች። አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሺ ጊዜ ልትፈትን ሁላ ትችላለች። ይህን አምኖ መቀበል ነው የሚሻለው። ሃሳባችንን ሁሉ ተስፋ ሳንቆርጥ ለአላህ እንንገር፣ ለነገሮችም ከልክ በላይ አንጓጓ። ከሆነ ሆነ፣ ካልሆነ ፈሶብሩን ጀሚል .. ዉብ ትዕግስት ብቻ ነው ሚያዋጣው።
ዓኢሻን የፈተነች ዱንያ እኛን ብትፈትን ምኑ ይገርማል።

አዎ .. እስቲ እንረጋጋ
እስክናብድና ናላችን እስኪዞር ደስ በነገሮችና ሀሳቦች አንወጠር፣ ለጤናችንም እንጨነቅ።
አንዳንዴ ደግሞ እስቲ እንርሳቸው። ተሸክመን ከምንዞር ነገሮችን መሬት እናድርጋቸው። የአላህ መሻት ከሌለበት ተስገብግበን የምናመጣው ሪዝቅ የለምና።

የሀብት ይሁን የልጅ፣ የትዳር ይሁን የሥራ ሪዝቅ አላህ ባለው ጊዜ ይመጣል ኢንሻአላህ አይቀርም። እንደማይቀርም አውቀን ቀልባችንን እንሰብስብ። ሄደንበት ካልመጣና ከደከመን በራሱ ጊዜ ይምጣ እንተወው። አላህ የሚወደዉን ነገር ብቻ እንናገር። ከሱ መልካም ነገር እንጠብቅ።

ወዳጆቼ ...
የምትመኙትን ነገር እስኪመጣ እስከዚያው ድረስ ጊዜያችሁን በመልካም ነገር ላይ አሳልፉ፣ በተለይ ሶደቃ። ራሣችሁንና ሌላዉን በሚጠቅም ነገር ቢዚ ሁኑ እሺ። እሺ በሉኝ።
ደግሞም ለሸይጧን መጥፎ ሀሳብና ለክፉ ጥርጣሬ በር አትስጡ። የተስፋ መቁረጥ ስሜት መግቢያ ቀዳዳዎችን ሁሉ ዝጉ ።

እኔ ግን ይህችን ጽፌ እንደወጣሁ አንድ መልካም ነገር እንደማገኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

ብከዳህ የቆምኩባት መሬት ትክዳኝ ረቢ ኪያ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
823 views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ