Get Mystery Box with random crypto!

ለፍጡራንን የተለያዩ መልካም ነገሮችን የሚያገራው አላህ ነው፣ እኛ ሀይልም ጉልበትም የለን። ፨ የ | ABX

ለፍጡራንን የተለያዩ መልካም ነገሮችን የሚያገራው አላህ ነው፣ እኛ ሀይልም ጉልበትም የለን።

፨ የሱንና ፆሞችን የገራልህ እንደሆነ በማይፆሙት አትሳቅ፣
፨ ኒቃብን የገራልሽ እንደሆነ ሒጃብ የሚለብሱትን አትናቂ፣
፨ ቁርኣን ሒፍዝ የገራልህ እንደሆነ ባላፈዙት አታላግጥ፣
፨ በትምህርት የጎበዝክ እንደሆነ ባልጎበዙት ሙድ አትያዝ፣
፨ ንግድና ዱንያ የገራልህ እንደሆነ ድሆችን አትናቅ፣
፨ የሌሊት ሶላት የገራልህ እንደሆነ የማይሰግዱትን አታሸማቅቅ፣
'ከሌሊት ሶላት ተኝተህ ግና ባለመስገድህ ተፀጽተህ ማደርህ ሰግደህ ከምትመፃደቀው ይመረጣል።' ይላሉ ኢብኑል ቀይም።

http://t.me/MuhammedSeidABX