Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ዝምብሎ ፍጡር አይደለም። መልካም ሥራን እንዲያስቀጥል፣ ዓለምንም በበጎ ሥራዎች ሁሉ እንዲያሳም | ABX

ሰው ዝምብሎ ፍጡር አይደለም። መልካም ሥራን እንዲያስቀጥል፣ ዓለምንም በበጎ ሥራዎች ሁሉ እንዲያሳምር ምድርን በፈጠራት አምላክ የተወከለ የተከበረ ፍጡር ነው።
እና እንደው ዝምብለህ አትኑር ...

ሰው ሆይ! አንተ የትልቁ ዱንያ ላይ መብራት ነህ፣ ዕድሜህም እንደ ሻማ ነው፣ ሰዓትና ቀን ባለፈ ቁጥር ይቀልጣል፣ ያልቃልም።
ጨለማን ለማብራት፣ መሃይምነትን ለመግፈፍ፣ እውነትን ለመግለጥ፣ በመልካም ነገር ለመምከር፣ የከፋዉን ለማጽናናት፣ መሰናክልን ለማስወገድ ካልሆነ ዝም ብለህ በሆነው ባልሆነው ነገር ሁሉ ቃልህንም ጉልበትህንም አትፍጅ፣ አትቃጠል፣ አትንደድ፣ አትቅለጥ፡፡
አትባክን ወንድሜዋ፡፡

http://t.me/MuhammedSeidABX