Get Mystery Box with random crypto!

እኔ የምልሽ … *** ግርም ከሚሉኝ የሕወት ታሪኮች መካከል አንዱ የእናታችን የእመት ዓኢሻ ነው፡፡ | ABX

እኔ የምልሽ …
***
ግርም ከሚሉኝ የሕወት ታሪኮች መካከል አንዱ የእናታችን የእመት ዓኢሻ ነው፡፡ በስንት ዓመቷ አገባች በሚለው ላይ ዉዝግብ ስላለ ልለፈው፡፡ ግና በ18 ዓመቷ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) ተለዩዋት፡፡ አሥር ዓመት እንኳን ከነቢዩ ጋር አልኖሩም፡፡ 

ዓኢሻ ገና በአፍላ ወጣትነቷ ነበር ያዉም በእጅጉ የምትቀናባቸዉን ተወዳጅ ባለቤቷን ያጣችው፣ ልጅ አልነበራትም፡፡የሚገርመው “ልጅ ይኖረኝ ዘንድ ዱዓ አድርጉልኝ” ብላ ነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ.) ወትዉታለች የሚል ሐዲሥ አልተገኘም፡፡ ልብ በሉልኝ። ከርሣቸው ህልፈት በኋላ 47 ዓመታትን ብቻዋን ነው የኖረችው፡፡ አዎ ብቻዋን። አላህ ለዓኢሻ ልጅ ያልሰጣት ስለሚጠላት ነው የሚል ይኖር ይሆን??
አላህ ምንን ለምን እንደዳደረገ የሚያውቅ ጌታ ነው፣ አንችን ባርያዉን አይጠላም እሺ።

እናታችን ዓኢሻ አላህ ሱ.ወ. ልጅ ስላልሰጣት መፈጠሯን አልጠላችም፣ በአምላኳም አላማረረችም። እምነቷን አልቀየረችም። 'የኔስ ተለየ' አላማረረችም። የሷ ባልሆነው ልጅ 'ኡሙ ዐብደላህ' ተብላ እየተጠራች ሙሉ ሕይወቷን በዒባዳ፣ በዕውቀትና በጂሃድ አሳለፈች፡፡ ትላልቅ ሶሐቦች ከሷ ተምረዋል፣ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ለብዙዎች ታስረዳ ነበር፡፡

ከዚህ ምን እንማራለን መሰለሽ ...
ልጅ ስለጠፋ፣ ትዳር ስለጠፋ፣ ቤት ስለጠፋ፣ መኪና ስለጠፋ … ሕይወት አትቆምም ትቀጥላለች፡፡

ዱንያ የፈተና ምድር ናት፣ እሷ ለማንም ሳታደላ ሁሉንም ትፈትናለች። አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሺ ጊዜ ልትፈትን ሁላ ትችላለች። ይህን አምኖ መቀበል ነው የሚሻለው። ሃሳባችንን ሁሉ ተስፋ ሳንቆርጥ ለአላህ እንንገር፣ ለነገሮችም ከልክ በላይ አንጓጓ። ከሆነ ሆነ፣ ካልሆነ ፈሶብሩን ጀሚል .. ዉብ ትዕግስት ብቻ ነው ሚያዋጣው።
ዓኢሻን የፈተነች ዱንያ እኛን ብትፈትን ምኑ ይገርማል።

አዎ .. እስቲ እንረጋጋ
እስክናብድና ናላችን እስኪዞር ደስ በነገሮችና ሀሳቦች አንወጠር፣ ለጤናችንም እንጨነቅ።
አንዳንዴ ደግሞ እስቲ እንርሳቸው። ተሸክመን ከምንዞር ነገሮችን መሬት እናድርጋቸው። የአላህ መሻት ከሌለበት ተስገብግበን የምናመጣው ሪዝቅ የለምና።

የሀብት ይሁን የልጅ፣ የትዳር ይሁን የሥራ ሪዝቅ አላህ ባለው ጊዜ ይመጣል ኢንሻአላህ አይቀርም። እንደማይቀርም አውቀን ቀልባችንን እንሰብስብ። ሄደንበት ካልመጣና ከደከመን በራሱ ጊዜ ይምጣ እንተወው። አላህ የሚወደዉን ነገር ብቻ እንናገር። ከሱ መልካም ነገር እንጠብቅ።

ወዳጆቼ ...
የምትመኙትን ነገር እስኪመጣ እስከዚያው ድረስ ጊዜያችሁን በመልካም ነገር ላይ አሳልፉ፣ በተለይ ሶደቃ። ራሣችሁንና ሌላዉን በሚጠቅም ነገር ቢዚ ሁኑ እሺ። እሺ በሉኝ።
ደግሞም ለሸይጧን መጥፎ ሀሳብና ለክፉ ጥርጣሬ በር አትስጡ። የተስፋ መቁረጥ ስሜት መግቢያ ቀዳዳዎችን ሁሉ ዝጉ ።

እኔ ግን ይህችን ጽፌ እንደወጣሁ አንድ መልካም ነገር እንደማገኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

ብከዳህ የቆምኩባት መሬት ትክዳኝ ረቢ ኪያ።

http://t.me/MuhammedSeidABX