Get Mystery Box with random crypto!

ታሞ “በምን ዳንክ” ሲሉት በምን እንደዳነ እንኳን የማያውቅ ብዙ ሰው አለ፡፡ አዎ አንዳንድ ጊዜ እ | ABX

ታሞ “በምን ዳንክ” ሲሉት በምን እንደዳነ እንኳን የማያውቅ ብዙ ሰው አለ፡፡ አዎ አንዳንድ ጊዜ እንታመምና እንድናለን፤ ምን እንዳዳነን እንኳን አናውቅም፤ ብቻ ድንገት እንድናለን፡፡
አንዳንድ ጊዜ ልክ እንደ እስረኛ በል ከታሰርክበት የጤና ችግር ተፈታ፣ በል ከአልጋህ ተነስ፣ ... ይልሃል ጀሊሉ።

ምን ይሆን ከበሽታችን የፈወሰን?
ምናልባት በመልካም ትዕግስታችን ድነን ይሆናል፣ በጥሩ ተስፋችን ድነን ይሆናል፣ በንፁህ ተውባችን ምክንያት ድነን ይሆናል፣ በሶደቃችን ድነን ይሆናል ማን ያውቃል፣ አላህ የወደደዉን በመውደዳችን ድነን ይሆናል፣ በከባድ ህመም ዉስጥ ባሳየነው ፈገግታ ምክንያት ድነን ይሆናል፡፡ በማይረባና በማይታሰብ ነገር ድነን ይሆናል፡፡ ብቻ በሆነ ነገር የተነሳ ድነናል፡፡ 
ቃል ይሁን ተግባር መልካም ነገር ይፈዉሳል።
በዳመናም ያለ ዳመና እንደሚያዘንበው ሁሉ እሱ በሰበብም ያለ ሰበብም ያድናል፡፡ 
እሱ አላህ ነው፡፡

ሶባሐል ኸይር።


http://t.me/MuhammedSeidABX