Get Mystery Box with random crypto!

ብዙ ሙስሊም ቤተሰቦች ልጆቻቸው የቁርኣን ሓፊዝ እንዲሆንላቸው ይመኛሉ። እርግጥ ነው ሓፊዝ መሆን መ | ABX

ብዙ ሙስሊም ቤተሰቦች ልጆቻቸው የቁርኣን ሓፊዝ እንዲሆንላቸው ይመኛሉ። እርግጥ ነው ሓፊዝ መሆን መታደል ነው። በዚህም ሆነ በመጨረሻው ዓለም ለልጅም ይሁን ለወላጅ ትልቅ ክብርን ያጎናጽፋል።
ግና አንድ ሰው ሓፊዝ ነው ሲባል ቁርኣንን መሸምደዱ ብቻ አይደለም ዓላማው፣ ትርጉሙን ማወቅና በአስተምህሮው መኖር፣ ለሌላዉም መልካም አርዓያ መሆን ግድ ነው።

አሁን አሁን በርካታ የሒፍዝ ማዕከላት በየአካባቢው ሲከፈቱ እናያለን። ከዉብ ድምፆች እና ከተጅዊድ ባለፈ እንደ ማኅበረሰብ በተጨባጭ ምን ተጠቅመንባቸው ይሆን?

ከሒፍዝ ማዕከላት ይልቅ የዒልም ማዕከላት ናቸው ይበልጥ የሚያስፈልጉን ብዬ አምናለሁ፡፡ የቁርኣንን ትርጉም እና ክብር ሳያውቁ በልጅነታቸው ቁርኣንን በቃላቸው የሸመደዱ ብዙዎችን አይተናል፤ ባደጉና በጎለመሱ ጊዜ ቁርኣን ሐራምን ከመዳፈር አላገዳቸዉም፡፡ ሳያውቁት እንዴት ሊኖሩት?
'ከባሮቹ መካከል አላህን የሚፈሩት አዋቂዎቹ ናቸው።' ይላል ቁርኣን።

ቁርኣንን መሐፈዝ ብቻዉን የአላህን ፍራቻ አያስገኝም። ዓሊምም አያደርግም። ማወቁና መረዳቱ ግድ ነው። በሶላት ኢማምነት ሸምዳጅ እና የቁርኣን ዕውቀት ያለው ቢቀርቡ ለማሰገድ በላጩ አዋቂው ሰው ነው ይላሉ ዑለሞች።

ወላጆች እንድታስቡበት ለማለት ነው።

http://t.me/MuhammedSeidABX