Get Mystery Box with random crypto!

ABX

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX A
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedseidabx
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.70K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-01-16 22:12:07 የአፍሪካው የድሆች አባት
*****

ጊዜ “ኢስላ እዚህ አካባ አልደረሰም” የሚል መረጃ ደረሳቸዉና ወደዚያ አካባቢ ለመሄድ ወሰኑ፤
ባልደረቦቻቸው ትልቅ ወንዝ ስላለና በወንዙም ዉስጥ አደገኛ አዞዎች ስላሉ ወደዚያች አፍሪካዊት መንደር መዝለቅ እንደማይችሉ ነገሯቸው፡፡
“እኔ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ” እንሂድ አሏቸው፡፡
በአላህ ፈቃድ ወንዙን በሰላም ተሻገሩ፡፡
የመንደሩ ሰዎች “እንዴት ተሻግራችሁ እዚህ ደረሳችሁ?” አሏቸው
የምንንቀሳቀሰው የሱን ሃይማኖት ላልደረሳቸው ለማድረስ ነዉና የሃይማኖቱ ባለቤት ረዳን አሏቸው፡፡
ወደ እስልምና በጠሯቸው ጊዜ የመንደሩ አለቃ የሆነው ሰው “ወደ ኢስላም ለመግባት አንድ መስፈርት አለን፤ እሱን ከፈፀማችሁልን እምነታችሁን እንቀበላለን፡፡” አለ፡፡
ሸይኹ “ምንድነው እሱ?”
“ለዓመታት እዚህ አካባቢ ዝናብ አልዘነበም፣ አምላካችሁን ለምናችሁ ካዘነባችሁልን …” አለ፡፡
ዳዒው ሸይኽ “የመንደሩን ሰዎች ሰብስቡልኝ” አላቸው፡፡ ሰበሰቡላቸው፡፡
ሸይኹ ተነስተው ዉዱእ አደረጉ፣ ሶላት አል-ኢስቲስቃእ ሰገዱ፡፡ በሶላታቸዉም ዉስጥ አብዝተው አለቀሱ፡፡ ሱጁዳቸው ዉስጥ ረጅም ሰዓት ቆዩ፡፡
“አላህ ሆይ እኔን ባርያህን አታሳፍር፡፡” አሉ፡፡
ብዙም ሳይቆይ ሰማዩ አስገመገመ፤ ወዲያዉም ዘነበ፡፡
የመንደሯ ሰዎች በደስታ ጮኹ፡፡
የመንደሯ ሰዎች በአላህ አመኑ፣ እስልምናንም ተቀበሉ፡፡
ሸይኹ አላህን አመሰገኑ፡፡
ደዕዋ ሐያታቸው ነው፤ የኩዌት ዜጋ ሲሆኑ ብዙዉን ኑሯቸዉን በአፍሪካ ነበር ያደረጉት፡፡
ከማዳጋስካር እስከ ሞዛምቢክ እና ማላዊ በአውሬ የተሞሉ እጅግ አደገኛ ተራሮችና ሸለቆዎችን አስፈሪ ጫካዎችን በማቆራረጥ ጭምር ወደ እስልምና ተጣርተዋል፡፡
በአፍሪካ ምድር አሥራ አንድ ሚሊዮን ሰው በእጃቸው እንደሠለመ ይነገራል፡፡
በጥሪያቸው 29 ዓመታትን አሳልፈዋል፡፡ የአፍሪካ ሙስሊም ኤጀንሲ ኃላፊና መሥራችም ናቸው፡፡

5700 መስጂዶችን ፤ 15000 የወላጅ አጥ ማዕከላትን ገንብተዋል፤
124 ሆስፒታሎችን እና የመድሃኒት ቤቶችን 840 የቁርኣን ትምህርት ቤቶችንም አሠርተዋል፡፡
ሸይኽ ዐብዱረሕማን አስ-ሱመይጥ
የአፍሪካ ድሆች አባት በመባል ይታወቃሉ፡፡
በባግዳድ፣ ሊቨርፑል እና ካናዳ የሕክምና ትምህርት ተምረዋል፣
ታመው ጭምር ደዕዋቸዉን ሳያቋርጡ፣ ዕድሜያቸዉን በሙሉ በአላህ መንገድ እንደለፉ በኦገስት 2103 በልብ ህመም ነው ያረፉት፡፡
አላህ ይዘንላቸው፤ ጀነትን ይሸልማቸው፡፡


https://t.me/NejashiPP
831 views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-16 19:49:57 ለአላህ የተተው ነገሮች ሁሉ ሙሉ ዋስትና አላቸው።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.0K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-16 15:24:22 ወይ ጭራ እንደሆናችሁ፣ እንደተዋረዳችሁ ትኖራላችሁ ፣ ወይ ወደ ዲናችሁ ተመልሳችሁ ከፊት ትሆናላችሁ፣ ክብራችሁንም ታስጠብቃላችሁ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.3K views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 21:15:47 ሱብሒ እነሳለሁ ብለህ ነይተህ ተኛ፣
ለሱብሒ መነሳትህ ለአምላክህ ያለህን ዉዴታና ታማኝነት የምትገልጽበት ነው፣
"የሱብሒ ሶላት እንደጦርነት ነው" ጠንካሮች ብቻ ናቸው ሚገኙበት ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
592 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 11:04:22 ለሰው ልጅ የምሰጠው ትልቁ ነገር ማክበር ነው። መከባበር ካለ የሰው ልጅ የግንኙነት ገመዱ እረጅም ነው።
ከመከባበርና ከፍቅር መካከል ምረጥ ብባል ክብርን እመርጣለሁ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
428 views08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-13 15:24:44 አላህ በልቦናዎቻችሁ ዉስጥ ያለን የምታስቡትን ነገር ያውቃል፣ በዚያው መሠረትም ይሠጣችኋል።


http://t.me/MuhammedSeidABX
370 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 19:52:44 ፨ "ወቁሉ ሊናስ ሑስነን" ይላል ቁርአናችን።
፨ 'ለሰዎች መልካምን ተናገሩ' ማለት ነው።
፨ ነቢዩም 'በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ይናገር አልያም ዝም ይበል።' ይላሉ።
፨ ከአንደበታችን የሚወረወር መልካም ቃል የደከመን ያበረታል፣ የታመመን ይፈዉሳል።
፨ ዱንያ ላይ ያለ ሰው ሁሉ ቁስለኛ ነው፣ ለሰው የማያሳየው የተጎዳ ጎን አለው፣
፨ የተጎዳን አይዞህ በሉ፣ የቆሰለን አክሙ፣
፨ መናገር ባትችሉ እንኳን የመልካም ተናጋሪዎችን መልካም በማስተላለፍ በሌሎች አንደበት መልካምን ተናገሩ፣
፨ ቀኑን በብርቱ ትውሉ ዘንድ ማለዳ፣ ለሊቱን በተስፋ ታድሩ ዘንድ ምሽት ላይ አላህ ያስቻለኝን ያህል እናገራለሁ።
ጌታዬ የንግግር ጥበብን ያስተምረኝ ዘንድ እለምነዋለሁ።

መልካም ምሽት።


http://t.me/MuhammedSeidABX
673 views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 11:13:28 የ “ቡሉግ አል-መራም” መጽሐፍ
****
በሙሉ ሥሙ ቡሉግ አል-መራም ሚን አዲለት አል-አሕካም ይሠኛል፡፡

ዓለም ላይ በእጅጉ ከተሠራጩና ዝነኛ ከሆኑ ፍቅሃዊ ይዘት ካላቸው የሐዲሥ መጽሐፎች አንዱ ነው፡፡

አዘጋጁ ፡-  ሺሃቡዲን አቡል ፈድል አሕመድ ኢብኑ ዐሊ ኢብኑ ሙሐመድ አል-ኪናኒ ይባላሉ፡፡
     ኢማም አል-ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር አል-ዐስቀላኒይ በመባል ይታወቃሉ፡፡
         ዐስቀላን - ፈለስጢን ነው የተወለዱት፡፡
        (ከ1371- 1449 ዓ.ል/ ወይም ከ773-852 ዓ.ሂ የኖሩ ናቸው፡፡)
      ታላቅ የሐዲሥ ሊቅ እና ዓሊም ናቸው፡፡
“ፈትሑል ባሪ” የተሠኘው የሶሒሕ ቡኻሪ ማብራሪያ መጽሐፍ ከዝነኛ ድርሠቶቻቸው መካከል ይጠቀሳል፡፡
የመጽሐፉ ይዘት ፡- ሸሪዓዊ ድንጋጌዎችን የተመለከቱ ሐዲሦች የተካተቱበት ነው፡፡
 መጽሐፉ 1596 ሐዲሦችን ይዟል፡፡
መጽሐፉ እጅግ ጠቃሚ ሆኖ በመገኘቱ በተለያዩ ዑለሞች በርካታ ማብራሪያዎች ተሠርተዉለታል፡፡ ሱበለ ሰላም፣ ተውዲሕ አል-አሕካም፣ አል-ኢፍሃም፣ …የተወሰኑት ናቸው፡፡

ከዓመታት በፊት በትናንሽ ጥራዞች ተጀምሮ የነበረው ይህ መጽሐፍ በ2008/2009 በሁለት ቅፆች ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በነጃሺ ማተሚያ ቤት ታትሟል፡፡
ተርጓሚው አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ ሲሆኑ ከበቂ ማብራሪያ ጋር አዘጋጅተዉታል፡፡
አንደኛው ቅጽ ገፆች 506 ያሉት ሲሆን ሁለተኛው 508 ገፆች አሉት፡፡

ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ


https://t.me/NejashiPP


https://bit.ly/3r4948i
108 views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 06:38:14 ለሶላት ስትነሱ ብቻችሁን አትነሱ። ቤተሰቦቻችሁን ቀስቅሱ። ሶላት ከእንቅልፍ፣ ከምግብ፣ ከጨዋታ፣ የምትበልጥ መሆኗንም ለልጆቻችሁ ንገሩ፡፡ ይላሉ።
ኩሉ ሸይኢን በዕደ ሶላት።
ሁሉ ነገር ከሶላት በኋላ።
ማለዳችን የሚባረከው፣ ቀናችን የሚያምረው በሶላት ነው።


http://t.me/MuhammedSeidABX
491 views03:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 22:39:27 'ወደ አላህ ቅረቡ መልካም ነገር ሁሉ ይቀርባችኋል።'
ይላል አሁን ያነበብኩት አንድ መስመር።

ጌታዬ ሆይ ልቀርብህ አልቻልኩም፣ አንተ ግን አትራቀኝ።
ያ ረብ
እደሩልኝ


http://t.me/MuhammedSeidABX
716 views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ