Get Mystery Box with random crypto!

ABX

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX A
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedseidabx
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.70K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-01-27 11:41:06 ትቶህ የሄደን ይሂድ ተወው። ማን እንደሚጎዳ እናያለን። ስላንተ ግድ የሌለዉን ለሰከንድ እንኳን ጊዜ አትስጠው፣ ሞኝ አትሁን። እንደማይገባው እያወቅክ ከፍ ያረግከው እንደሆን የሰው ልጅ ልኩን ይረሳል።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.1K viewsedited  08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 21:09:00 ሕይወት ዋጋዋ ዉድ ነው፣ አላህ ምድር ላይ ያስገኘን ለተራ ጉዳይ አይደለም፣ ያልሆኑ ሪሌሽኖችን ጨክናችሁ አቁሙ፣ በሞቱ ህልሞች ላይ መሠረታችሁን አትገንቡ፣ የማይረቡ ጓደኝነቶችን ቁረጡ፣ በተራ ፊልሞችና መጽሐፎች ጊዜያችሁን አታቃጥሉ፣ ከማይመጥኗችሁ ሰዎች ጋር አትዋሉ፣ ቁምነገር በማይገኝባቸው ቦታዎች ላይ አትገኙ፡፡

እነኚህ ነገሮች ሁሉ ከዕድሜያችሁ ይቆርጣሉ፣ ከሕይወታችሁ ይቀንሳሉ፡፡ መኖራችሁ ካልቀረ ኮስተር በሉ፡፡ እውነተኛ ሕይወት ኑሩ፣ በፍቅር የተሞላ፣ በቁምነገር የታጀበ ሕይወት፡፡

መሳአል ኸይር


http://t.me/MuhammedSeidABX
605 views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 20:10:58 ነጭ ሳንቲም ለጥቁር ቀን እንዲል አባባሉ
የሰላምና የደስታ ምንጭ ነው ብላችሁ
ገንዘባችሁን ትጠብቃላችሁ ትንከባከባላችሁ አይደል?
እውነቴን ነው የምላችሁ
የቤታችሁ ዋና የደስታ ምንጭ ግን ሚስታችሁ ናት፣
እሷ ናት ሰላም የምትሰጣችሁ የምትነሳችሁ፣
ከሰው ከተጣላህ ወደ ቤትህ ትገባለህ፣
ከሚስትህስ ከተጣላህ ወየት አባህ ትሄዳለህ?

http://t.me/MuhammedSeidABX
789 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 15:09:24 ተውሒድ ሲባል በቃል የሚመሰከር ሸሃዳ ብቻ አይደለም፡፡ በተግባር የሚኖሩት ሕይወት እንጂ፡፡ የሚያሳዝነው ዛሬም ላይ ከአላህ ይልቅ ሸሆቹን፣ ቃልቾቹን፣ ጅኖቹን፣ ቆሌዎቹን .. የሚፈሩ ብዙ ናቸው፡፡ አላህን ፈጽሞ ረስተው በየቀብሩ፣ በየዶሪሑ፣ በየቃልቻው ቤት የሚያደገድጉም በርካቶች ናቸው፡፡
ተውሒድ የጥንት የተዋት ቃልኪዳናችን ነው፡፡ ከአላህ ዉጭ ላንፈራ፣ ከአላህ ዉጭ ላናመልክ፣ ከአላህ ዉጭ ላንከጅል፡፡
ሁሌም ለአላህ የገባችሁትን ቃል ጠብቁ። ከርሱ ዉጭ ከማንም አትጣበቁ።

ወላሂ ይገርመኛል … ስንቶች ናቸው! አላህን ለማግኘት ብለው ከአላህ የራቁ፡፡ ወደ አላህ የሚደርሱት በሸሆቹ እና በወሊዮቹ በኩል ብቻ መሰላቸዉና የአላህን ሥም አንድም ቀን ሳይጠሩ፣ ወደ አላህም አንድ ቀን እጃቸዉን ሳያነሱ፣ ሸሆቹ እግር ላይ ወድቀው፣ ወሊዮቹ በሚሏቸው በር ላይ ተደፍተው እነርሱን ሲያገለግሉና ሲኻድሙ ኖረው ዱንያን የተሰናበቱ፡፡
ጌታዬን አንተን ከማግኘት ከሚጋርድ ዕውቀት አንተው ጠብቀኝ፡፡

ወሏሁል ሙስተዓን

http://t.me/MuhammedSeidABX
855 views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 11:13:03 https://www.facebook.com/100001438609403/posts/4900078556716716/
991 views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 08:49:07



እየገባችሁ ሼር እያደረጋችሁ ፣ ተራኪው ጀዕፈር አሕመድ ነው
1.1K views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-23 20:57:48 አይጠቅማችሁም፡፡ ቲክ ቶክ ሲቀጠቅጡ መዋል አይጠቅማችሁም፣ ረጅም ሰዓት በማይረባ ቻት ላይም መቆየትም አይጠቅማችሁም፣ በዩቱዩብ አልባሌ ወሬ ተጠምዳችሁ መዋልም አይጠቅማችሁም፣ ምን አለ ምን ተባለ አይጠቅማችሁም፣ ፋይዳ በሌለው ፊልም ምሽታችሁን ማባከናችሁም አይጠቅማችሁም፡፡
የሚጠቅማችሁ ዲን ነው፣ ቁምነገር ነው፣ ሥራ ነው፣ መማር ወይም ማስተማር፣ መፃፍ ወይም ማንበብ ነው፣ ዕድሜያችሁን ራሣችሁንም ሆነ የሰዉን ልጅ በሚጠቅም ሥራ ላይ ማሳለፍ ነው ፡፡ ለዕድሜያችሁ አስቡ፣ ለጊዜያችሁ ሰስቱ አደራ፡፡ አላህ ይሁነን፡፡

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.6K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-22 10:37:10 አንደኛው ናይት ክለብ ውስጥ ሞተ፣
ሁለተኛው መስጂድ ውስጥ ሞተ።
የመጀመሪያው ሊዘፍን ሳይሆን ሊመክር ነበር የገባው ።
ሁለተኛው ሊሰግድ ሳይሆን ጫማ ሊሰርቅ ነበር የገባው።
እኛ ላያቸዉን እናይና የመሰለንን እንናገራለን ።
የልብ አውቃው ጌታ አላህ ግን በኒያቸው መሠረት ይፈርዳል።
ወደርሱ የምንቀርበው ማናችን እንደሆንን አላህ ብቻ ነወ የሚያውቀው።

http://t.me/MuhammedSeidABX
900 views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 21:36:53 ከሷ ተጣልቶ ነው መሰል ሰሞኑን ደግሞ መፃፍ ትቷል።
የፍቅርን ኃያልነት አውቃለሁ፣
ግና
ሲሄድ የምትሄዱ፣ ሲቀመጥ የምትቀመጡ፣ በሰው ሳንባ የምትተነፍሱ ልፍስፍሶች አትሁኑ።

ከአላህ ዉጭ ማንም ቢሆን ፍፁም በሆነ መልኩ አንጎላችሁን እንዲቆጣጠር አትፍቀዱ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.2K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-16 23:45:50 ዱዓ አርጌ፣ አላህን ለምኜ ምንም ያገኘሁት ነገር የለም የሚል ካለ በርግጥ ጌታዉን አላወቀም ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
702 views20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ