Get Mystery Box with random crypto!

ተውሒድ ሲባል በቃል የሚመሰከር ሸሃዳ ብቻ አይደለም፡፡ በተግባር የሚኖሩት ሕይወት እንጂ፡፡ የሚያሳ | ABX

ተውሒድ ሲባል በቃል የሚመሰከር ሸሃዳ ብቻ አይደለም፡፡ በተግባር የሚኖሩት ሕይወት እንጂ፡፡ የሚያሳዝነው ዛሬም ላይ ከአላህ ይልቅ ሸሆቹን፣ ቃልቾቹን፣ ጅኖቹን፣ ቆሌዎቹን .. የሚፈሩ ብዙ ናቸው፡፡ አላህን ፈጽሞ ረስተው በየቀብሩ፣ በየዶሪሑ፣ በየቃልቻው ቤት የሚያደገድጉም በርካቶች ናቸው፡፡
ተውሒድ የጥንት የተዋት ቃልኪዳናችን ነው፡፡ ከአላህ ዉጭ ላንፈራ፣ ከአላህ ዉጭ ላናመልክ፣ ከአላህ ዉጭ ላንከጅል፡፡
ሁሌም ለአላህ የገባችሁትን ቃል ጠብቁ። ከርሱ ዉጭ ከማንም አትጣበቁ።

ወላሂ ይገርመኛል … ስንቶች ናቸው! አላህን ለማግኘት ብለው ከአላህ የራቁ፡፡ ወደ አላህ የሚደርሱት በሸሆቹ እና በወሊዮቹ በኩል ብቻ መሰላቸዉና የአላህን ሥም አንድም ቀን ሳይጠሩ፣ ወደ አላህም አንድ ቀን እጃቸዉን ሳያነሱ፣ ሸሆቹ እግር ላይ ወድቀው፣ ወሊዮቹ በሚሏቸው በር ላይ ተደፍተው እነርሱን ሲያገለግሉና ሲኻድሙ ኖረው ዱንያን የተሰናበቱ፡፡
ጌታዬን አንተን ከማግኘት ከሚጋርድ ዕውቀት አንተው ጠብቀኝ፡፡

ወሏሁል ሙስተዓን

http://t.me/MuhammedSeidABX