2021-12-27 06:02:52
ሰሞኑን አንድ ወዳጃችን ከረጅም ጊዜ በኋላ አላህ ልጅ ሠጥቶት ከባድ ዒሽቅ ላይ ነው፣
የማይበርድ ሐሴት!።
ዐጂብብብብብ ! ያስብላል
'እንዴት ነው ደስታው?' አልኩት።
'እንዲህ ያለም የለ!!፣' አለኝ።
(አባባሉን ደጋግሙት እስቲ)
አስከተለ ...
" አንዷ እንዲሁ እንደኔው ደስ ብሏት አንድ ሸህ ዘንድ ሄደች አሉ" አለኝ።
እህሳ አልኩት
" እንደው ደስ ብሎኛል አላህዬን ምን ብዬ ላመስግን?" አለቻቸው።
"አልሐምዱ ሊላህ በይ" አሏት።
ቅር አላት፣ አነሰባት።
"ሌላ የሚባል ነገር የለም?" አለቻቸው።
"ዝም ብለሽ 'አልሐምዱ ሊላህ' በይ" አሏት።
"እንግዲያዉስ እሱ ነው ያሳነሰው ምን ላርግ።" አለች።
ለአላህ ምን ታድርግ!
አላረካ እያላት "አልሐምዱ ሊላህ ! " አለች።
'አልሐምዱ ሊላህ' በርግጥ ሚዛንን ትሞላለች።
ሰባሐል ኸይር
http://t.me/MuhammedSeidABX
986 views03:02