Get Mystery Box with random crypto!

አልሆነም አይደል ... በቃ የአላህ መሻት በለጠና እርሱ ያለው ሆነ። ያለ ሀሜት፣ ያለ ወሬ፣ ያ | ABX

አልሆነም አይደል ...
በቃ የአላህ መሻት በለጠና እርሱ ያለው ሆነ።
ያለ ሀሜት፣ ያለ ወሬ፣ ያለ ሥም ማጥፋት ግንኙነታችሁን ቁረጡት። በሱ በፊት ማውራት የማትደፍሩትን ነገር ሰው ከሄደ በኋላ አታውሩ።
ያኔ በአላህ ፈቃድ የተዋወቃችሁባቸዉን እና ጥሩ ጊዜ ያሳለፋችሁባቸዉን እነዚያን መልካም ቀናት አክብሩ። አንዳችሁ ለአንዱ የዋለዉንም ዉለታ አትርሱ።
መልካም መልካሙን እያስታወሳችሁ አልሐምዱ ሊላህ በሉ።
እስከመጨረሻው ድረስም ሰላማዊ እና በጎ አሳቢ ሁኑ።

http://t.me/MuhammedSeidABX