Get Mystery Box with random crypto!

ABX

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX A
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedseidabx
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.70K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2021-12-14 18:48:30 ሁሉም ዕዳዎች ይከፈላሉ የእናት ዕዳ ሲቀር። በእናት ጉዳይ ተጠንቀቁ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.4K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-13 19:36:55 ላንተ ለመኖር እየሞከርኩ ነው አግዘኝ ያ ረብ

http://t.me/MuhammedSeidABX
775 views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-13 19:30:01 አላህ አንዳንድ ነገሮችን ድብቅ ያደረጋቸው ለምክንያት እንደሆነ በፅኑ አምናለሁ። ጌታዬ ጥበቡ እና ዕውቀቱ ፍፁም ነዉና። እሱ የሸፈነው ነገር እንደተሸፈነ ሲኖር ደስ ይላል። በጀሊሉ ሥራና ጥበብ ዉስጥ ሁሌም ጎልቶ የሚነበበብ ትልቅ ትምህርት አለ።

በተፈጥሮ አላህ የደበቃቸዉን ነገሮችን ቀድሞ ለማወቅ መጣር ኋላ ላይ ያን ነገር አሰልቺ እና ጣዕም አልባ ያደርገዋል ብዬ አስባለሁ። ቴክኖሎጂ ግን ከፀሐይ በታች አዲስ የለም አለና ሁሉን ነገር ገላልጦ አረፈው። የዘመኑ ሰዉም እሱን ተከተለና ነገሮችን ቀድሜ ካላወቅኩ አለና በገዛ እጁ ራሱን በራሱ ረበሸ።
ለምሳሌ - አላህ ልጅ የሠጣቸው ወላጆች በርግዝና ፀጋ የባረካቸዉን አምላካቸዉን በብዙ ከማመስገን ይልቅ የፅንሱን ምንነት ለማወቅና ሽፍኑን ለመግለጥ የሚጣደፉበት ዘመን ላይ ነን። ደስ ቢላቸዉም ባይላቸዉም አላህ የከተበዉን ላይቀይሩ ነገር። ገና አራት ወር ላይ ያለን ፅንስ ፆታው ምንድነው? ብሎ ወላጆችን መጠየቅም የጤና አይመስለኝም።

ዉሃን ሰብስቦና ዘርን አዋህዶ ፅንስን የሚፈጥር፣ በእናቱ ሆድ ዉስጥ ተንከባክቦ የሚያሳድግ፣ ቀኑን ጠብቆ በሰላምም ወደ ምድር እንዲመጣ የሚያደርግ አላህ ነው። የኛ ድርሻ ታላቅ በረከቱን አመስግኖ መቀበል ነው። ወደ ዱንያ መንገድ የጀመረን ልጅ አላህ በሰላምና ጤና ያምጣው። የምንጠቀምበት እንጂ የምንፈተንበት አያድርገው።

የልጅ ፆታን በአልትራሳዉንድ አይተው ካወቁ በኋላ በከፍተኛ ደስታም እና በቀዘቀዝ ስሜት ዜናዉን የተቀበሉ ሰዎችን አየሁ። ከማወቁ በፊት እና በኋላ በወላጆች ላይ የሚታይ ስሜት አንድ እንዳልሆነም ታዘብኩ። ቀዝቃዛው ስሜት የአላህን ፀጋ ማንኳሰስ ነው።

ስለሆነም ከአላህ ስጦታ አንፃር እይታችን መስተካከልና እኩል መሆን አለበት ብዬ አሰብኩ። ልጅን የሚሰጥ አላህ ብቻ ነው። አይደል እንዴ?!። ምንም ይሁን ምን አላህ የሰጠው ነገር ዋጋው መቀነስ የለበትም። የአላህ ስጦታ ግራዉም ቀኝ፣ ቀኙም ቀኝ ነው። በረከቱ ትንሹም ትልቅ፣ ትልቁም ትልቅ ነው። የሱ ሁሉም ፀጋው የሚመሰገን እንጂ አስተያየት የሚሰጥበት አይደለም።

በማኅፀን ያለ ልጅ ተጠቅልሎ የተቀመጠ የአላህ ስጦታ ነው። ስጦታዉን በእጅ ላይ በደረሰ ጊዜ መክፈት የበለጠ ደስ ይላል ወደማለት።

ወላድ ሁሌም በሞገስና በድባብ ትሂድ።

ጧበት ለይለትኩም።


http://t.me/MuhammedSeidABX
837 views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-13 09:29:34 አንድ አማኝ ትናንት ሐራም ነው ብሎ ሲከራከርበት የነበረን ጉዳይ ዛሬ ሐላል ነው ብሎ የሚከራከር ከሆነ ኢማኑ አደጋ ላይ ነው ይላሉ ሑዘይፋ ኢብኑ አልየማኒ።

እስቲ ራሳችንን እንገምግም ። ከስንት ጠንካራ አቋም ወርደን ነው እዚህ የደረስነው። ስንቱን ነገር በራሣችን ድክመትና ነፍሲያ ሐላል አድርገናል?

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.0K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-12 19:46:13 አላህ አዕምሮ ሰጥቶን ከፍጥረታቱ ሁሉ አከበረን፣
እኛ ስሜታችንን ተከትለን ከሰዉነት ደረጃ ወረድን።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.2K views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-12 18:47:45 በትልቅ የአላህ ፀጋ ዉስጥ ዋልን፣ እሱም የአላህ ሲትር ነው።
አዛኙ አላህ ገመናችንን ሸፈነ። ሲትራችን ቢገለጥ ኖሮ ስንት ጉዳችን በወጣ።

ያ ረብ ከኔ ጋር ሁን።

እንዴት አመሻችሁ ወዳጆቼ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.3K views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-12 04:27:29 በየቀኑ በሰላምና ጤና ስለምንቀበላቸው ቀናት ሁሉ ምስጋና ለአላህ ይሁን።

አልሐምዱ ሊላህ

እንዴት አደራችሁ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.3K views01:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-10 22:24:54 እኛ የዱንያ አይደለንም፣
ዱንያም የኛ አይደለችም፣
እኛ የአላህ ነን፣
ወደ አላህም ተመላሾች ነን።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.5K views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-09 09:53:18 * ሰይዲ
አቤት
* ወንጀሌ ብዙ ነው
ምህረቱ ሰፊ ነው፣
* አስቀያሚ እኮ ነኝ
እሱ ቆንጆ ነው፣
* ከሱ እሩቅ ነኝ
እሱ ቅርብ ነው፣
* ደከመኝ
እሱ ብርቱ ነው፣
* በየቀኑ አጠፋለሁ
አዛኝ ነው፣
* ይምረኝ ይሆን
አትጠራጠር ፣
* ይወደኝ ይሆን
ባርያው እኮ ነህ፣
* እደርስ ይሆን
ተስፋ አትቁረጥ፣
* ያውቀኝ ይሆን
ፈጥሮህ የለ።።



ጌታዬ አሁንስ ካንተ ለመገናኘት ቸኮልኩ!


http://t.me/MuhammedSeidABX
2.2K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-09 09:28:01 ማንንም ሰው አትመን፣ ከሱ የተፈጠርከው አፈር እንኳን አንድ ቀን መልሶ ይቀብርሃል።

አለኝ አንዱ ሲመክረኝ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.6K views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ