Get Mystery Box with random crypto!

ABX

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX A
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedseidabx
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.70K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-20 17:34:49 ዲንን ኡስታዝ ወይም ዓሊም ነኝ የሚል አስመሳይ ከቀበሮ ከተማርክ፤ ኋላ ላይ የሚሰማህ ነገር ቢኖር ዶሮ መስረቅ አጅር እንዳለው ነው። ይላሉ።
ዲንን ከዲን ሰው፣ አላህን ፈሪ እና ዓሊም ከሆነ ሰው ተማሩ።
ዓሊም የሆነ ሰው ምልክቱ አላህን መፍራቱ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.5K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:31:10 መሞትና መኖር
·        መሞት ለአላህ (ሱ.ወ.) ሲሆን ህይወት ነው፡፡
·        እጅ መስጠት ለሀያሉ ፈጣሪ ሲሆን ማሸነፍ ነው፡፡
·        መውደቅ ለታላቁ አምላክ ሲሆን የበላይነት ነው፡፡
·        መስገብገብ ለጀነት ሲሆን ጉጉት ነው፡፡
·        መደህየት የአላህ (ሱ.ወ.( ውዴታ ተፈልጎበት እንደሆነ ሀብት ነው፡፡
·        መሸሽ ከሀጢኣት ሲሆን ጀግንነት ነው፡፡

ስለሆነም ወዳጆቼ ሆይ! የዘላለም ህይወት ከፈለግን በአላህ መንገድ ላይ እንሙት፡፡ በነገሮች ውስጥ ሁሉ ማሸነፍ ካሰብን ለአምላካችን እጅ እንስጥ፡፡ ጀነትን ካለምን እንስገብገብላት፡፡   


http://t.me/MuhammedSeidABX
1.8K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:22:23 ታላቁ ሰሓባ ዐብዱላህ ኢብኑ ሑዛፋ ረ.ዐ. ከእስልምና በፊት ምንም ጥረትም ሆነ አስተዋጽኦ አልነበረውም፡፡ የአላህ ፈቃድ ሆነና እስልምናን ተቀበለ፡፡ ከሰለመ በኋላ በምርኮነት በሩም ንጉስ እጅ ወደቀ፡፡ ንጉሱም ሊገድለው አሰበ፡፡
‹ሃይማኖትህን የምትተው ከሆነ ይህን ያህል ሀብት እሰጥሃለሁ፡፡› አለው፡፡
ሑዘይፋም ‹በአላህ እምላለሁ ሃይማኖቴን እንድተው ብለህ ሙሉ ሀብትህን ብትሰጠኝ የምተው አይደለሁም፡፡› አለው፡፡
ቀጥሎም ‹ሃይማኖትህን ከተውክ ከሥልጣኔ አካፍልሃለሁ፡፡› በማለት ሊያግባባው ሞከረ፡፡
ሑዘይፋም ‹በአላህ እምላለሁ የዚህ ዓለም ስልጣን ለኔ ምንም አይደለም፡፡› አለው፡፡
‹እንግዲያውስ እገድልሃለሁ፡፡› አለው፡፡
ሑዘይፋም ‹የሻህን መስራት ትችላለህ፡፡› አለው፡፡
ንጉሱ ጋሻጃግሬዎቹን ‹በቀስት ወጋጉትና አሰቃዩት፡፡ አትግደሉት፡፡› በማለት አዘዛቸው፡፡
ከፍተኛ ስቃይ እስኪሰማው ድረስ እጆቹን በቀስት ወጋጉት፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡› በማለትም ጠየቁት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
‹በቀስቱ እግሩን ወጋጉት› አላቸው፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡› አሉት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
ንጉሱ በመቀጠልም ‹ሁለት ባልደረቦቹን አምጡና በበርሜል ዘይት በማፍላት እዚያ ውስጥ ክተቷቸው፡፡› አለ፡፡ ከሱ ጋር የነበሩትን ሁለት ሙስሊሞች አመጡና ዐይኑ እያየ በፈላ ዘይት ውስጥ ከተቷቸው፡፡ አሁንም ጠየቁት፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡ አለበለዚያ …› አሉት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
‹በሉ ውሰዱና ዘይቱ ውስጥ ክተቱት፡፡› አላቸው፡፡
ሊከቱት ወደ በርሜሉ ሲያስጠጉት ታላቁ ሑዘይፋ ረ.ዐ. አለቀሰ፡፡
ሰዎቹ ይህንኑ ለንጉሱ ነገሩት፡፡ ንጉሱም ‹መልሱት ወዲህ› አላቸው፡፡ መልሰው አመጡት፡፡
ንጉሱም ‹ማልቀስህ ተነግሮኛል፡፡› አለው፡፡ ሑዘይፋም ‹አዎን› አለው ለንጉሱ፡፡
‹እንግዲያውስ ሃይማኖትህን ተው፡፡› አለው፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አለ፡፡
‹እንግዲያውስ ለምን አለቀስክ?› አለው፡፡
‹በአላህ መንገድ የምሰጠው ነፍስ አንዲት ብቻ መሆኗ ነው ያስለቀሰኝ፡፡ በሰውነቴ ላይ ባለው ፀጉር ልክ ነፍስ ቢኖረኝና በአላህ መንገድ አንድ በአንድ ብሰጥ እመኝ ነበር፡፡› አለው፡፡

ለተጨማሪ መሳጭ ታሪኮች
ቢስሚከ ነሕያ መጽሐፍን ያንብቡ።
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል።

https://t.me/NejashiPP
1.6K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 19:12:15 አይሳካልኝም ብለህ ስትብሰለሰል ከቆየህ ከብዙ ጭንቀት በኋላ በመጨረሻም ስጋትህ ሁሉ ከንቱ ሆኖ አልፎ ስታገኘው …. እንዲህ ትላለህ

-   ለካ ዝምብዬ ነበር  የተጨነቅኩት፣
-   መጨነቄ ከተገቢው በላይ ነበር፣
-   እንደው ዝምብዬ እኮ ነው የፈራሁት፣
-   መረጋጋት ነበረብኝ፣
-   ክፉ መጠርጠሬ ትክክል አልነበረም፣
-   ሁሉ ነገር በእጄ መስሎኝ ነበር ዝምብዬ ተስገበገብኩ፣
-   ለወቀሳና ለመጥፎ አቋም ቸኩያለሁ፣
-    የማያልፍ ማዕበል የለም፣ ላያልፍ የመጣ ነገርም የለም፣

አላህዬ መልካም ነገር እንጂ አያስብልኝም።


ከአላህ ጋር ሊኖረን ከሚገቡ ሥርዓቶች መካከል በመከራ ጊዜ አለመደናገጥ፣ በችግር ጊዜ አለመረበሽ ነው፡፡


http://t.me/MuhammedSeidABX
1.7K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 15:12:01 አንዳንድ ቁስል አይድንም፣
አንዳንድ መሰበር አይጠገንም፣
አንዳንድ ህመም አይፈወስም፣
አንዳንድ ሐዘን አይሽርም፣
አንዳንድ ሀሳብ አያልቅም፣
አንዳንድ ትዝታ አያረጅም።

ጨምሩበት

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.7K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:17:49 ሲርበው ብቻ የሚያውቅህ ሲጠግብ ይክድሃል ይላሉ።
ሲቸግረን ብቻ ዘመድን፣ ጓደኛን፣ ወዳጅን ከማስታወስ አባዜ አላህ ይጠብቀን።

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.9K views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 10:35:18 "አላህ ሆይ ወደ መልካም ሥነምግባራት ምራኝ። ወደ መልካም ነገር የሚመራ ካንተ ዉጭ ማንም የለምና።"
ይሉ ነበር የአላህ መልዕክተኛ ሶ.ዐ.ወ.

https://t.me/NejashiPP

https://bit.ly/3r4948i
1.9K views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 10:03:40 ዱንያ ላይ ስትኖሩ ነገ በአኺራ ልታገኙት ከምትናፍቁት ሰው ጋር ተወዳጁ።

የዛሬ መገናኘት ምንም አይደል። የነገው ግን ትልቅ ጥፍጥና አለው።

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.0K views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 14:17:29 ሌባ ቢለብሰው ኒቃብ ምን አጠፋ!
ሙናፊቅ ቢሰግደው ሶላት ምኑ ከፋ!
አጭበርባሪ ቢያሳድገው ፂም ምን አጎደለ!
አታላይ ቢያሳጥረው ሱሪ ምን በደለ!
ዐረቄ ቢጨመቅበት ገብስ አይወቀስም፣
ጃሂል ቢያሸብርበት ኢስላም አይኮሰስም።

ዲኑን እና ምልክቱን ሳይሆን አጥፊ ሰዎችን ብቻ ነጥላችሁ ተቹ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.2K views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:37:26 ኢማም አር-ራዚ እንደሚሉት ...

የሕመምተኛው ሁኔታ መጥፎ መኾኑን የሚያውቅ ቢሆንም እንኳን ሐኪም የኾነ ሰው ለሚያክመው ሰው ተስፋ መስጠት ይኖርበታል።
አንዳንድ ጊዜ ሰውነት ለጥሩ ቃላቶች ሳይታሰብ እጅግ አዎንታዊ ምላሽ የሚሠጥበት ሁኔታ አለ።

አንዳንድ አገራት በፕሪስክሪፕሽናቸው ግርጌ ጥሩ ጥቅሦችንና መልዕክቶችን በመፃፍ ለህመምተኛ ተስፋ ይሠጣሉ። በአካል ከመዳን በፊት በሥነልቦና መዳን ትልቅ ነገር ነው።

~ አላህ እንድንም በሽታ አልፈጠረም መድኃኒት የፈጠረለት ቢሆን እንጂ ።

~ ኢንሻአላህ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ይድናሉ።
~ ከበሽታም እዝነት የኾነ አለ አብሽሩ።
~ አላህ እያለ የምን ሐዘን!
~ አማኝ በሚወጋው እሾህ እንኳ አላህ ዘንድ ምንዳ አለው።
~ የሚሆነው ነገር ሁሉ በአላህ ፈቃድና ዉሳኔ ነው።
~ መታመማችሁ ላለመስገዳችሁ ምክንያት ሳይሆን ይበልጥ ወደ አላህ የምትቃረቡበት አድርጉት።
~

http://t.me/MuhammedSeidABX
2.2K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ