Get Mystery Box with random crypto!

የአፍሪካው የድሆች አባት ***** ሆነ ጊዜ “ኢስላም እዚህ አካባቢ አልደረሰም” የሚል መረጃ ደ | ABX

የአፍሪካው የድሆች አባት
*****

ጊዜ “ኢስላ እዚህ አካባ አልደረሰም” የሚል መረጃ ደረሳቸዉና ወደዚያ አካባቢ ለመሄድ ወሰኑ፤
ባልደረቦቻቸው ትልቅ ወንዝ ስላለና በወንዙም ዉስጥ አደገኛ አዞዎች ስላሉ ወደዚያች አፍሪካዊት መንደር መዝለቅ እንደማይችሉ ነገሯቸው፡፡
“እኔ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ” እንሂድ አሏቸው፡፡
በአላህ ፈቃድ ወንዙን በሰላም ተሻገሩ፡፡
የመንደሩ ሰዎች “እንዴት ተሻግራችሁ እዚህ ደረሳችሁ?” አሏቸው
የምንንቀሳቀሰው የሱን ሃይማኖት ላልደረሳቸው ለማድረስ ነዉና የሃይማኖቱ ባለቤት ረዳን አሏቸው፡፡
ወደ እስልምና በጠሯቸው ጊዜ የመንደሩ አለቃ የሆነው ሰው “ወደ ኢስላም ለመግባት አንድ መስፈርት አለን፤ እሱን ከፈፀማችሁልን እምነታችሁን እንቀበላለን፡፡” አለ፡፡
ሸይኹ “ምንድነው እሱ?”
“ለዓመታት እዚህ አካባቢ ዝናብ አልዘነበም፣ አምላካችሁን ለምናችሁ ካዘነባችሁልን …” አለ፡፡
ዳዒው ሸይኽ “የመንደሩን ሰዎች ሰብስቡልኝ” አላቸው፡፡ ሰበሰቡላቸው፡፡
ሸይኹ ተነስተው ዉዱእ አደረጉ፣ ሶላት አል-ኢስቲስቃእ ሰገዱ፡፡ በሶላታቸዉም ዉስጥ አብዝተው አለቀሱ፡፡ ሱጁዳቸው ዉስጥ ረጅም ሰዓት ቆዩ፡፡
“አላህ ሆይ እኔን ባርያህን አታሳፍር፡፡” አሉ፡፡
ብዙም ሳይቆይ ሰማዩ አስገመገመ፤ ወዲያዉም ዘነበ፡፡
የመንደሯ ሰዎች በደስታ ጮኹ፡፡
የመንደሯ ሰዎች በአላህ አመኑ፣ እስልምናንም ተቀበሉ፡፡
ሸይኹ አላህን አመሰገኑ፡፡
ደዕዋ ሐያታቸው ነው፤ የኩዌት ዜጋ ሲሆኑ ብዙዉን ኑሯቸዉን በአፍሪካ ነበር ያደረጉት፡፡
ከማዳጋስካር እስከ ሞዛምቢክ እና ማላዊ በአውሬ የተሞሉ እጅግ አደገኛ ተራሮችና ሸለቆዎችን አስፈሪ ጫካዎችን በማቆራረጥ ጭምር ወደ እስልምና ተጣርተዋል፡፡
በአፍሪካ ምድር አሥራ አንድ ሚሊዮን ሰው በእጃቸው እንደሠለመ ይነገራል፡፡
በጥሪያቸው 29 ዓመታትን አሳልፈዋል፡፡ የአፍሪካ ሙስሊም ኤጀንሲ ኃላፊና መሥራችም ናቸው፡፡

5700 መስጂዶችን ፤ 15000 የወላጅ አጥ ማዕከላትን ገንብተዋል፤
124 ሆስፒታሎችን እና የመድሃኒት ቤቶችን 840 የቁርኣን ትምህርት ቤቶችንም አሠርተዋል፡፡
ሸይኽ ዐብዱረሕማን አስ-ሱመይጥ
የአፍሪካ ድሆች አባት በመባል ይታወቃሉ፡፡
በባግዳድ፣ ሊቨርፑል እና ካናዳ የሕክምና ትምህርት ተምረዋል፣
ታመው ጭምር ደዕዋቸዉን ሳያቋርጡ፣ ዕድሜያቸዉን በሙሉ በአላህ መንገድ እንደለፉ በኦገስት 2103 በልብ ህመም ነው ያረፉት፡፡
አላህ ይዘንላቸው፤ ጀነትን ይሸልማቸው፡፡


https://t.me/NejashiPP