Get Mystery Box with random crypto!

የ “ቡሉግ አል-መራም” መጽሐፍ **** በሙሉ ሥሙ ቡሉግ አል-መራም ሚን አዲለት አል-አሕካም ይሠኛ | ABX

የ “ቡሉግ አል-መራም” መጽሐፍ
****
በሙሉ ሥሙ ቡሉግ አል-መራም ሚን አዲለት አል-አሕካም ይሠኛል፡፡

ዓለም ላይ በእጅጉ ከተሠራጩና ዝነኛ ከሆኑ ፍቅሃዊ ይዘት ካላቸው የሐዲሥ መጽሐፎች አንዱ ነው፡፡

አዘጋጁ ፡-  ሺሃቡዲን አቡል ፈድል አሕመድ ኢብኑ ዐሊ ኢብኑ ሙሐመድ አል-ኪናኒ ይባላሉ፡፡
     ኢማም አል-ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር አል-ዐስቀላኒይ በመባል ይታወቃሉ፡፡
         ዐስቀላን - ፈለስጢን ነው የተወለዱት፡፡
        (ከ1371- 1449 ዓ.ል/ ወይም ከ773-852 ዓ.ሂ የኖሩ ናቸው፡፡)
      ታላቅ የሐዲሥ ሊቅ እና ዓሊም ናቸው፡፡
“ፈትሑል ባሪ” የተሠኘው የሶሒሕ ቡኻሪ ማብራሪያ መጽሐፍ ከዝነኛ ድርሠቶቻቸው መካከል ይጠቀሳል፡፡
የመጽሐፉ ይዘት ፡- ሸሪዓዊ ድንጋጌዎችን የተመለከቱ ሐዲሦች የተካተቱበት ነው፡፡
 መጽሐፉ 1596 ሐዲሦችን ይዟል፡፡
መጽሐፉ እጅግ ጠቃሚ ሆኖ በመገኘቱ በተለያዩ ዑለሞች በርካታ ማብራሪያዎች ተሠርተዉለታል፡፡ ሱበለ ሰላም፣ ተውዲሕ አል-አሕካም፣ አል-ኢፍሃም፣ …የተወሰኑት ናቸው፡፡

ከዓመታት በፊት በትናንሽ ጥራዞች ተጀምሮ የነበረው ይህ መጽሐፍ በ2008/2009 በሁለት ቅፆች ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በነጃሺ ማተሚያ ቤት ታትሟል፡፡
ተርጓሚው አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ ሲሆኑ ከበቂ ማብራሪያ ጋር አዘጋጅተዉታል፡፡
አንደኛው ቅጽ ገፆች 506 ያሉት ሲሆን ሁለተኛው 508 ገፆች አሉት፡፡

ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ


https://t.me/NejashiPP


https://bit.ly/3r4948i