Get Mystery Box with random crypto!

፨ 'ወቁሉ ሊናስ ሑስነን' ይላል ቁርአናችን። ፨ 'ለሰዎች መልካምን ተናገሩ' ማለት ነው። ፨ ነቢ | ABX

፨ "ወቁሉ ሊናስ ሑስነን" ይላል ቁርአናችን።
፨ 'ለሰዎች መልካምን ተናገሩ' ማለት ነው።
፨ ነቢዩም 'በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ይናገር አልያም ዝም ይበል።' ይላሉ።
፨ ከአንደበታችን የሚወረወር መልካም ቃል የደከመን ያበረታል፣ የታመመን ይፈዉሳል።
፨ ዱንያ ላይ ያለ ሰው ሁሉ ቁስለኛ ነው፣ ለሰው የማያሳየው የተጎዳ ጎን አለው፣
፨ የተጎዳን አይዞህ በሉ፣ የቆሰለን አክሙ፣
፨ መናገር ባትችሉ እንኳን የመልካም ተናጋሪዎችን መልካም በማስተላለፍ በሌሎች አንደበት መልካምን ተናገሩ፣
፨ ቀኑን በብርቱ ትውሉ ዘንድ ማለዳ፣ ለሊቱን በተስፋ ታድሩ ዘንድ ምሽት ላይ አላህ ያስቻለኝን ያህል እናገራለሁ።
ጌታዬ የንግግር ጥበብን ያስተምረኝ ዘንድ እለምነዋለሁ።

መልካም ምሽት።


http://t.me/MuhammedSeidABX