Get Mystery Box with random crypto!

የጤናማ ቀልብ ምልክት *** ** ከቀልብ ጤንነት ምልክቶች መካከል ሰውዬው አንድ ዊርዱ ወይም | ABX

የጤናማ ቀልብ ምልክት
*** **

ቀልብ ጤንነት ምልቶች መካከል ሰውዬው አንድ ዊርዱ ወይም ከአምልኮ ተግባሩ ባመለጠው ጊዜ፣ ከዚያ አንድ ጥንቁቅ ሰው ገንዘቡ ባመለጠው ጥሩ ባመለጠው ጊዜ ከሚሰማው ሕመም የበለጠ ሕመም እርሱን በዚህ የተነሳ ማግኘቱ ነው፡፡ ልክ የተራበ ሰው ለምግብና ለውሃ እንደሚናፍቀው ሁሉ እርሱም ለአላህ ኺድሚያ ይናፍቃል፡፡ የሕያ ኢብን ሙዓዝ እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹እርሱ ያ አላህን በማገልገል የሚደሰት ሰው፣ ሁሉም ነገሮች እርሱን በማገልገል ይደሰታሉ፡፡ እርሱ ያ ዓይኑ በአላህ ላይ የረጋ ሰው፣ የያንዳንዱ ነገር ዓይኖች ወደርሱ በመመልከት ይረጋሉ፡፡››
የጤናም ቀልብ ባለቤትን የሚያሳስበው ነገር አንድ ብቻ ነው፣ ያም የአላህ ጉዳይ ነው፤ ማለትም ሁሌም በአላህ አምልኮና መታዘዝ ላይ መገኘት፡፡
ሌላው ባለቤቱ ከሰዎች መካከል ከዚያ ለገንዘቡ በብርቱ ንፉግ ከሆነው ሰው በላይ ጊዜው በከንቱ እንዳይባክንበት ሲበዛ ንፉግ መሆኑ ነው፡፡
ወደሶላቱ በሚገባበት ጊዜ የዱንያ ጭንቀቱና ሐሳቡ ሁሉ ይወገዳል። በርሷም ውስጥ ዕረፍትና እርካታን ያገኛል፡፡ ሶላት ለርሱ የዓይን ማረፊያው እና የቀልቡ ደስታ ናት፡፡
ጌታውን ከማውሳት አይቋረጥም ፡፡ እርሱን ከማገልገል ፈጽሞ አይደክምም፡፡ ከርሱ ውጭ ማንንም አይወዳጅም።
ሌላው ባለቤቱ ከሥራው በላይ ስለሥራው ትክክለኛነት ያለው ትኩረት የበለጠ ትልቅ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ በዚያ ውስጥ በኢኽላስ ላይ፣ ምክርን በመለገስ ላይ፣ መልዕክተኛውን በመከተል ላይ፣ በመልካምነት ላይ ጠንቃቃ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህም ጋር በዚያ ውስጥ ያለውን የአላህን ፀጋና የአላህን ሐቅ በመወጣቱ ረገድ ደግሞ ያለበትን ጉድለት በራሱ ላይ ይመሰክራል፡፡
 

ነፍስን ማጥራት
ትርጉም ፣ በአቡ አማን የሕያ
ከነጃሺ ማተሚያ ቤት
በቅርቡ ይታተማል - ኢንሻአላህ

https://t.me/NejashiPP

https://bit.ly/3r4948i