Get Mystery Box with random crypto!

ኢማም አል-ገዛሊ “ኢሕያእ ዑሉሚዲን” በተሠኘው መጽሐፋቸው ስለ ሀሜት ዓይነቶች ሲገልፁ እንዲህ ይላ | ABX

ኢማም አል-ገዛሊ “ኢሕያእ ዑሉሚዲን” በተሠኘው መጽሐፋቸው ስለ ሀሜት ዓይነቶች ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ፡-  

ከሀሜተኞች ሁሉ እጅግ ክፉዎቹ ለታይታ ብለው የሚያሙት ናቸው፡፡ እነሱን ዓላማቸዉን የሚያሳኩት ከሀሜት የታቀቡ ጨዋዎች በመምሰል ነው፡፡ ግና በዚህ አካሄዳቸው ሁለት መጥፎ ነገሮችን መያዛቸዉን አያስተዉሉም፡፡ ሀሜት እና ታይታን፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው እነርሱ ዘንድ በተወሳ ጊዜ “ባለሥልጣን ሥር በመሄድ ላልፈተነን አላህ ምስጋና ይገባው፡፡” ይላሉ፡፡ ወይም ደግሞ “እፍረተ ቢስ ከመሆን በአላህ እንጠበቃለን፤ አላህ ይጠብቀን፡፡” ይላሉ፡፡ ዓላማቸው የሌሎችን ነዉር ማሳወቅ ነው፡፡ በዱዓ እያስመሰሉ ሰዉን ያማሉ፡፡ ግና አላህ የዉስጣቸዉን መጥፎ ሀሳብ እና ዓላማ ያውቃል፡፡

መሳአል ኸይር

http://t.me/MuhammedSeidABX

የኢማሙ ሀሳቦች ጥልቅ ናቸው፡፡
በአላህ ፈቃድ እንቀጥላለን