Get Mystery Box with random crypto!

Injibara University

የቴሌግራም ቻናል አርማ injiuniversity — Injibara University I
የቴሌግራም ቻናል አርማ injiuniversity — Injibara University
የሰርጥ አድራሻ: @injiuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.73K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-01 15:38:50
የሀዘን መግለጫ

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ተከታታይ ፕሮግራም ማኔጅመንት ተማሪ የሆነው ተመስገን ሽቴ ባጋጠመው ህመም በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በተማሪ ተመስገን ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ እና ለወወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።
የካቲት 22/2015 ዓ.ም
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
2.9K views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 15:37:47
የባህላዊ መድሃኒት አዋቂዎችን በማጎልበት የህብረተሰብ ጤናን ለማሳደግ የስልጠና እና የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር መልካም አባተ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ከለየው የትኩረት መስክ አንዱ የሆነው የሀገር በቀል እውቀትን መለየት፣መሰነድ፣መረጃ ቋት ውስጥ ማስገባት፣ መጠበቅና ማልማት ነው።

ስልጠናውም የሀገር በቀል ዕውቀትንና የዕውቀቱን አዋቂዎችን በመለየት፣ዕውቀቱን በመመርመር እንዲጠበቁ በማድረግና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

የጥናቱ ባለቤትና አሰልጣኝ የሆኑት መ/ር ዬናስ ደረበ እንደገለጹት ስልጠናው በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የሚገኙ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች ተሳታፊ እነደሆኑ ገልጸው የሃገር በቀል መድሃኒትን በተመለከተ ከሥራ አጋሮቻቸው ጋር ሆነው ያካሄዱት ምርምር መሆኑን ጠቅሰው በተገኘው ውጤት መሰረትም ባህላዊ ዕውቀትን ከዘመናዊው ጋር ለማዋሀድ የሚያግዝ ዓላማ ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና እየሰጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ስልጠናውን የሚሰጡት መ/ር አማረ ፋሲል፣ ዮናስ ደረበ እና በቀለ ገብረአማኑኤል ናቸው፡፡

የካቲት 21/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
2.7K views12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 20:23:39
ማስታወቂያ በትርፍ ሰዓት መስራት ለምትፈልጉ በሙሉ፦
1.6K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 06:13:25
ማስታወቂያ
ለተከታታይ ትምህርት ለፈላጊዎች በሙሉ፦
1.5K views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 20:58:32
የጥሪ ማስታወቂያ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች፦

በ2015 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ቀን ከታች በተገለጸው መሰረት የካቲት 27 እና 28 መሆኑን እናሳውቃለን!
1.4K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 20:48:29
በማህበራዊ እና ሰብዓዊ ሳይንስ ኮሌጅ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመክፈት የሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ (validation workshop) አካሄደ፡፡

ኮሌጁ (PhD in TEFL) እና በሁለተኛ ዲግሪ (MA in Comparative Literature and Cultural Studies) ለማስጀመር የሥርዓተ-ትምህርት ቅኝት አካሂዷል፡፡

በሥርዓተ ትምህርት ግምገማው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነባር በሆኑት ደብረ ማርቆስና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሚገኝ በመሆኑ ለእነዚህና ለሌሎችም በቀጣይ ለሚከፈቱ አዳዲስ ፕሮግራሞች ተጨማሪና አስፈላጊ የሆነውን የሰው ኃይል ግብዓት ከእነዚህ ዓይነት ነባር ተቋማት በመጠቀም ለተሻለ የትምህርት ጥራት መረጋገጥ ብሎም ተቋሙን በተማሪዎች ዘንድ ይበልጥ ተመራጭ ለማድረግ ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም በቀጣይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ተቋማት የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸውን ምሁራንን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በመሳብ ሌሎች ተጨማሪ ፕሮግራሞችን ለማስፋፋት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid04rYnwEHCJhUXhbij47YzknCKMfdWC1ibJuoYrD2pphSPYtpkVtgG7We3XgMby7QJl/?app=fbl
1.3K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 13:59:20
የጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህራንና ተማሪዎች የአካባቢ ጥበቃ ክለብ (Environmental Protection Club) አቋቋሙ።

ክለቡ መቋቋሙ ዩኒቨርሲቲው የሚታወቅበት ጽዱ እና አረንጓዴነቱን ለመጠበቅ የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ እና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል ኃላፊ አበበ አናጋው (ዶ/ር) እንደገለጹት ትምህርት ክፍሉ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በግቢው ውስጥ የችግኝ የማፍላት ስራ የጀመረ እና ትልቅ እገዛ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው ዕለት ደግሞ የUrban and Regional Development Planning የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ጋር በመሆን የአካባቢ ጥበቃ ከለብ በይፋ መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid06HDeYUR5tMiK9v8UcUtyexjh3YhW8s931De5UmZNMArt84vf4RPsN8Ds8cEJYbx4l/?app=fbl
1.6K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 13:59:17
1.5K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 13:56:01
በምህንድስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ውስጥ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሁለተኛ ድግሪን ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ግምገማ (External Workshop) ተካሄደ::
---------------------
በግምገማው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር እሱባለው ስንቴ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪን ለመጀመር የሚያስችሉ ካሪኩለምን ጨምሮ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ጠቅሰው ተጨማሪ ግብዓቶችን ለማግኘት የውጭ ግምገማ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ ሥራ ለተሳተፉ ገምጋሚዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የግምገማ መድረኩን መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት የምህንድስና እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የድኅረ ምረቃ፣ ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ዲን የሆኑት ይርጋ ያየህ(ዶ/ር) ሲሆኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በሁለተኛ ዲግሪ መሰጠቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እድገት በተለያዩ ዘርፎች (በትምህርት፣ በግብርና፣ በጤና እና ህክምና፣ በንግድ ዘርፍ፣ በስራ ፈጠራ በመገናኛ ብዙኃን እና የቴሌኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም በሌሎች አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች) ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ ከሌሎች ሴክተሮች ጋር በማጣመር የተለያዩ ሴክተሮችን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል አንድ ግብዓት መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከወሎ ዩኒቨርሲቲ አለሙ ጆርጊ (ዶ/ር) እና ክባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አብዱከሪም መሀመድ (ዶ/ር) በቨርቹዋል ገምጋሚነት የተሳተፉ ሲሆን በተነሱት ሃሳብ እና አስተያየቶች ላይ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግምገማው ወርክሾፕ ተጠናቋል፡፡
የካቲት 7/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
1.4K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 13:55:16
የልማት ተነሺ አርሶአደሮች የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡
////////////////
5ኛ ዓመት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የሰላም ኮንፈረንስ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡
በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) የሰላም ኮንፈረንሱ ዓላማ የተቋሙን እና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ጤናማ ግንኙነትን ከማጠናከር ባሻገር አካባቢውን የሰላም ቀጠና በማድረግ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ያለምንም ስጋት እውቀት ጨብጠው እንዲወጡ ለማድረግ ማኅበረሰቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02CZDTPygrYpbHajYAQWxLepLhKBu3F4vnuzMAKLPrf2hNEFARCr1BnL79h4uvJPrTl/?app=fbl
1.3K views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ