Get Mystery Box with random crypto!

Injibara University

የቴሌግራም ቻናል አርማ injiuniversity — Injibara University I
የቴሌግራም ቻናል አርማ injiuniversity — Injibara University
የሰርጥ አድራሻ: @injiuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.73K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-12-30 17:45:48

1.9K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 17:06:28
ለተከታታይ አራት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቀቀ፡፡
///////////////
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከታኅሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሰላም ተጠናቋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የፈተና ፕሮግራም በህመም፣ በወሊድ እና መሰል ምክንያቶች ፈተናውን መውሰድ ላልቻሉ ከአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር፣ ከምዕራብ ጎጃም እና ከመተከል ዞን ከተመደቡ 251 ተማሪዎች ውስጥ 152 ያክሉ ፈተናው በአግባቡ ወስደው ወደየመጡበት ተሸኝተዋል፡፡

ታኅሳስ 21/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
1.8K views14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 16:09:24
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከእንጅባራ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የስፖንሰርሽፕ ስምምነት ተፈራረመ።
በስምምነቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና የእግር ኳስ ክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) የስፖርቱ ዘርፍ የዓለምን ህዝብ በአንድ የሚሰበስብ የሰላም ምልክትና ሀገርን የሚገነባ የኢኮኖሚ ዘርፍ በመሆኑ የከተማው የእግር ኳስ ክለብ የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ ላይ የተመሰረተ ስምምነት ነው ብለዋል። አያይዘውም ክለቡ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ህዝባዊ መሰረት ማስያዝ ዋናው ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት አእምሮ ታደሰ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍልን ከፍቶ ሲያስተምር ትኩረቱ ተማሪዎችን አስተምሮ ማስመረቅ ላይ ብቻ ሳይሆን በስፖርቱ ዘርፍ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሙያዊ የሆነ ድጋፍ መስጠት መሆኑን ጠቁመው ዩኒቨርሲቲው እንደተቋም ክለቡን በመደገፍ ሙያዊ ኃላፊነቱን ይወጣል ብለዋል፡፡

የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን (ዶ/ር) በበኩላቸው እግር ኳስና ሌሎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ለወጣቱ ማህበረሰብ አስፈላጊ በመሆናቸው ክለቡን መደገፍ አስፈላጊ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ እና የክለቡ ም/ፕሬዝደንት አቶ ግዛቸው ጥላሁን ክለቡ ሥራ ሲጀምር በርካታ ተግዳሮቶች እንዳጋጠሟቸው ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲው ከአሁን በፊት ባደረገው ድጋፍ በርካታ ችግሮች የተቀረፉለት ሲሆን በዛሬው እለት የተደረገው ስምምነት የተጠናከረ ክለብን ለመመስረት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በስምምነቱ የክለቡ አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው ስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና መምህራን ተገኝተዋል።

ታኅሳስ 18/2015 ዓ.ም
2.0K views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 19:11:07
በሁለተኛ ዙር የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ገለፃ(Orientation) ተደረገላቸው፡፡
//////////////
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ ከ250 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በፈተና ህግና ደንቦች ላይ ያተኮረ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሀብታሙ ዘገዬ(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ከአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እና ከምዕራብ ጎጃም ዞኖች እንዲሁም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከ250 በላይ የሁለተኛ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበሉን ገልጸዋል፡፡ በሁለተኛ ዙር ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በመጀመሪያው ዙር በህመም፣ በወሊድ እና መሰል ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩ ሲሆኑ በዛሬው እለት አጠቃላይ ገለጻ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል፡፡

ገለጻውን የሰጡት በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የጉድኝት ኃላፊ ወ/ሮ እናኑ በዛብህ ሲሆኑ ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በቆይታቸው መከተል ስላለባቸው መብትና ግዴታዎች፣ በፈተና ወቅት የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮች፣ የፈተና ደንብ ጥሰት (ኩረጃ)፣ የፈተና ወረቀት ምን መሆን እንዳለበት፤ በአጠቃላይ የፈተና ሥነ ምግባር ምን መምሰል አለበት በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ አተኩረው አብራርተዋል፡፡
ሁለተኛው ዙር የ2014/15 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ከነገ ማክሰኞ ታህሳስ 18 /2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናትየሚሰጥ ይሆናል፡፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈታኝ ተማሪዎች መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል!
ታህሳስ17/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
2.3K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 16:03:59
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአማራ ክልል ስፖርት እንዲስፋፋ እና እንዲጠናከር በገንዘብ፣ በእውቀት እና በጉልበት ላደረገው አስተዋፅኦ የአማራ ክልል ስፖርት ም/ቤት ይህን የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡

ታኅሳስ 17/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
2.3K views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 19:06:57

2.5K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 18:54:00
በሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለ136 የግቢ ውበት እና አትክልት ልማት ሠራተኞች የሥነ ምግባር ምንነት፣ የሥራ ሥነ ምግባር፣ የዩኒቨርሲቲው የአመራር አካላትና ሠራተኞች የሥነ ምግባር መመሪያ፣ እንዲሁም የሙስና ምንነትና የሚያስከትላቸው ጉዳቶች በሚሉ ርእሶች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና ከፍ በማድረግ የሙስና ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት አስቀድሞ ለመከላከል እንደሀገር የተያዘው የሙስና መከላከል ስትራቴጂ አካል መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደሳለው ጌታሁን አስረድተዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የመከታተያ ክፍሉ ዳይሬክተር አቶ ደሳለው ጌታሁን እና የስነ ምግባር ግንባታ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ፈቃዴ ተሾመ ሲሆኑ እንዲህ አይነት ስልጠናዎች የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ግንዛቤ ከፍ በማድረግ ሁሉም አካል ሙስናን ከመከላከል አንጻር ድርሻውን እንዲወጣ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርጉ በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

ታኅሳስ 14/2014 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
2.4K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 18:53:02
የልማት ተነሽ አርሶ-አደሮች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የልማት ሥራ አከናወኑ።

ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የልማት ተነሽ የሆኑ አርሶ-አደሮች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ባላቸው መልካም የሆነ ግንኙነት ዩኒቨርሲቲው ለሚያረባቸው የወተት ላሞች ምግብነት የሚሆን በግቢው ውስጥ የሚገኘውን ሳር በጋራ የአጨዳ ስራ አከናውነዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው እነዚህን የወተት ላሞች ከመግዛቱ በፊት ይህንን ሳር ሙሉ በሙሉ ለማህበረሰቡ ሲሰጥ እንደነበር የገለፁት የማህበረሰቡ ተወካይና የልማት ሥራው አስተባባሪ አቶ አደራው ታምር አሁንም ከወተት ላሞቹ ፍጆታ በላይ የሆነውን ሳር ማህበረሰቡ የሚወስድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ አደራው አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ከዚህ መልካም ተግባር በተጨማሪ እነዚህ የልማት ተነሽ አርሶ-አደሮች ለሚገለገሉባቸው ሁለት የሃይማኖት ተቋማት የመብራት አገልግሎት እንዲሁም እነዚህን ማህበረሰቦች በልዩ ልዩ ሥራዎች በማደራጀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የማድረግ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ይህ የዩኒቨርሲቲውና የአርሶ-አደሮች የሁለትዮሽ መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ ለወደፊት እንዲቀጥል በማሰብ በዓመት አንድ ጊዜ ጥር ወር ውስጥ “ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የልማት ተነሽ አርሶ-አደሮች የሰላም ኮንፈረንስ” በሚል መሪ ሀሳብ ዓመታዊ የውይይትና የምክክር መድረክ በማህበረሰቡ አዘጋጅነት ይካሄዳል፡፡ በዚህ የሰላም ኮንፈረንስ በተቋሙና በማህበረሰቡ መካከል በዓመት ውስጥ የተከናወኑ አበይት ተግባራት ይዳሰሱበታል፤ ለመልካም ተሞክሮዎችና ክንውኖችም በማህበረሰቡ በኩል ዕውቅና ይሰጣል፡፡
መልካም ግንኙነታችን ከበርካታ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቀፍ ዕድሎች ተጠቃሚ ስላደረገን ለወደፊቱ ይህንን መልካም ተግባር አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የልማቱ ተሳታፊ አርሶ-አደሮች ሀሳባቸውን ገልፀውልናል፡፡
ታኅሳስ 14/2014 ዓ.ም
2.0K views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 16:35:21
እንኳን ደስ አላችሁ!
---------
"ጥበበ ዛጉዌ" ሳምንታዊ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ቅዳሜ ታኅሳስ 15/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1:30 ጀምሮ ይተላለፋል።
2.2K views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 11:13:40
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
699 views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ