Get Mystery Box with random crypto!

በሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሥነ | Injibara University

በሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለ136 የግቢ ውበት እና አትክልት ልማት ሠራተኞች የሥነ ምግባር ምንነት፣ የሥራ ሥነ ምግባር፣ የዩኒቨርሲቲው የአመራር አካላትና ሠራተኞች የሥነ ምግባር መመሪያ፣ እንዲሁም የሙስና ምንነትና የሚያስከትላቸው ጉዳቶች በሚሉ ርእሶች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና ከፍ በማድረግ የሙስና ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት አስቀድሞ ለመከላከል እንደሀገር የተያዘው የሙስና መከላከል ስትራቴጂ አካል መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደሳለው ጌታሁን አስረድተዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የመከታተያ ክፍሉ ዳይሬክተር አቶ ደሳለው ጌታሁን እና የስነ ምግባር ግንባታ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ፈቃዴ ተሾመ ሲሆኑ እንዲህ አይነት ስልጠናዎች የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ግንዛቤ ከፍ በማድረግ ሁሉም አካል ሙስናን ከመከላከል አንጻር ድርሻውን እንዲወጣ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርጉ በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

ታኅሳስ 14/2014 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ