Get Mystery Box with random crypto!

የልማት ተነሽ አርሶ-አደሮች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የልማት ሥራ አከናወኑ። ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ | Injibara University

የልማት ተነሽ አርሶ-አደሮች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የልማት ሥራ አከናወኑ።

ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የልማት ተነሽ የሆኑ አርሶ-አደሮች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ባላቸው መልካም የሆነ ግንኙነት ዩኒቨርሲቲው ለሚያረባቸው የወተት ላሞች ምግብነት የሚሆን በግቢው ውስጥ የሚገኘውን ሳር በጋራ የአጨዳ ስራ አከናውነዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው እነዚህን የወተት ላሞች ከመግዛቱ በፊት ይህንን ሳር ሙሉ በሙሉ ለማህበረሰቡ ሲሰጥ እንደነበር የገለፁት የማህበረሰቡ ተወካይና የልማት ሥራው አስተባባሪ አቶ አደራው ታምር አሁንም ከወተት ላሞቹ ፍጆታ በላይ የሆነውን ሳር ማህበረሰቡ የሚወስድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ አደራው አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ከዚህ መልካም ተግባር በተጨማሪ እነዚህ የልማት ተነሽ አርሶ-አደሮች ለሚገለገሉባቸው ሁለት የሃይማኖት ተቋማት የመብራት አገልግሎት እንዲሁም እነዚህን ማህበረሰቦች በልዩ ልዩ ሥራዎች በማደራጀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የማድረግ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ይህ የዩኒቨርሲቲውና የአርሶ-አደሮች የሁለትዮሽ መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ ለወደፊት እንዲቀጥል በማሰብ በዓመት አንድ ጊዜ ጥር ወር ውስጥ “ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የልማት ተነሽ አርሶ-አደሮች የሰላም ኮንፈረንስ” በሚል መሪ ሀሳብ ዓመታዊ የውይይትና የምክክር መድረክ በማህበረሰቡ አዘጋጅነት ይካሄዳል፡፡ በዚህ የሰላም ኮንፈረንስ በተቋሙና በማህበረሰቡ መካከል በዓመት ውስጥ የተከናወኑ አበይት ተግባራት ይዳሰሱበታል፤ ለመልካም ተሞክሮዎችና ክንውኖችም በማህበረሰቡ በኩል ዕውቅና ይሰጣል፡፡
መልካም ግንኙነታችን ከበርካታ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቀፍ ዕድሎች ተጠቃሚ ስላደረገን ለወደፊቱ ይህንን መልካም ተግባር አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የልማቱ ተሳታፊ አርሶ-አደሮች ሀሳባቸውን ገልፀውልናል፡፡
ታኅሳስ 14/2014 ዓ.ም