Get Mystery Box with random crypto!

Injibara University

የቴሌግራም ቻናል አርማ injiuniversity — Injibara University I
የቴሌግራም ቻናል አርማ injiuniversity — Injibara University
የሰርጥ አድራሻ: @injiuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.73K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-13 20:24:49
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲውን በማስተዋወቅ እና  የሥራ ጉብኝት በማደርግ ላይ ይገኛሉ።

ከሚያዚያ 29/2015 ዓ.ም  ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በአሜሪካ የሥራ ጉብኝት የሚያደርጉት ፕሬዝደንቱ ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት  የሚያከናውናቸውን ተግባራት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በመገኘት ለኢምባሲው የሥራ ኃላፊዎች ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን በአሜሪካ ካሉት ተቋማት ጋር በማገናኘት እና በማስተሳሰር የዩኒቨርሲቲው  ዓለምአቀፍ ትስስር እንዲጠናከር አምባሲው  እንዲያግዝ ለኤምባሲው ጥያቄ አቅርበዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ኢምባሲ አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ  እና ምክትል አምባሳደር ዘላለም ብርሃን እንዲሁም የዲያስፓራ ጉዳዮች ኃላፊ  አቶ አቻሜለህ ሙላት  እና የፐብሊህ ዲፕሎሚሲ ኃላፊ አቶ ነጋልኝ መኳንንት  እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ ያለውን ስራ አድንቀው  ኢምባሲው የዲያስፓራ አባላትን በማስተባበር ጭምር  እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች  ጋር  ለማስተሳሰር  አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። 

ፕሬዝደንቱ በሥራ ጉብኝታቸው ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችንም በማግኘት ትስስር ለመፋጠር  እና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነትን ለማዳበር የማስተዋወቅ ሥራ እየሠሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ግንቦት 5/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
2.3K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 16:50:09
ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ (Exit Exam) ሞዴል ፈተና መሰጠት ተጀመረ።

ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ሞዴል ፈተና መስጠት የተጀመረ ሲሆን የሞዴል ፈተናው ለዋናው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በቂ የሆነ ዝግጅት እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሞዴል ፈተናው አይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት እና በምንድህስና እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ አስተባባሪነት ከዛሬ ሚያዚያ 25 እስከ 30/2015 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ዋናውን መውጫ ፈተና ያለምንም ችግር እንዲፈተኑ የሚያስችላቸው መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ሀብታሙ ዘገዬ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የፈተና ሂደቱ ተመራቂ ተማሪ ባላቸው ኮሌጆች ሥር በሚገኙ ትምህርት ክፍሎች አማካኝነት ፈተናው ከተዘጋጀ በኋላ ወደ ኮምፒውተር ሲስተም ገብቶ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ቀደም ሲል የመውጫ ፈተናን በአግባቡ እንዲፈተኑ ለማድረግ ስልጠናዎች እና የተለያዩ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች መሰራታቸውን አስታውሰዋል፡፡

የሞዴል ፈተናው በቀጣይ ጊዚያት በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ተዘጋጅቶ ከሚሰጠው ከዋናው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ቀድሞ መሰጠት መቻሉ በፈተናው የአሰራር ሂደት ዙሪያ በቂ ልምምድ እንዲኖረን ከማስቻሉም በላይ ተሸለ የሥነ-ልቦናና የክህሎት ዝግጅት እንዲኖረን ያደርጋል ሲሉ የሞዴል ፈተናውን እየወሰዱ የሚገኙ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡
2.9K views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 16:49:32
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2015ዓ.ም የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የመንግስት መስሪያቤት ሰራተኞች የእግር ኳስ ውድድር የዋንጫ ባለቤት ሆነ፡፡

ከሚያዚያ 17-24/2015 ዓ.ም በአገው ግምጃ ቤት ከተማ ሲካሄድ የነበረው የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ስፖርት ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ዩኒቨርሲቲው በእግር ኳስ ጨዋታ አንከሻ ወረዳን በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በርካታ የስፖርት ቤተሠቦች በተገኙበት እና በአገው ግምጃቤት ሁለገብ ስታዲየም በተካሄደው በእንጅባራ ዩንቨርስቲና የአንከሻ ወረዳ የእግር ኳስ ቡድኖች የዋንጫ ጨዋታ ከፍተኛ ፋክክር ተደርጎበት እንጅባራ ዩንቨርስቲ የእግር ኳስ ቡድን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ጨዋታው በጥላሁን የኔው ቡድን መሪነት ሲካሄድ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ተጫዋች እና አምበል አዲሱ ሙሉቀን የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች እንዲሁም የቡድኑ አሰልጣኝ መምህር አማረ መብራት የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የቮሊቮል የፍጻሜ ጨዋታ 2ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሙሉቀን ማሩ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተሸላሚ ሆኗል። በተመሳሳይ በጠረጴዛ ኳስ ጨዋታ ደግሞ በይበልጣል ጥላሁን አማካኝነት 2ኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

በውጤቱ መሰረት ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ለሚደረው የአማራ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ስፖርት ውድድር ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
2.7K views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 11:51:39
የሀዘን መግለጫ
------
ተማሪ ተሾመ በሪሁን መኩሪያው የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዓመት የህግ ተማሪ የነበረ ሲሆን ቤተሰቦቹ ጋር በሄደበት ባደረበት ህመም ምክንያት ሚያዚያ 21/2015 ዓ.ም ህይወቱ አልፏል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በተማሪ ተሾመ በሪሁን ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።
3.6K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 07:59:11
ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በሥነ ልቡና ዝግጅት (Psychological readiness) ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ በሚያደርጉት ዝግጅት በራስ የመተማመን ብቃታቸውን የሚያጎለብት መሆኑ ተገልጿል።

በዩኒቨርሲቲው ሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የተዘጋጀው ስልጠና ዋና ዓላማው የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በቂ የሆነ የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በማስቻል በራስ የመተማመን ባህላቸውን ከፍ በማድረግ ፈተናውን ውጤታማ በሆነ መንገድ መስራት እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን የትምህርት ክፍል ኃላፊው መምህር ሙላት አራጋው አስረድተዋል።

በፈተና ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ አሉታዊ ስሜቶችን ቀድሞ መከላከል፣ የጊዜ አጠቃቀም፣ ሳይንሳዊ የአጠናን ስልት፣ እንዲሁም ፈተና ወለድ ጭንቀትን መቀነሻ መንገዶች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ የሚሉ ርዕሰጉዳዮች በስልጠናው ተዳሰዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ሳይኮሎጅ መምህራን የሆኑት ሙላት አራጋው፣ ሙሉዓለም አለማየሁ፣ ጥላሁን ፈንቴ(ረ/ፕ)፣ ፈንታሁን እንዳሌ፣ አበባው የኔነህ፣ አድምጠው አበበ፣ እርቂሁን አለምነህ እና ሽመልስ አያልነህ ሲሆኑ በሁሉም ኮሌጆች ስር የሚገኙ የመውጫ ፈተናውን ለመወሰድ በዝግጅት ላይ ያሉ ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
ለተከታታይ ሁለት ቀናት የተሰጠው ስልጠና በቀጣይ ቅዳሜ እና እሁድ እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ሚያዚያ 22/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
3.7K views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 15:43:01
የተሻሻለ የድንች ዘር ብዜት የምርምር ሙከራ ተካሄደ።
//////////
የተሻሻለ የድንች ዘር ብዜት የምርምር ሙከራ ሥራው የተሻለ ምርታማነት ያላቸው የድንች ዝርያዎችን በአካባቢው በማላመድ ለማህበረሰቡ ተደራሽ የማድረግ እሳቤ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ሚያዚያ 19/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) የምርምር ሥራውን በቦታው ተገኝተው በጎበኙበት ወቅት የምርምር ሙከራ ሂደቱን በየወቅቱ በመከታተልና በመገምገም ውጤታማነቱን የማረጋገጥ ተግባሩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የምርምሩን የሙከራ ተግባር እያካሄዱ የሚገኙት የዕፅዋት ሳይንስ መምህር አቶ ዘላለም ካሳ እና የሆርቲካልቸር መምህር አቶ አዲሱ ሙሉቀን ሲሆኑ “ጉደኔ” እና “በለጠ” በተባሉ ሁለት የድንች ዝርያዎች ላይ እየተካሄደ የሚገኘው የምርምር ሥራ የአርሶ-አደሩን የዘር ፍጆታ ለመቀነስና የዘር ብዜትን በመጨመር የተሻለ ምርትን ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም እነዚህን ሁለት የተሻሻሉ የድንች ዝርያዎችን አንዱን ለሁለት በመቁረጥ የተሻለ ምርትን ለማግኘት እና ለዘር ብዜት ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የምርምር የሙከራ ጣቢያ በመትከል እና ሂደቱን እስከመጨረሻው በመከታተል ሊያስገኙ የሚችሉትን የተሻለ የንፅፅር ውጤት ለአካባቢው ማህበረሰብ ተደራሽ የማድረግ ሥራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0ieygj6p9tkF6wDN5kvSxmRGTCbYbH9HSiGeWTeaZLjsehPvJD7iRBxdvzXb3S4qfl/?app=fbl
2.0K views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 21:56:53
ለትርፍ ሰዓት ሥራ አመልካቾች በሙሉ
1.1K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 19:11:38
The Ethiopian Herald
1.5K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 21:37:27
1444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከብሯል።

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ተማሪዎች 1444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን በጋራ አክብረዋል።

የኢድ አልፈጥርን በዓል በማስመልከት የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በላይ ዘለቀ (ዶ/ር) እና ሌሎችም አመራሮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የተማሪ ህብረት አባላት እና በጸጥታ ሥራ ላይ ተሠማርተው የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላት በዓሉን በጋራ አክብረዋል።
ኢድ ሙባረክ!

ሚያዚያ 13/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
2.3K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:59:16
እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ይመኛል።

ኢድ ሙባረክ!

ለቴሌግራም-https://t.me/injiuniversity
ለኢንስታግራም -https://www.instagram.com/injibara12
ለዌብ ሳይት- https://www.inu.edu.et/
ለፌስ ቡክ ገፃችን -https://www.facebook. Com/injibaruni
ለኢሜይል- injibarau@gmail.com
ለInstitution Email -injibarauniversity@inu.edu.et
ለትዊተር- Twitter (https://twitter.com/injibara_Inu/)
በተጨማሪም የዩቱዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉን!
https://www.youtube.com/c/injibarauniversity
Explore Your Creative Potential
3.4K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ