Get Mystery Box with random crypto!

በሁለተኛ ዙር የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎ | Injibara University

በሁለተኛ ዙር የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ገለፃ(Orientation) ተደረገላቸው፡፡
//////////////
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ ከ250 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በፈተና ህግና ደንቦች ላይ ያተኮረ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሀብታሙ ዘገዬ(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ከአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እና ከምዕራብ ጎጃም ዞኖች እንዲሁም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከ250 በላይ የሁለተኛ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበሉን ገልጸዋል፡፡ በሁለተኛ ዙር ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በመጀመሪያው ዙር በህመም፣ በወሊድ እና መሰል ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩ ሲሆኑ በዛሬው እለት አጠቃላይ ገለጻ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል፡፡

ገለጻውን የሰጡት በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የጉድኝት ኃላፊ ወ/ሮ እናኑ በዛብህ ሲሆኑ ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በቆይታቸው መከተል ስላለባቸው መብትና ግዴታዎች፣ በፈተና ወቅት የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮች፣ የፈተና ደንብ ጥሰት (ኩረጃ)፣ የፈተና ወረቀት ምን መሆን እንዳለበት፤ በአጠቃላይ የፈተና ሥነ ምግባር ምን መምሰል አለበት በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ አተኩረው አብራርተዋል፡፡
ሁለተኛው ዙር የ2014/15 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ከነገ ማክሰኞ ታህሳስ 18 /2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናትየሚሰጥ ይሆናል፡፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈታኝ ተማሪዎች መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል!
ታህሳስ17/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ