Get Mystery Box with random crypto!

በምህንድስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ውስጥ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሁለተኛ ድግሪን ለመክፈት የሚያስችል የ | Injibara University

በምህንድስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ውስጥ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሁለተኛ ድግሪን ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ግምገማ (External Workshop) ተካሄደ::
---------------------
በግምገማው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር እሱባለው ስንቴ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪን ለመጀመር የሚያስችሉ ካሪኩለምን ጨምሮ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ጠቅሰው ተጨማሪ ግብዓቶችን ለማግኘት የውጭ ግምገማ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ ሥራ ለተሳተፉ ገምጋሚዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የግምገማ መድረኩን መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት የምህንድስና እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የድኅረ ምረቃ፣ ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ዲን የሆኑት ይርጋ ያየህ(ዶ/ር) ሲሆኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በሁለተኛ ዲግሪ መሰጠቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እድገት በተለያዩ ዘርፎች (በትምህርት፣ በግብርና፣ በጤና እና ህክምና፣ በንግድ ዘርፍ፣ በስራ ፈጠራ በመገናኛ ብዙኃን እና የቴሌኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም በሌሎች አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች) ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ ከሌሎች ሴክተሮች ጋር በማጣመር የተለያዩ ሴክተሮችን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል አንድ ግብዓት መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከወሎ ዩኒቨርሲቲ አለሙ ጆርጊ (ዶ/ር) እና ክባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አብዱከሪም መሀመድ (ዶ/ር) በቨርቹዋል ገምጋሚነት የተሳተፉ ሲሆን በተነሱት ሃሳብ እና አስተያየቶች ላይ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግምገማው ወርክሾፕ ተጠናቋል፡፡
የካቲት 7/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ