Get Mystery Box with random crypto!

በማህበራዊ እና ሰብዓዊ ሳይንስ ኮሌጅ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመክፈት የሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ (v | Injibara University

በማህበራዊ እና ሰብዓዊ ሳይንስ ኮሌጅ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመክፈት የሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ (validation workshop) አካሄደ፡፡

ኮሌጁ (PhD in TEFL) እና በሁለተኛ ዲግሪ (MA in Comparative Literature and Cultural Studies) ለማስጀመር የሥርዓተ-ትምህርት ቅኝት አካሂዷል፡፡

በሥርዓተ ትምህርት ግምገማው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነባር በሆኑት ደብረ ማርቆስና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሚገኝ በመሆኑ ለእነዚህና ለሌሎችም በቀጣይ ለሚከፈቱ አዳዲስ ፕሮግራሞች ተጨማሪና አስፈላጊ የሆነውን የሰው ኃይል ግብዓት ከእነዚህ ዓይነት ነባር ተቋማት በመጠቀም ለተሻለ የትምህርት ጥራት መረጋገጥ ብሎም ተቋሙን በተማሪዎች ዘንድ ይበልጥ ተመራጭ ለማድረግ ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም በቀጣይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ተቋማት የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸውን ምሁራንን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በመሳብ ሌሎች ተጨማሪ ፕሮግራሞችን ለማስፋፋት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid04rYnwEHCJhUXhbij47YzknCKMfdWC1ibJuoYrD2pphSPYtpkVtgG7We3XgMby7QJl/?app=fbl