Get Mystery Box with random crypto!

የባህላዊ መድሃኒት አዋቂዎችን በማጎልበት የህብረተሰብ ጤናን ለማሳደግ የስልጠና እና የምክክር መድ | Injibara University

የባህላዊ መድሃኒት አዋቂዎችን በማጎልበት የህብረተሰብ ጤናን ለማሳደግ የስልጠና እና የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር መልካም አባተ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ከለየው የትኩረት መስክ አንዱ የሆነው የሀገር በቀል እውቀትን መለየት፣መሰነድ፣መረጃ ቋት ውስጥ ማስገባት፣ መጠበቅና ማልማት ነው።

ስልጠናውም የሀገር በቀል ዕውቀትንና የዕውቀቱን አዋቂዎችን በመለየት፣ዕውቀቱን በመመርመር እንዲጠበቁ በማድረግና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

የጥናቱ ባለቤትና አሰልጣኝ የሆኑት መ/ር ዬናስ ደረበ እንደገለጹት ስልጠናው በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የሚገኙ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች ተሳታፊ እነደሆኑ ገልጸው የሃገር በቀል መድሃኒትን በተመለከተ ከሥራ አጋሮቻቸው ጋር ሆነው ያካሄዱት ምርምር መሆኑን ጠቅሰው በተገኘው ውጤት መሰረትም ባህላዊ ዕውቀትን ከዘመናዊው ጋር ለማዋሀድ የሚያግዝ ዓላማ ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና እየሰጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ስልጠናውን የሚሰጡት መ/ር አማረ ፋሲል፣ ዮናስ ደረበ እና በቀለ ገብረአማኑኤል ናቸው፡፡

የካቲት 21/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ