Get Mystery Box with random crypto!

አትሮኖስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የሰርጥ አድራሻ: @atronosee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 159.61K
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።
Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-16 17:29:43 አወጣሁልሽ...እና ሮሪ ሁሉ ነገር እንደዛ ነው የሆነው።"አለና የመጨረሻውን የሲጋራ ቁራጭ መጠጠና ጫፍን  ወለሉ ላይ በመጣል በእግሩ በማሸት እሳቱን አጠፋው።
"እና እኔስ ብጠፍ...ልክ እንደፍቅረኛህ የምትጠልቀው የማታ  ፀሀይ ብሆንስ?"ስትል ጠየቀችው።
"በፍፁም እንደዛ አይሆንም።  አንቺ  በሰማይ ላይ ዘወትር የምታንፀባርቂው ፀሀይ ነሽ።ተመልከች ገና 21 አመትሽ ነው።በጣም ስኬታማና ታዋቂ ድምፃዊ ነሽ።በዚህ ዕድሜሽ በርካት ሽልማቶችን የግልሽ አድርገሻል።ግን ይሄ በቂ አይደለም አለማቀፍ ብርሀን እንድትሆኚ ነው የምፈልገው።ከዚህ መቶ ጊዜ እጥፍ እንድታንፀባርቂ.."
"አጎቴ እኔ ግን ውስጤ በጨለማ ድቅድቅ ተውጦ የአለም ብርሀን መሆን ፈልጋለሁ እያልኩ እራሴን ማታለል ነው የሠለቸኝ ...እኔ ማንም የማያውቀኝ ተራ ግን ደግሞ ደስተኛ ሴት መሆን ነበር የምፈልገው።"
"እንደዛ ከሆነ ከእናትሽ ሞት ጋር የተያያዘ ህመምሽን ታክሞ ለመዳን ሞክሪ ፣የተሠበርሽበት ቦታ ፈራርሰሽ አትቅሪ "
"አንተ ከአሮራ ሞት ጋር የተያያዘውን ቁስልህን መርሳት ችለኸል? እኔስ የእናቴ ሞት ገና አራት አመት አልሆነውም አንተ ግን 15 አመት ሙሉ እራስህን ማከም አልቻልክም..ዛሬም ቁስልህ አዲስ ነው።"
ምን ታደርጊዎለሽ... አንዳንድ ቁስሎችን ጊዜ በቀላሉ አይፈውሳቸውም...አንቺ ግን ማድረግ ያለብሽ ቢያንስ ከእኔ ከእብድ አጎትሽ  የከሸፈ ህይወት መማር ነው... አሁን መጠጥ አማረኝ "ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ።
"አጎቴ ደግሞ...እዚሁ ምትፈልገውን መጠጥ ያምጡልህ "
"አይ የዚህ ቤት መጠጥ ውስኪ.. ቢራ ምናምን ነው ..እኔ ምፈልገው ካቲካላ ነው።"አላት።

.

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
7.6K views◔͜͡◔ A ◔͜͡◔, 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-16 17:29:43 አሮሯ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _አንድ
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

አሮራ  ውብ ነች ከማለት ይልቅ ጣኦት ትመስላለች ማለት ይበልጥ ይገልፃታል።ብዙውን ጊዜ የውበት መስፈሪያውን ወይም መለኪያውን በተመለከተ አጨቃጫቂ የሆነ ክርክር አለ።አንድ ማህበረሰብ ጋር ደልደል እና ደርፎጭ ያለች ሴት ውብ ስትባል በሌላው ማህበረሰብ ደግሞ ሰበር-ቅንጥስ የምትል ሴት ውብ ነች ይባላል።በግለሠብ ደረጃም እያንዳንድ ሰው የራሱ የሆነ ቴስት አለው። አሮራ ግን ለማንም ሰው አስማሚ የውበት ሚዛን ነች።ሴቶች በቅናት ወንዶች በመጎምዠት  እኩል የሚያደንቋት ሴይጣንም መላዕክም እኩል የሚስማማባትና ሳይጨቃጨቅ የሚመርጣት የውበት ጣኦት ነች።የወንዶችን  የፍቅር ስሜታቸውንና የወሲብ ረሀባቸውን በአንድ ቅፅበታዊ እይታ የማናጋት ልዩ ኃይል ያላት አደገኛ ሴት ነች፤በዛ ላይ ተስረቅራቂና ተንሳፋፊ ድምፅ ያላት ታዋቂ ወጣት ድምፃዊ ነች።
አሮራ እድሜዋ 21 ነው።የምትኖረው ኑሮ ከላይ በድፍኑ ሲታይ እጅግ የቅምጥልና  ፍፅም የምቾት ነው።አባቷ ከተማዋን  ከሚዘውሩ ጥቂት  ቱጃሮች መካከል አንደኛውና ዋነኛው ነው።በዛ ላይ በእሷ ህይወት ውስጥ ፍፁም አድራጊ ፈጣሪ ከመሆኑም በላይ ማናጀሯ  ነው።በእሱ በኩል ካልሆነ ማንም ሰው ወደዚህቺ አማላይና ፅፀ-ወሲብ ወደ ሆነች ልጅ  መጠጋት አይችልም።ለሠላምታ እንኳን እሱ መፍቀድ አለበት።
አሮሯ አሁን የገዛ መኝታ ቤቷ አልጋዋ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላለች።ፊት ለፊቷ የልቧ ሰው የሆነው ተወዳጅ አጎቷ እዝራ ቁጭ ብሎ እያጫወታት ነው።እዝራ አጎቷ ብቻ አይደለም ከ20 ዓመት በላይ የእድሜ ልዩነት በመሀከላቸው ቢኖርም ብቸኛውና ተወዳጅ ጓደኛዋም ጭምር ነው።ለሰው የሚነገር ሆኖ ለእሱ የማትነግረውና ከእሱ ጋር ማትማከርበት አንድም ጉዳይ የለም።ክፋቱ ከእሷ ነገሮች አብዛኞቹ ለማንም መነገር የማይችሉ አሰቃቂ ጨለማ ምስጢሮች በመሆናቸው እሱም ቢሆን እንኳን ስለእሷ የማያውቃቸው ነገሮች ከግማሸ ይበልጣሉ።
እዝራ አባቷ ካለምንም ገደብና ክልከላ እንደፈለገች እንድትገናኘው የሚፈቅድላት ብቸኛው ሰው ነው።ምን አልባት በጣም የሚወደው ብቸኛ ታናሽ ወንድሙ ስለሆነ ሊሆን ይችላል?ምን አልባትም ነገረ-አለሙን እርግፍ አድርጎ በህይወት ተስፋ የቆረጠ ጉዳት- አልባና ጥቅም-አልባ ሰው አድርጎ ስለሚያስበውም ሊሆን ይችላል።

"ሮሪ ስምሽን አሮራ ብሎ ማን እንዳወጣልሽ ታውቂያለሽ?"ሲል ጠየቃት።
"አጎቴ አውቃለሁ አንተ ነህ።"
"ከመልክሽ በላይ አንፀባራቂ ስም ነው ያወጣሁልሽ።አሮራ ጥልቀት ያለው ብርሀናማ  ስም ነው።ቀለል አድርገሽ ስትተረጉሚው  በማለዳ  ከእንቅልፍሽ  ተነስተሽ ከነቢጃማሽ በረንዳ ላይ ቁጭ እንዳልሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ብልጭ ስትል የምታያት ልብ ሰንጣቂ  የፀሀይ ብርሀን ማለት ነው።በሌላ ጎኑም ማታ ለመጨረሻ ጊዜ ውስጥሽ በፍራቻ እየተሸበረ እያየች ግን ደግሞ ተሠናብታሽ የምትጠልቀው የመጨረሻዋ የፀሀይ ፍንጣቂ  ማለት ነው።"
"አጎቴ ስሜ ብዙ ትርጉም ያለው ነው..አውቃለሁ ደጋግመህ ነግረኸኛል።"
"አዎ ነግሬሻለሁ።የፀሀይ አካል የሆኑ የኤሌክትሪክ ቻርጆች (ፓርቲክሎች) በምድር አካባቢ  ከሚገኙ ናይትሮጂን እና ኦክስጅንን ከመሰሉ ጋዞች ጋር  ሲዋሀድ   የሚፈጠርና  በምድር  ከፍታ(ሰማይ) ላይ በሚፈጠር በአረንጓዴ ፣ቢጫ፣ ቀይና ነጭ ቀለም የሚገለፅ የተፈጥሮ ክስተት ማለትም ነው።ሌላውጨደቡብ እና ሰሜን ዋልታ ጫፍ ላይ ያለች ውብና ተወዳጅ የፀሀይ ብርሀንም ብለሽ ብትተረጉሚው ትክክል ነሽ።"
"አጎቴ ይሄንን ስም ለእኔ መሰየም የለብህም ነበር።ዝብርቅርቅ ትርጉም ያለው ስም ሰጥተኸኝ ዝብርቅርቋ የወጣ ልጅ ሆኜ ቀረሁ።" አለችው።
"ወድጄ ይመስልሻል ይሄን ስም የሰጠሁሽ?እንዲህ አሁን ባለሽበት አፍላ እድሜ ላይ ጣሊያን እያለሁ  ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ ልቤን የከፈትኩትና በእንብርክኬ እስክሄድ ያፈቀርኩት አሮራ የተባለች  ስፔናዊት ልጅን ነበር...."
ንግግሩን አቆመና ኪሱን በረበረ...የሮዝማን ሲጋራ ፓኮውንና ላይተሩን ከኪሱ አወጣና  አንድን ከውስጡ መዞ በመለኮስ የሲጋራውን ፓኮና ላይተሩን ፊት ለፊት ጠረጴዛው ላይ ጣል አድርጎ  የለኮሰውን ማብነን ጀመረ...እዝራ ይሄንን ታሪክ ለአሮራ ሲነግራት   ምን አልባት ለአስር ሺኛ ጊዜ ሊሆን ይችላል ።እሱም ስለፍቅረኛው አሮሯ  አውርቶ አይደክመውም እሷም አይ ይሄኛውን ታሪክን ከመቶ ጊዜ በላይ ነግረሀኛል አሁን ሰለቸኝ መስማት አልፈልግም ብላው አታውቅም።እንደዛ የማትለው ደግሞ እሱን ማስቀየምና ማስከፋት ስለማትፈልግ ብቻ አይደለም በእሱ የማፍቀር መጠንና ጥልቀት ስለምትቀናም ጭምር  ነው።በእሱ መጠን አፍቅሮ በእሱ መጠን መሠቃየት ስለሚያምራት ነው።እንደዚህ እንዴት ልታስብ እንደቻለች ለራሷም ይገርማታል።እንደእሱ ለይቶላት ህይወቷን ሙሉ በሙሉ እርግፍ አድርጋ በመተው የሙሉ ጊዜ እብድ አትሁን እንጂ ከእሱ የበለጠ የውስጥ ህመም፤ ከእሱ የበለጠ የልብ መሠባበርና የስሜት መፈረካከስ ያጋጠማትና በዛም የተነሳ የማይድን በሽታ ታቅፋ የምትኖር ልጅ  ነች፣ለዛውም በዚህ ጨቅላ ዕድሜዎ። እሱ ግን ስለዛ መራር የስደት አለም የፍቅር ታሪኩ ለእሷም ሆነ ለሚያዳምጠው ለማንኛውም ሰው ሲያወራና በናፍቆት እንባ በጉንጮቹ እያንጠባጠበ በኩራት ሲተርክ ደስታውንም ሆነ ሀዘኑን ከሌላው ሲያጋራ ይኖራል ።በዛም እራሱን ያክማል።እሷ ግን እንደዛ አይነት እድል የላትም።ስለፍቅር ታሪኳ ለራሷም የማውራቱ ሞራልም ሆነ ድፍረቱ የላትም።ስሜቷን አዳፍና ህመሞን በውስጧ ቀብራ እህህ ማለት ብቻ ነው ያላት እድል።እስከአሁን ግን እንዴት እንደእሱ እንዳለየላትና እንዳላበደች ይገርማታል...አንድ ቀን ግን የእሱ እጣ እንደማይቀርላት እርግጠኛ ነች።ከአንድ ቤት ሁለት እብድ።

እዝራ ሲጋራውን ግማሽ ድረስ ከማገ በኃላ ወሬውን ካቆመበት ቀጠለ"አሮራ ልክ እንደአንቺ ውብ ነበረች.. ጥርት ያለ ድምፅ፣ልስልስ ቆዳ፣ ስስ ልብ...ሰው ሳይሆን ከሰማያዊው መንደር ጠፍታ በስህተት በምድር እየኖረች ያለች መላአክ ስለምትመስለኝ አብዝቼ እሳሳላት ነበር...ስስማት እንኳን ከንፈሯን አሳምማት ይሆን ?እያልኩ እጨነቅ ነበር።በሆነ ንግግሬ ግንባሯን ከቋጠረችማ በቃ  ክፍሌ ገባና በራፌን ዘግቼ በጉልበቴ ተንበርክኬ ለሠራሁት ሀጥያት እግዜር ይቅር እንዲለኝ እፀልይ ነበር።በእሷ ምክንያት የድሮ ነገሬን ሁሉ ረስቼ ነበር።ከኢትዬጰያ መሄዴን ረሳሁ።ዘመዶች እንዳሉኝ እረሳሁ።ጥቁር መሆኔንም እረሳሁ።..በቃ እኔ የአሮራ ፍቅር ብቻ ሆንኩ።ለመጋባት ወሰንን፣ እቤት ገዛን ፣ሁሉ ነገር ተዘጋጀን ...ግን ለሰርጋችን አንድ ወይም ሁለት ቀን  ሲቀረን እሷ ከጎደኞቾ ጋር እቃ ለመግዛት የሆነ ሱፐርማርኬት እንደገባች አጋጣሚ ሆኖ  የሆኑ ዘራፊዎች በቦታው ተከሰቱ፤ ፓሊስ በአካባቢው ስለነበረ መታኳስ ጀመሩ ፤ከአንድ አስጠሊታ ሽጉጥ የወጣች አስጠሊታ ጥይት የእኔ መልአክ  ጉሮሮ ውስጥ ተሠነቀረች።ከዛ አሮራ የምትጠልቀው ፀሀይ ሆነች....ከዛ በኃላ እንደምታውቂው  ሁለ ነገሬ ፈራረሰ ..መስራትም መማርም አልቻልኩም። ከአስር አመት ቆይታ  በኃላ ሳልወድ  በግድ  ግማሽ ልቤና ግማሽ ነፍሴ ታሞ ወደሀገሬ ተመለስኩ።ስመለስ ወንድሜ እንዳገባ እንኳን ሳላቅ አንቺን የመሰለች ፀሀይ ልጅ ወልዶ ጠበቀኝ ።በወቅቱ አምስት አመትሽ ነበር ።በጣም ነው የወደድኩሽ ...ሰው ሁሉ ቢያስጠላኝም አንቺን ግን ወደድኩሽ። ከዛ አንቺም የምታንፀባርቂ ፀሀይ ስለሆንሽ እግረመንገድም ለፍቅሬ መታወሻ ለማድረግ...ማለቴ በየቀኑ ደጋግሜ  ስሟን ለመጥራት እድሉን ለማግኘት ስል  አሮራ የሚል ስም
7.0K views◔͜͡◔ A ◔͜͡◔, 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-16 13:42:08 የእናቴ ልጅ
ክፍል ሠላሳ ሁለት
የመጨረሻ

ቀን ቀንን እየተካ በሄደ ቁጥር በወንድሜ ላይ የነበረኝ የመረረ ጥላቻ እና ቂም እየደበዘዘ ሲመጣ ይታወቀኛል  ይህን ስሜት ወደድኩት ምክንያቱም እኔ ቂመኝነት በውስጤ ሰርፆ ቤቱን እንዲሰራብኝ የምፈልግ ሰው አይደለውም ። መጥፎ እና ልክ ያልሆኑ ጉዳዮች ጭንቅላቴ ውስጥ ጊዜ ወስደው በቁዩ ቁጥር እታመማለው ፡መረጋጋት አልችልም ። ያንን ስሜት ለማስታገስ ስል ነውጠኛ ነው የምሆነው ፡ከዚበፊት የእናቴን ጥላቻ እና የሰፈሬን ሰው ግልምጫ ለመወጣት ስል ንዴቴን ካገኘውት ሰው ጋር ሁሉ ነገር ፈልጌ እጣላ ነበር ። አሁን ላይ ከጉርምስናውም እየወጣው ነው እና ያ ስሜት እንዲቆጣጠረኝ አልፈልግም ። ስለዚ በወንድሜላይ ያለኝ ብስጭት እየቀነሰልኝ ሲመጣ ተጠቃሚ ነኝና ደስታ እየተሰማኝ ነው ። እሱ በሰው አገር ላይ ምን እያሳለፈ እንዳለ የምናውቀው ነገር የለም ። ሲዊዲን መድረሱን ከተቀባዮቹ ጋር ሆኖ ለእናቴ ደውሎ ከነገራት በዋላ ።ድጋሚ ደውሎም አያውቅም ። እናቴም ብትሆን ጨከን ብላበታለች ። 'ከአሁን በዋላ ቤተሰብ አለኝ ብለህ ወደእኛ እንዳታስብ 'ብላ እንደተናገረቸው አባቴ ነግሮኛል ። በእርግጥ ምንእንደሚሰማት  እሷው ነው የምታውቀው ።የእናት አንጀት እንዲ በቀላሉ ይቆርጣል ማለት ዘበት ነው ። አባታችንም ቢሆን ስሙን ለማንሳት ድፍረቱ ባይኖረውም አንዳንዴ በጨዋታችን መሃል ተክዞ ተክዞ በረጅሙ ሲተነፍስ አጋጥሞኛል ።ምን አልባት ስለ አቤል እያሰበ ይሆናል ብዬ እጠረጥራለው  ።
እኔ እራሱ ሳስበው ለአቤል እንዲመሆን ጥፋተኛው ማነው ? ብዬ አስባለው ። ያለ አባት አድገናል ፣እናታችን የሌለ አቅርባው አቅብጣውም ነበር ። የራሱስ አስተዋፆ ? እኔስ ብሆን ጥፋቶቹን በኔ ሲያላክክ የረዘመ ዝምታ አሳይቼስ አልነበረ ? ብቻ አንዳንዴ ሳስበው አቤል እንዲ እንዲሆን ትንሽ አስተዋፅዖ ሳይኖረን አይቀርም እላለው !!!!
እሁድ ቀን  ተሰብስበን እንደተለመደው እየተጨዋወትን ፡ ቤቱን ሞቅ ደመቅ አድርገነዋል ፣ አባታችን እናቴን እየቀለደባት ያስቀናል ማማ በእናቴ ዙሪያ እየዞረች ባልገባት ነገር ትፈነድቃለች የኛ ሳቅ ሳይጋባባት አይቀርም ፣ እናቴ  ስለተሳቀባት አልከፋትም በጣም ደስተኛ ትመስላለች በባሏ ጎኗ መሆን ሙሉነት ሳይሰማት አይቀርም ልዩ ሆናለች ፡ በዛላይ ትላንትና የማማን እናት በማግኘቷ እፎይታ ተሰምቷታል ፡ የአቤልን ትልቅ ስህተት እንዳረመች ሳይሰማት አይቀርም ፡ የማማን እናት ይዛት መጥታ በማንኛውም ሰአት ልጇን የማየት መብት እንዳላት ነግራ ፡ ነገር ግን እፃኗ ከኛጋር መኖር እንዳለባት አስረግጣ አስረድታታለች እሷም ብትሆን ለልጇ ያን ያክል የምትጓጓ መስላ አልታየችም ።እንዲ መሆኑን የፈለገች ነው የምትመስለው ይሄ በራሱ ለኔም እንደ ግልግል ነው ።በአራስነቷ የተረከብኳትን ስንት ነገር ያየውባትን ልጅ ልውሰድ ብትል ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም ።  ማማ ለኔ ትምህርት ቤቴ ናት በሷ የተነሳ እራሴን ገዝቻለው  ስለ ዓለም ክፋት ደግነት አይቻለው  ማጣት ምን ያክል እንደሚፈትን ገብቶኛል ። ብቻ ብዙ ብዙ ,,,,,
ዛሬ ላይ ግን በዛ ሂደት ውስጥ ስንት የምወዳቸውን ሰው አውቄ አለው ።ለየት ባለ መልኩ ባዩሽን የክፉ ቀኔ ። ብሌኔን ፍቅሬን የወደፊት ሚስቴ የአይኔን ማረፊያ ፡የልብ ምቴ የሕይወቴ ቅመም ማጣፈጫዬን ፡ ብሌኔ ውዴን ብሌኔ ብሌኔ ፡ስሟን እንኳ ስጠራው የሆነ መሃዛ ከአፌ ወጥቶ አብሮ ያውደኛል  ብሌኔ ብሌኔ ......
እረፋዱ ላይ አንዳችን በአንዳች እየሳቅን ጨወታችን ደርቶ ፡  ሳለ የእናቴ ስልክ ጮኽች ።እናቴ እንደሌላው ጊዜ አልፈጠነችም ታነሳዋለች ብለን ስንጠብቅ ፡ወደኛ ማየት ሆነ ። ስትዘገይብኝ ስልኳን አንስቼ ቁጥሩን አየውት የውጪ ለጠ ር ነው ደንገጥ አልኩ ። እናቴ በፍርሃት ስታየኝ
"የውጪ ስልክ ነው አንሺው አልኳት "
"አንተአንሳው "አለች እንደፈራች ስለገባኝ ፡ እኔው አነሳሁት
"ሄሎ "
"ሄሎ የወይዘሮ ዘውድነሽ ስልክ አይደለም "አለኝ የሴት ድምፅ ድንጋጤዬ ጨመረ አቤል ምን ሆኖ ነው
"ነው ማን ልበል አንቺን"አልኳት
"ዲና እባላለው እእ ከሲዊዲን ነው የምደውለው "አለች
"እሺ ምምን የየተፈጠረ ችግር አለ ወንድሜ ምን ሆኖ ነው "አልኳት እየተርበተበትኩ ።እናቴ ስታቃስት ሰማው ዞሬ ሳይ ዕንባዋ ቀድሟል ።
"ኧረ ተረጋጋ እሱ ምንም አልሆነም እኔ ፍቅረኛው ነኝ ያው ብቻ ስለ እናንተ ብዙጊዜ ያወራኛል እና ዛሬ አበረታትቼው አብረን እናወራቸዋለን ብዬ ነው በስንት መከራ የደወልኩት "አለች ፈጠን ፈጠን ብላ
"ድምፁን መስማት እንችላለን "አልኳት
"አዎ እባክህ አንተ ወንድሙ ከሆንክ በጣም ተፀፅቷል እና ይቅር በለው  "አለች
"ችግር የለም ይቅር ብዬዋለው አጠገብሽ ካለ ስልኩን ለሱ ስጪው እናቱን ያናግራት "አልኳት
"እሺ "ብላ ስታስተላልፍ እኔም ስልኩን ለእናቴ ሰጠዋት ።እናቴ ልትደብቀው የማትችለው የልጇ ፍቅር ገንፍሎ ወጣ ፡ በቃ ከአቤል ጋር በናፍቆት አወሩ በተደጋጋሚ ይቅር በይኝ ሲላት ይሰማል ልቡ የተሰበረ ይመስላል ፡ ከአባታችንም ጋር አወራ ፡አባታችንም አለቀሰ ፡ብዙ ነገር ተናገረው እንደዚ አይነት ክፋት ከገዛ ልጁ ስላልጠበቀ እስካሁንም ድረስ እየተሰቃየ እንደሆነ ነገረው አቤል ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ ይሰማል ፡ጓደኛው ነኝ ያለችው ሴት ታባብለዋለች ፡ላውድ አድርገነው ስለሆነ የምናዳምጠው ፡አክስቴ ደግነሽም ባዩሽም ማልቀሳቸው አልቀረም ፡ አክስቴ ደግነሽ ወደኔ እያየች "ይቅር በለው ልጅነት ነው አውሬ ያደረገው "አለችኝ ሆደባሻነቷ አይሎ ፡  እኔ ውስጤ ተረጋግቷል ሞተ የምባል መስሎኝ ስለነበር ክፉ ነገር ስላልሰማው ሰላም ሰፍኖብኛል ። ዓለም እንግዴ እንደዚ ናት እንደ ዥዋዥዌ ነው ነገሯ ወደዚ ወደዚያ ፣ እንደ ፈለገች አንተ ጠንክረ ገመዷን ይዘህ እየተቆጣጠርክ ካልተጫወጥክ ፈንግላ ልትጥልህ ትችላለች ፡ እራስህን ከማንም ጋር ሳታወዳድር የማንንም ንዋይ ሳትመኝ የሕይወት መንገድህን በራስህ በንፁ ሕሊናህ ታግዘህ አስምር መስመሩ ሲበላሽ በትህግስት እያስተካከልክ  ወደፊት ቀጥል ። ለሌሎች የደስታ የሰላም ምንጭ እንጂ ፣የስቃይ የመከራ ምንጭ አትሁን ፣ አንተ ደስተኛ የምትሆነው በዙሪያህ ደስተኞች ሲኖሩነው ፡ 'ብቻህን በሚያለቅሱ ሰዎች መሃል ብትስቅ እብድ ነው የምትባለው'
             ,
                  ተፈፀመ
ደራሲ Unknown

    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
7.1K viewsTsiyon Beyene, 10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-15 18:05:59 የእናቴ ልጅ
ክፍል ሠላሳ አንድ

ከባባድ የሚባሉ ጉዳዮችን አለፌለው ነገሮችን ሲናገሩት እንደሚቀሉ ሆነው አታገኛቸውም ፡በውስጡ ማለፍ እንደመናገር ላይሆን ይችላል ፡ ነገር ግን ምን አማራጭ አለህ ፡ አልችልም አልቻልኩም ካልክ ፡ አይምሮህ በራሱ ጠላት ነው የሚሆንብህ ።
አልቻልኩም ስትለው አዎ አትችልም የሚለውን አሳብ ወስዶ ይደጋግመዋል ፡ ይበልጥ እንዳትችል ያደርግሃል። ለራስህ መንገር ያለብህ ይሄ ጉዳይ ከባድ ነው ነገርግን ፡ እወጣዋለው !በየቀኑ የመጣብኝን ችግር ለመቅረፍ አእሰራለው እታገላለው ፡ እናም ደሞ ቀስ በቀስ አሸንፈዋለው ማለት መቻል አለብህ።
    እውነት ለመናገር አልችልም አይሆንልኝም ብትልስ ቁጭብለህ አደጋዎችን ከማስተናገድ ውጪ ምን ታመጣለህ ?ምንም ! ከዛ ይልቅ እየተንቀሳቀስክ እየታገልክ በሕይወት ጎዳና ላይ  ወደፊት ብትራመድ አይሻልም።  በነገራችን ላይ ፈጣሪም በኑሮህ በግንኙነቶችህ ላይ ለውጥ እንዲመጣ እየጣርክ ስትፀልይ ነው የሚሰማህ ።
ከነገሮች ማለፍ በዋላ ዛሬ ሁላችንም እንደ ቤተሰብ ተሰብስበናል ።ቤተሰቦቼ ተሟልተዋል ማለት ይቻላል ፡እናትና አባቴ ፣አክስቴ ደግነሽ እና ፡ በችግሬ ወቅት ያገኘዋት የእናት ያህል የማያት ባዩሽ ፣  ትንሿ  ማማ ፣ሁሉም ተሰብስበው ቡና እየተፈላ ምግብ ቀርቦ እየበላን ንፁ የሆነ ጨዋታ እየተጫወትን ቅዳሜን ቀን በጥሩ መንፈስ ጀምረነዋል ፡ እንዲ አይነት የተረጋጋ ቤተሰባዊ ግንኙነት መፍጠር ቀላል አይደለም ፡ ሰላም እና ጤና ያለው ደስተኛ ቤተሰብ  ያለው ሰው እሱን መቼም እንዳይበረዝ መንከባከብ አለበት ፡ ምክንያቱም  የአገር ሰላም እራሱ የሚጀምረው ከቤት ነው ፡ ቤት የተሰራነገር ነው አንዳንዴ  ወደውጭ ወጥቶ ፡ ማህበረሰቡን ብሎም አገርን የሚረብሸው ።
እናም ለቤተሰብህ የምትሰጠውን ትኩረት ከልብህ አድርገው  እልሃለው
አቤልን በሰው ሀገር ሕይወት የራሷን ምክር ትስጠው ብለን ትተነዋል  ።እናም የማማን እናት ጭምር እናቴ እያፈላለገቻት ነው ።እናቴ እሷም ወዳ አይደለም ልጇን እኛላይ እንድትጥል የሆነችው ።አቤል ነው አላፊነቱን መውሰድ ያለበት የሚል አሳብ አምጥታለች ።እኔም ብሆን ነገሩን በተረጋጋ መንፈስ ሳስበው ልክ ናት ፡ ለዚሁሉ ጥፋት መነሻ አቤል ነው ። እሱው ነው መቀጣት ያለበት ያቺ ሴት ከልጇ ጋር የሚገባትን ቦታ እንሰጣታለን ብዬ እኔም በእናቴ ውሳኔ ተስማማው.....


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
7.3K viewsTsiyon Beyene, 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 10:21:41 የእናቴ ልጅ
ክፍል ሃያ ስምንት

አባታችን አቤል ላይ መንገድ ዘግቶ ሲቆም ምን ሊፈጠር ነው በሚል ሁላችንም ማፍጠጣችን አልቀረም ። አቤል ፍርሐቱ እንዳለ ሆኖ የአባታችንን ሁኔታ ለመጋፈጥ አይል ለማሰባሰብ ሲሞክር አየውት እጆቹን እንደማወራጨት ብሎ  ወደክፍሉ ለመግባት አባታችንን ዘወርበልልኝ በሚል አስተያየት አየው ።
"እስካሁን ምንም አይነት የጥፋተኝነት ስሜት አላየውብህም ።ከዛ ይልቅ ስላወቅንብህ የቆጨኽ ነው የምትመስለው ፡እንዴት በአንድ ወንድምህ ላይ የዚህን ያክል በደል አድርሰህበት ምንም አይመስልህም ፡እውነት አንተ የኔ ልጅ ነህ ምን አይነት ጉድ ነህ ፡ አንተ ዛሬ አንድኛውን ልጄን አሳጥተኽኝ ነበር  አዎ እዛቦታላይ ደርሼ ነገሩን ባላስቆመው ኖሮ በጭካኔ አስገድለኽው ነበር እና ስለዚ አንተ የሚገባህ በሰላም ወደ ክፍልህ ገብተኽ መተኛት ሳይሆን መቀጣት ነው ያለብህ ፡እና የትም እንዳትሄድ እዚሁ ቁም የወንድምህን ውሳኔ እስክትሰማ "አሉት ።እናቴ በድጋሚ አለቀሰች ።እናቴ ምናልባት ዛሬ ባለቤቷን በዛ መልኩ በማግኘቷም ጭምር ግራ መጋባት ውስጥ ሳቶን አትቀርም ፡ብዙ አዘኖች ተደራርበው እየሰባበሯት ነው ምን እንደምትወስን ገና አላወቀችም ፡አቤልን ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ገብቷታል ። እኔ ደሞ አሳቤ ሁሉ ተምታቶብኛል ፡ የአባታችን በዚመጠን እራሱን ዝቅ አድርጎ ከኛ መደበቁንና ፡አኗኗራችንን ሲከታተል መቆየቱ በጣም ነው ያሳዘነኝ ።ጠጋብሎ ያለበትን ሁኔታ ቢነግረን ምን አለ ፡ ይሁሉ ላይፈጠር ይችል ነበር ፡እናታችን ያለአጋዥ ያሳለፈችውን ሕይወት በግልፅ ቢመጣ ያቀልላት ነበር  ።መቼም እናቴ በግልፅ ነገሮችን ስትረዳ ለይቅርታ አትሰስትም ።  ግን ያሳዝናል። እንግዲ አባታችን በራሱመንገድ እራሱን እየቀጣ ነበረ ። አቤል በአባታችን ቆፍጠን ያለ ንግግር የተደናገጠ መሰለ እናም እየተርበተበተ "እኔ ስለምትሉት ነገር አአላውቅም ሆነ ብለው እኔንና ወንድሜን ለማለያየት ያደረጉት ነው ፡ "አለ ።እኔ በጣም ተናደድኩ መናገር ግን አቃተኝ ።
"ተው ተው ቢያንስ እንኳ ከዚ በዋላ እንኳ ለመፀፀት ልብ ይኑርህ"አለው አባታችን ተቆጥቶ
"ለምን ባላረኩት ነገር እፀፀታለው ፡"አለ አቤል በድርቅና
"አንተ የማትረባ ልጅ እናትህ እንዴት አድርጋ እንዳሳደገችህ አላውቅም ፡ በጣም አስመሳይ እና ከሃዲ ነህ አንተ ልጄ አይደለህም አፈር ብላ "አለው አባታችን በንዴት ጦፎ
"እኔም ድንገት አንድ የጎዳና ሰው መጥቶ አባትህ ነኝ ቢለኝ የምቀበል ሰው አይደለውም "ሲል ለመነሳት ሞከርኩ አቅም አጣው ።እናቴ ግን ከመቅስበት ተነስታ እኔ ያሰብኩትን ፈፀመች ።አቤልን ሄዳ በጥፊ ስታጮለው ቤቱውስጥ ፍንዳታ የተከሰተ መሰለ ።ደስ ነው ያለኝ ።እራሴን ግን አልቻልኩም ፡ ህመሙ እየበረታብኝ ነው አይኖቼ ብዥዥ እያሉብኝ ነው ።የአባታችን ቁጣ ወደ አይል ተለወጠ እናቴ ከዚ በፊት የአባቱ ልጅ ብላ በስድብ መልክ የተናገረችኝ ትዝ አለኝ ፡ አባቴ የመጨረሻ ትህግስቱን ሲያጣ ማንም አይችለውም ፡ልክ እንደኔ ፡ አቤልን አንቆ ያዘው ።
"አንተ ደደብ እያናገርኩህ ያለውት ስለኔ አይደለም ስለ ምስኪኑ መልካሙ ወንድምህ ነው ፡እና እኔን ልትዋሸኝ ነው ና እንደውም ከአጋርህ ጋር ነው የምትቆየው ።እዚህማ በሰላም አታድርም እውነቱን ከሱጋር ታወራላቹ !!"ብሎ አባታችን አቤልን እየጎተተው ከትልቁቤት ይዞት ወጣ ። አቤል ለመከላከል ሲሞክር ደና ጥፊ አቀመሰው ። እናቴ ወደ እኔ አየች
"እናቴ በአቤል ተቀጥሮ ሊገለኝ የነበረው ልጅ እዚ ነው ያለው ይዘነው መጥተን ሰርፒስ ቤት ቆልፈንበታል እዛ ነው የሚወስዱት "አልኳት ።አፏን ያዘች ። ደግነሽ "ጉድ ነው ኧረዋ ጭካኔ ፡እኔ አፈር ይብላኝ ናቲዬ ወንድሜ ወንድሜ ስትል ለሱ ስትለፋ ፀባዩ ተስተካክሏል ስትል ድፍት አድርጎ ሊያስቀርህ ነበር ፡ናቲዬ መቼም አንተን ገሎ አያቆምም ነበር እናትህም አይቀርላት ፡መቼም ገንዘብ አይን ያሳውራል አብዝቶ መውደድ አያስፈልግም ኧረ ኧረ"አለች ።ባዩሽ አንገቷን ነቀነቀች ።
የጊቢያችን መጥሪያ ስታቃጭል ተሰማ  ደግነሽ "አሁን ደሞ ምንድነው "አለች
"ተረጋጊ ብሌን ትሆናለች "አልኳት
"እሺ እኔ ከፍታለው "ብላ ወጣች እናቴ ወደኔ ቀረብ ብላ"ደና ነህ ግን ልጄ አኪም ቢያይህ አይሻልም ፡ከሱጋር ስንጨቃጨቅ አንተን እረሳንህ ።"አለችኝ
"አይ ደና ነኝ እናቴ አታስቢ ትንሽ እራስምታት ነው "አልኳት እንደ እውነቱ ከሆነ ከባድ ነው  ።ብሌን ስትገባ ድንገት ተነስታ እንደመጣች ያስታውቅባታል ቢጃማዋ ላይ የሴት ካቦርት ነገር ጣል አድርጋ ነጠላ ጫማ ተጫምታ እረጅም ፀጉራ ላይ ሻሽ ሸብ አድርጋ ለች ።ሁኔታውን ወደድኩት ሁሉም ነገር የሚያምርባት ልጅ !!!!    ስታየኝ በድንጋጤ ወከክ አለች ስፍስፍ ብላ ስትነካካኝ "ደና ነኝ አትጨነቂ "አልኳት
"አይ አይ ደና አይደለህም ምንድነው እሱ በፈጣሪ "አለች አናቴላይ የተጠቀለለውን ጨርቅ በፍርሃት ነበር የምታየው
"ደና ነኝ ሳላስበውከዋላ አጠቁኝ  ሁኔታው ያስፈራ ነበር አሁን ግን ደና ነኝ "አልኳት
"ታውቆኝ ነበር እንዲ አይነት የተጨናነቀ እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም በጣም አስፈሪ የሚያስደነግጥ ስላንተ ብቻ ነበር የኔ ውድ በጣም ጎድተውሃል "አለችኝ ዕንባዋን እየታገለች
"እእ አዎ በእርግጥ ቅጥረኛ ነብሰ ገዳይ ነበር አመጣጡ ሊገለኝ ነበር "አልኳት ሳወራ እራሱ አቅም እያጣው ነበር
"በቃ በቃ ዝም በል ።ተነስ አሁኔ አኪም ሊያይህ ይገባል እንዳየሁት ከሆነ ደም ፈሶሃል ተነስ "አለቼ
"ብሌን የኔ ውድ አትጨነቂ ደና እሆናለው "አልኳት
"አይ እንደሱ አይደለም ስታድር ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም ግድ ነው ተነስ መሰፋት ያለበት ቦታ ሊኖር ይችላል "አለች ።እናቴ አሳቧን የሚጋራት በማግኘቷ ደስ ያላት ይመስላል ቀብሌን አሳብ ተስማማች እሷም ግፊት አድርጋ ።በመጨረሻ ተስማማው ።ስንወጣ አባታችን ከሰርፒስ ቤቱ ወጥተው ሲመጡ አይታ ብሌን በጥያቄ አስተዋለችኝ።
"እሳቸው ናቸው ያዳኑኝ ታሪኩን ሌላ ጊዜ እነግርሻለው "አልኳት
"እሺ "አለች ።አባታችን ወደ አኪም ቤት መሄዳችንን ስንነግረው ተስማማ ።እናቴ እና ብሌን ከኔጋር አብረን ውጪ የቆመችዋ የብሌን መኪና ውስጥ ገባን ። ቀስበቀስ አቅሜ እየተዳከመ መጣ ወደ እናቴ ዘንበል አልኩ እናቴ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል ።እጇን በትኩሳት ያበደ ጭንቅላቴ ላይ ጣል አድርጋ ታሻሸኝ ጀመር ....
ብሌን መኪናዋን በፍጥነት እየነዳች ስቅ የሚል ድምፅ ስታወጣ ይሰማኛል ፡የኔ ፍቅር የኔ እብድ ዛሬ በኔ እየተፈተነች ነው ምንም እንዳልሆንባት ነው የምትፈልገው ...........


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
3.2K viewsTsiyon Beyene, 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 21:00:03 "ልጅ ያላትን ሴት ማን ሊፈልጋት ይችላል እና በዚህ ምክንያት እሱን ላጣው ነው" እንባዬ ከየት መጣ ሳልለው ዱብ ዱብ አለ።

"እና የእውነትም ልጅ አለሽ ማለት ነው"

"አዎ አለችኝ"

"የት?.... እንዴት?... ማለቴ..." አይን አይኔን እያየ ቀበጣጠረ

ከውስጤ አንዳች ነገር ፈንቅሎ የወጣ እስከሚመስለኝ በሀይል ተናገርኩ"ዝርዝሩን አይደለም ላንተ ለራሴም ደግሜ አልነግረውም እና ለዮናታንም ቢሆን ንገረው በጣም የምወዳት ልጅ አለችኝ ግን ስለ ልጄ የት? እንዴት? ከማን ወለድሻት? የሚል ጥያቄ የሚጠይቀኝ ከሆነ አጠገቤ እንዳይደርስ ንገረው.... አንተም ብትሆን እንደዛው" በተቀመጠበት ትቼው እያለቀስኩ ወደ ዶርም ሄድኩ። በር ላይ ስደርስ የዶርም አጋሮቼ እንዳያውቁ እንባዬን ጠራርጌ ገባሁ። የለበስኩትን ቱታ በቀሚስ ቀይሬ ነጠላዬን አንስቼ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩ። ገና የውጨኛው በር ላይ እንደደረስኩ እንባዬን ዘረገፍኩት

"ለምን አምላኬ...? ያለፈው ህመሜን ለምን እንድረሳው አታደርገኝም? ለምን ዛሬ እንደሆነ ሁሉ እንደፊልም አየዋለሁ? ዛሬም ከእንቅልፌ በርግጌ መነሳት ዛሬም ስለልጄ ሲጠይቁኝ ደስተኛ ሆኜ ስለሷ ከማውራት ይልቅ እሷ የተፈጠረችበትን አጋጣሚ መርገም..... አምላኬ እኔ ከአቅሜ በላይ ሆነብኝ... እንዴት ባደርግ ነው ትላንትናን ረስቼ ዛሬን መኖር የምችለው...." ረጅም ሰዓት በእንባ እና በእልህ ነገርኩት።

ብዙ አመታቶች ቢቆጠሩም ደስተኛ ቤተሰብ ቢኖረኝም ህልሜ የነበረውን ህክምና እየተማርኩ ቢሆንም የህይወቴ ግማሽ ስኬት ትላንቴን ሊያስረሳኝ አልቻለም። ልክ ዛሬ እንደሆነ ሁሉ ያስፈራኛል.... እንዴት ወንድ የተባለ ፍጡር ላፈቅር እንደቻልኩ ለኔ ጥያቄ ነው። ቢያንስ ግን ውስጤ ያለውን የትዝታ አውሬ እስካልቀሰቀሱብኝ ለሰዎች ሰላማዊና የተረጋጋሁ ሰው ነኝ።

ክላስ ረፍዶብኝ በፍጥነት እየተራመድኩ
"እንኳን ደስ አለሽ ህያብ በዛብህ.... እንኳን ደስ አለሽ" እርምጃዬን ገትቼ ወደኋላ ዞርኩ.... የትናዬት

"እባክሽ ክላስ ረፍዶብኛል" ፊቴን አዙሬ ልሄድ ስል

"ዮናታን ወደ አዲስ አበባ እንደተዘዋወረ ሰማሽ"አለችኝ። ክው ብዬ ቀረሁ

"ምን እያልሽ ነው" ይሄን ሁሉ ቀን ሊያገኘኝም ሆነ ሊያወራኝ ያልፈለገው ልጅ አላት ስለተባለ እንደሆነ ቢገባኝም እሱ የኔ እንደማይሆን ባስብም ከአይኔ እንዲርቅ ግን አልፈልግም

"ህያብ ዮኒ እንደሚወድሽ ከኔ በላይ ማንም ሊያውቅ አይችልም። የኔ ይሆናል ብዬ ባንቺም ላይ በሌሎችም ላይ ብዙ ተንኮል ሰርቻለሁ... " ከአይኗ እንባ ኮለል ብሎ ወረደ

"ይቅርታ አድርጊልኝ ህያብ ከልቤ ነው ብዙ ነገር አድርጌሻለሁ። አንቺ እንኳን ለይተሽ ያላወቅሽውን ብዙ ነገር.... መምህር ውጤትሽን እንዲያበላሽ አልጋው ላይ ወድቂያለሁ... የዶርምሽን ልጆች ገንዘብ እየከፈልኩ እዚህ መሆንሽን እንድትጠይ አድርጊያለሁ... ይሄን ይሄን ብልሽ ጊዜ አይበቃኝም። እኔን ይቅር ባትይኝም ችግር የለውም ስለሚገባኝ ነው። እነሱን ግን ይቅር በያቸው ሁሉንም በደካማ ጎናቸው ይዣቸው ነው" ወደ ጎን ስታይ ከሷ እኩል ዞር ብዬ አየሁ ሁሉም ተደርድረው ቆመው ያዩኛል... አንደኛዋ መጥታ እግሬ ላይ ወደቀች ሌሎቹም ተከተሏት እነሱን አንስቼ ዞር ስል የትናዬት የለችም።

ኦ የትናዬት አልኩ ለራሴ አንደኛ አመት ላይ ሰርቻለሁ ያልኩት ኮርስ ውጤት ተበላሽቶብኝ ያየሁት መከራ ትዝ አለኝ።

ዶርሜ ውስጥስ ቢሆን አንዳቸው እንኳን ጓደኛ ሊያደርጉኝ ፈቃደኛ አልነበሩም በማደርገው በእያንዳንዱ ነገር ይሳለቁብኝ ነበር። ትንሽ ህይወት የምትባለው ትሻላለች። ትዝታ፣ ቤዛዊት እና ዝናሽ የነሱ ይለይ ነበር። እንደ ድንገት ተስቶኝ ከሎከር ውጪ እቃ ካስቀመጥኩ ወይም ሳልቆልፍ ከረሳሁ ወይ የሆነ ነገር ይጠፋል ወይም ደግሞ ቅባትና ሎሺኔ ግማሽ ደርሶ ነው የማገኘው... ኧረ ብዙ ብዙ ለመተኛት ካልሆነ ወደ ዶርም አልሄድም ነበር። የነሱ ይህን ያክል እኔን መግፋት ቢኒ ላይ እንድጣበቅ አደረገኝ። ቢኒ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነው ጓደኛዬ ወንድሜ አማካሪዬ አስጠኝዬ... ቃል ከሚገልፀው በላይ እወደዋለሁ። ለሴት ጓደኛ እንኳን ለመንገር የሚከብዱ ነገሮችን ነግረዋለሁ አማክረዋለሁ። ከ1 ነገር በስተቀር ስለኔ ሁሉንም ያውቃል ከ1 ውሸት በስተቀር ምንም ዋሽቼው አላውቅም እሱም የትውልድ ሀገሬ አዲስ አበባ እንደሆነ ነው የነገርኩት ሁሉም ቢሆን የሚያውቁት ይህን ነው። በአጠቃላይ ቢኒ የማላውቀውን የወንድም ፍቅር ያወኩበት ልጅ ነው። ይሄን ሰሞን እሱም ጥፍት ብሏል ምናልባት ተቀይሞኝ ይሆናል ቢሆንም አልፈርድበትም ካለን ቅርበት አንፃር እንዴት አልነገረችኝም ሊል ይችላል።

"ይቅርታ ህያብ ከራሴ ጋር ትንሽ ግጭት ውስጥ ነበርኩ ለዛ ነው ካንቺም ከክላስም የጠፋሁት" የእውነት አናዶኝ ነበር

"አንተ ሰው ያስባል ይጨነቃል እንኳን አትልም ግቢውን ለቀህ የት ሄደህ ነው" ትንሽ ካቅማማ በኋላ

"ቤተሰብ ጋ" አለኝ

"የት ድሬዳዋ.... እዛ ነበርክ"

"አዎ"

"ምነው ቤት ሰላም አይደሉም እንዴ"

"አይ ሰላም ናቸው። አሁን ለጠፋሁበት ራት በመጋበዝ እቀጣለሁ" ፈገግ እያለ እጁን ዘረጋልኝ

"ቅጣቱንማ የምወስነው እኔ ነኝ" ተንደርድሬ እቅፉ ውስጥ ገባሁ "የምር ናፍቀኸኝ ነበር ቢኒ ወንድሜ"

"እኔም ናፍቀሽኝ ነበር...
ተማሪማ ከዚህ የበለጠ ሊቀጣ አይችልም ሀሀሀሀ"

ቶሎ ቶሎ ለባብሼ ከዶርም ልወጣ ስል
"እንዲህ አምሮብሽ ወዴት ነው" አለችኝ ቤዛ። ዝም ብያት ልሄድ አልኩና እንደታረቅን ትዝ ሲለኝ "እራት ቀጠሮ አለብኝ ከተባልኩት ሰዓት አርፍጃለሁ" ፊቴን አዙሬ ልወጣ ስል

"ቆይ ቆይ እና እራት ተጋብዘሽ ነው እንደዚህ የለበሽው ነይ ሂዊ እኛ እናልብሳት" ወደኔ መጣችና ቦርሳዬን ተቀብላ ካስቀመጠችው በኋላ ልብስ እያነሰች ማማረጥ ጀመረች "ኧረ ቤዚ ረፍዶብኛል ደግሞኮ ፍቅረኛዬን ላገኝ አልሄድ ቢኒ እኮ ነው" ችኩል ብያለሁ ምክንያቱም ቢኒ ሲያስጠብቁት አይወድም

"ቢሆንም ፏ ዝንጥ ብለሽ ነው መሄድ ያለብሽ" በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ሌላ ሰው አስመሰሉኝ ራሴን በመስታወት ውስጥ ሳየው አምሮብኛል።

"አሁን መሄድ ትችያለሽ ሰላም ተመለሽ" ህይወት ጉንጬን ሳም አደረገችኝና በር ከፍታ አስወጣችኝ። ለኔ አዲስ ሰዎች ነው የሆኑብኝ ግን ከልባቸው እንደሆነ በደንብ ያስታውቃል።

"ይቅርታ ቢኒ ከወጣሁ በኋላ እኮ እነ ህይወት እንደዚ ለብሰሽ አትሄጂም ብለውኝ"

"ችግር የለውም ውዷ ብዙም አላስጠበቅሽኝም" ተያይዘን ከግቢ ወጣን በየጥጋጥጉ እንዲሁም በደንበኞች ጠረጴዛ ላይ የተቀመጡት የሻማ መብራቶች ለሆቴሉ ልዩ ውበት አጎናፅፈውታል። በአድናቆት ዙሪያ ገባውን እያየሁ አንድ አስተናጋጅ ወደኛ መጣና ለየት ብሎ ወደተዘጋጀ ጠረጴዛ እየመራ ወሰደን.... ከተቀመጥን በኋላ

"አንተ ምንድነው ነገሩን ሁሉ ሮማንስ አደረከው እኮ የምር ግራ እያጋባህኝ ነው ትልቅ ሆቴል መግባታችን ሲያስገርመኝ ጭራሽ.." የማወራውን ነገር ችላ ብሎ

"እባክህን ሜኑ አምጣልን" ግራ ገብቶኝ ዝም ብዬ አያየሁት ሜኑ እጄ ላይ አረፈ ተቀብዬ ስገልጠው የምታምር ትንሽዬ ቀይ አበባ ውስጡ ቁጭ ብላለች። ቀና ብዬ አስተናጋጁን አየሁት ቅልቅ ድንጋጤ.... አበባዋን አንስቶ አጠገቤ ብርክክ አለ

"ህያብ ያለፈ ታሪክሽ ምንም ይሁን ምን አንቺን ከማፍቀር ሊያቆመኝ አይችልም። የኔ ቆንጆ የፍቅር ጓደኛዬ ትሆኛለሽ?"

"ዮኒ.." ተርበተበትኩ... ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ፈገግ ብሎ እያዬን ነው.....

ይቀጥላል
3.5K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 21:00:01 #ህያብ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በኤርሚ

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

"እኔ ምንም እየገባኝ አይደለም ቢኒ ምንድነው እያወራህ ያለኸው"

"ተረጋጊ እነግርሻለሁ.... ዮናታን የያዝነው ክፍል ድረስ መጥቶ እንድናወራ ጠየቀኝ.... እሺ ብየው ተያይዘን ወደ ሆቴሉ ባር አመራን እናም ቁጭ ብለን ያልጠበኩትን ነገር ነገረኝ"

"ቀጥል ምን አለህ"

#ምሽት_8_ሰዓት_ላይ

የሆነውን ሁሉ እኔ ነኝ የምተርክላችሁ.... ቢኒያም

ከዮናታን ጋር ወደ ባሩ ከወረድን በኋላ መጠጥ አዘዘ እና
"የውልህ ቢኒያም ተረጋግተህ እንድትሰማኝና ከቻልክ እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ..."

"ለማንኛውም የምትለኝን ልስማህ" እስከዚህ ድረስ እንኳን አብሬው የመጣሁት ድጋሚ ካስተማረን F እንዳያስታቅፈኝ በሚል ፍራቻ ነው

"ሁሉም ሰው የሚያውቀው እኔ ሴት አተራማሽ እንደሆንኩ ነው። በእርግጥ እውነታም አለው ጥቂት ከማይባሉ ሴቶች ጋር ግንኙነት ነበረኝ ግን ነበር ነው ከ2 አመት በፊት በመጀመሪያ እይታ አንዲት ልጅ ልቤ ውስጥ ገባች። እናም ልክ ለሌሎቹ እንደሚሰማኝ ተራ ስሜት ነው ብዬ የነበረው ህይወቴን ለመቀጠል ሞከርኩ ግን እንደድሮው መሆን አቃተኝ። ለተወሰነ ጊዜ ስወዛገብ ከረምኩና ፍቅሬን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝና እሷን የኔ እንዴት እንደማደርግ ማሰብ ጀመርኩ።

ልጅቷ ኮስታራ እና የማያስቀርብ ፊት ነው ያላት ያለኝ አማራጭ አብራ ከምትማራቸው ሴቶች ስለሷ ሊነግረኝ የሚችል ሰው ፈልጌ መቅረብ ነበር እናም የትናዬትን ቀረብኳት...."

"ሰውዬ ስለምን እያወራህ ነው" እዚህ ጋ መምህር መሆኑን ረሳሁ

"ቢኒያም ለኔ ሁሉም ነገር የተገለፀልኝ ዛሬ ነው.... እና ከቻልክ ተረጋግተህ ስማኝ"

"ከየትናዬት ጋር ከተቀራረብን በኋላ በተደጋጋሚ ቢሮዬ እየጠራኋት ስለ ህያብ እንድትነግረኝ አደርጋት ነበር።"

"ምን እያልክ ነው እና ህያብን አንተም ታፈቅራታለህ" ማመን ከበደኝ

"አዎ ያውም በመጀመሪያ እይታ ነው ያንበረከከችኝ ለማንም ሴት እንደዚህ ሆኜ አላውቅም። የኔ ብትሆን ብዬ በምናቤ ስስላት የነበረችን ልጅ ነው በአካል ያገኘኋት"

"እሺ ከዛስ ምን ተፈጠረ"

" የትናዬት እንኳን ጠርቻት ሳልጠራትም እየመጣች ብዙ ነገር እንዳውቅ አደረገችኝ። የምትነግረኝ ነገሮች ግን ህያብን እንድቀርብ ሳይሆን እንድፈራ እና እንድሸሽ የሚያደርግ ነበር።"

"ምን ብላህ ነው"

"በመጀመሪያ ከሷ ጋር ኢለመንተሪ ጀምሮ አብረው እንደተማሩ እና እንደምትታየው ሳይሆን ውስጥ ውስጡን ወንድ አተራማሽ እንደሆነች ነገረችኝ። አላምንም ስላት በማስረጃ አረጋገጠችልኝ።"

"መቼ ነበር ያረጋገጠችልህ ማለቴ የት"

"ከአመት በፊት ካንተ ጓደኛ ጋር ቤርጎ ሲገቡ በአይኔ በብረቱ አየሁ እናም የምትለኝ እውነት እንደሆነ አረጋገጥኩ"

"የውልህ ዮናታን ያየኸው እውነት ነው ግን እንደምታስበው አይደለም። ጓደኛችን በሀይሉን ፍቅረኛው ከድታው ሌላ ሰው ጋር ሆነች እናም እሷን ማስቀናት እንደሚፈልግ ነገረን.... እኔም ለህያብ ነገርኳትና እምቢ ብትልም በግድ አሳመንኳት ከዛ ፍቅረኛው የምታይበትን ሁኔታ አመቻችተን አብረው ወደ ክፍል ሲገቡ እንድታያቸው አደረግን። ግን አንተ እዛ እንደነበርክ ማንም አላወቀም እንዴትስ ልትገኝ ቻልክ"

"የትናዬት ናት አላምንም ስላት 'ከቢኒያም ጋር ፍቅር ፍቅር እየተጫወተች የገዛ ጓደኛው ጋር ትማግጥበታለች' አለችኝ ማረጋገጥ ከፈለክ ብላ ወደዛ ቦታ ወሰደችኝ እና በአይኔ እንዳይ አደረገችን በሰዓቱ ራሴን መቆጣተር አቅቶኝ ነበር እናም እሱን ልደበድብ እሷን ልሰድብ ስራመድ የትናዬት አስቆመችኝ.... ከዛ በኋላ የምትለኝን ሁሉ አምናት ነበር እስከ ትላንትና ድረስ..... አሁን ግን ሁሉንም ከራሷ ከህያብ ነው ማረጋገጥ የምፈልገው"
ነገሩ ካሰብኩት ውጪ ሆነብኝ የትናዬት ተንኮለኛ ብትሆንም ይህን ያክል ርቃ ትሄዳለች ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"እሺ ሌላስ ምን ነገረችህ"

"አንተ ፍቅረኛዋ እንደሆንክ እና አዲስ አበባ ከሌላ የወለደቻት ልጅ እንዳለቻት"

"ምንድነው የምታወራው እኔ ከህያብ ጋር አብሬ ስለምታይ ፍቅረኛዋ ነው ብትል እሺ ግን ልጅ ከየት ፈጥራ ነው የነገረችህ...." ኪሱን በርብሮ የሆነ ፎቶ አወጣና እጄ ላይ አስቀመጠልኝ። ህያብ ልጅ አቅፋ.....

"ግን እኮ እህቷም ልትሆን ትችላለች" ካልኩ በኋላ ለእናቴም ለአባቴም አንድ ነኝ ብላ የነገረችኝ ትዝ አለኝ።

"አይደለችም ልጇ ነች ይሄን አረጋግጫለሁ ግን አንተ የምታውቅ ነበር የመሰለኝ"

"ኧረ በፍፁም ግራ እያጋባህኝ ነው" ፎቶውን ተቀብሎኝ ወደ ኪሱ ከተተና

"ቢሆንም ይሄ ጉዳዬ አይደለም.... ለሷ ያለኝን ፍቅር ያለፈ ታሪኳ ሊቀይረው አይችልም የሚያሳስበኝ የአሁኑ ነው..." ግንባሩን አሸት አሸት እያደረገ ትንሽ ከቆየ በኋላ

"ቢኒያም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እናም ሳትዋሽ መልስልኝ" አለኝ

"እሺ ጠይቀኝ"

"ከህያብ ጋር ፍቅረኛሞች ናችሁ?"

"አይደለንም" ፈገግ ሲል አየሁት

"እሺ ታፈቅራታለህ" ከንግግሩ እኩል ደነገጥኩ

"አይ አላፈቅራትም" መሬት ተንበርክኮ መሳም ነው የቀረው ደግሞ ደጋግሞ ፈጣሪን አመሰገነ... ሁኔታውን ሳይ የነገረኝ ሁሉ እውነት እንደሆነ ገባኝ።

"እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ"

"ጠይቀኝ" አለኝ በፈገግታ ተሞልቶ

"የትናዬት ፍቅረኛህ ካልሆነች ወይም የሆነ ግንኙነት ከሌላችሁ እንደዛ ተጠባብቃችሁ አንገትህን ስትስምህ...." ሳያስጨርሰኝ

"እሱ ለኔም የሚገርም አጋጣሚ ነበር። ህያብ እኛ ወደተቀመጥንበት ስትመጣ እኩል አየናት እናም የትናዬት ሳላስበው ጥምጥም ብላብኝ ሳመችኝ። ደንግጬ ስለነበር ላስቆማት አልቻልኩም ምን እያረግሽ ነው ብያት ዞር ስትልልኝ ህያብ ቆማ እያየችን ነው ወዲያው አንተ መተህ ወሰድካት"

"እንጂ ምንም አይነት ግንኙነት የላችሁም"

"ቢኖረን ለምን እዋሽሀለሁ"

ወደ ያዝነው ክፍል ከተመለስኩ በኋላ ረጅም ሰዓት ወስጄ ለማሰብ ሞከርኩ ከሁሉም አንድ ነገር ደጋግሞ አቃጨለብኝ.... "ህያብን ታፈቅራታለህ"

አዎ አፈቅራታለሁ አልኩ ጮክ ብዬ ልክ እንዳንተ መጀመሪያ ያየኋት ቀን ነው ልቤን የሰረቀችው ግን ምን ያደርጋል እሷ የምታፈቅረው አንተን.... ወዲያው በንግግሬ ደንግጬ ዝምም አልኩ ደግነቱ ከራሴ ውጪ የተናገርኩትን ማንም ሊሰማ አይችልም። ፍጥጥ እንዳልኩ ነጋ ግን ከራሴ ጋር ልስማማ አልቻልኩም እውነት ህያብ የሌላ ሰው ስትሆን ማዬት እችል ይሆን???
።።።
እኔ ነኝ ህያብ!
ፍንድቅድቅ ብያለሁ ከዚህ የበለጠ ምን ሊያስደስተኝ ይችላል በማፈቅረው ሰው መፈቅርን የመሰለ ምን ነገር አለ። ከነገረኝ ነገሮች ሁሉ ዮናታን ያፈቅርሻል የሚለው ሙሉ እኔን ተቆጣጥሮኛል።

"ህያብ ደስታሽን ላበላሽ ፈልጌ ሳይሆን እባክሽ ጥያቄዬን መልሽልኝ" ጮክ ብሎ ተናገረ

"ምን አልከኝ ቢኒ" በራሴ አለም ስዋዥቅ ምን እንዳለኝም አልሰማሁትም ነበር።

"ልጅ አለሽ" ከመደንገጤ የተነሳ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ።

"ህያብ እንደጓደኛሽ የምታይኝ ከሆነ እውነቱን ንገሪኝ ልጅ አለሽ" ከተቀመጠበት ተነስቶ እጄን ያዘና አንድቀመጥ አደረገኝ ከዛ በተማፅኖ አይን አይኔን ያይ ጀመር "እባክሽ ህያብ ላስጨንቅሽ ፈልጌ አይደለም... ግን ዮናታን ፎቶ ሲያሳየኝ ተጠራጠርኩ" የባሰ ድንጋጤ

"ምን? ዮናታንም ያውቃል"

"አዎ እሱ ነው የነገረኝ ስነግርሽ እኮ አልሰማሽኝም መሰለኝ"
3.0K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 19:48:41 የእናቴ ልጅ
  ክፍል ሃያ ሰባት

ያልጠበኩት ነገር ነበር የተፈጠረው ነገሩሁሉ ተምታታብኝ እናቴ የነገረችኝ የአባቴ ሁነታ እና እያየው ያለውት የተለየ ነው ።ሽማግሌው የኔ አባት ?ለማመን ተቸገርኩ ፡ እኛን ለማግኘት ያን ያክል ከባድ አልነበረም እንዴት ለሃያ ሦስት አመት ሳያየን ቆየ?
የት ነበር እስከዛሬ ለምን ሕይወቱን በዚ መልኩ ለመኖር ወሰነ የተሻለ ነገር ለማሰብ ለምን አልሞከረም ? አብታምና ምንም ነገር እንደማይሳነው አድርጋ ነበር እናቴ ስለ አባቴ የነገረችኝ ።አሁን የማየው ሰው ግን የተጎሳቆለ እና መንገድ ላይ ላስቲክ ወጥሮ የሚኖር የዋህ ሽማግሌ ነው ። ለምን አይምታታብኝ !
እናቴ በስንት ማባበል ጩኽቷንና ለቅሶዋን አቆመች እነባዩሽ አብረዋት አንብተው ዝም ስትል አብረው ዝም አሉ እኔግን ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ ለዛውም ቁጣን ያዘሉ ጥያቄዎች ። አቤል የሚገባበት ቀዳዳ የሚፈልግ ነው የሚመስለው ፡ሽማግሌው አባታችን መሆኑን ካወቀ ሰአት አንስቶ ምንም አይነት ነገር አልተናገረም ነገርግን ለአንዴ እንኳ ቀና አላለም አንገቱን እንደደፋ ነው ፊቱላይ ያለውን ለውጥ ለማየት እንኳ አልቻልኩም ።  እናቴ በቀስታ "ለምን?"ስትል ሰማዋት ።የኔም ጥያቄ ስለነበር ወደ ሽማግሌው አባቴ ዞርኩ
"ለምን ?ለምንድነው እስከዛሬ ድረስ በሕይወት እያለህ አንዴ እንኳን ተሳስተህ መጥተህ ያላየኽን ? እኛ ለማግኘት እንደማይከብድህ እርግጠኛ ነኝ !እንኳን አንተ ቀርቶ አክስቴ ደግነሽ እንኳ የቀድሞ ሰራተኛህን አግኝታ ያለንበትን አውቃ መጥታለች ። እና አንተስ ? "ብዬ ዝም አልኩ ።እናቴም ቀና ብላ መልሱን ጠበቀች ።
"ይቅርታ አድርጉልኝ እኔ ለእናንተ የምገባ ሰው አይደለውም ጥሩ ሰው አልነበርኩም ።በተለይ ለባለቤቴ ዘውድነሽ አልገባትም ነበር እሷ የዋሕና ገና ታዳጊ ልጅ ነበረች በዛች ትንሽዬ ልጅ ላይ የሕይወትን ሸክም አሸክሜያታለው።  ግን እንደዛ መሆን ነበረበት እንደሱ ባላደርግ ኖሮ ሁላችሁንም በኔ የተነሳ ያጠፏቹ ነበር ። ጓደኞቼ ካልኳቸው ሰዎች ጋር በድንገት በተፈጠረ አለመግባባት ተቃቅረን ነበር ሲያጣላን የነበረው ደሞ በጋራ የሰራነው ስራ ነበር ስራው እገወጥ ነው  ስራውን ሰርተን ስንጨርስ በምንከፋፈለው ድርሻ ምክንያት አለመስማማት ተፈጠረ  እቃውን ያስገባውት እኔነኝ  ነገርግን በስራው ላይ አነስተኛ ድርሻ የነበራቸው ሰዎች እኩል ክፍፍል ሲፈልጉ አይገባችሁም አልኳቸው ፡በወቅቱ የኔን አቅም ስለሚያውቁ የተስማሙ መሰሉ ።በዋላ ላይ ግን በሴራ ጠልፈው ሊጥሉኝ ተስማሙ ፡ከዛ ባላደረኩት ነገር እንድከሰስ አደረጉኝ ፡  ከዛ ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳላገኝ አዋከቡኝ ይህን ልቋቋም አልቻልኩም ክሴን እየተከታተልኩ ። እነሱን ደሞ በሌላ መልኩ ልበቀላቸው ወጥመድ መዘርጋት ጀመርኩ ፡ እና ይህን ፍላጎቴን ለማሳካት ደሞ እናታችሁን እና እናንተን እንዳይነኩብኝ ማራቅ ነበረብኝ ።እናንተ እንዳትቸገሩ ያለኝን በሙሉ ለዘውድነሽ አስተላለፍኩ ቤት ገዛው  ።ምክንያቱም እናንተ ለኔ አይኖቼ ነበራቹ ስጦታዎቼ ....."ብለው ዝም አሉ እኔ ደሞ እገወጥ ስራ ስላሉ ደስ የሚል ስሜት አልተሰማኝም ፡በዛላይ እነዛን ጓደኞቻቸውን ምን አድርገዋቸው ነው ብዬ ተሰቀቅኩ ።የወንጀለኛ ልጅ መሆን ይከብዳል
"እሺ አሳጥረው የት እንደነበሩ ይንገሩን "አልኩ
"ከዛማ እነሱን ለመበቀል የኔን ሰዎች አሰማራው ነገር ግን ሳይሆን ቀረ እኔ አንድ ጉዳት ከማድረሴ በፊት ከኔ የሆነሰው ለነሱ የሚወግን ሆኖ ተገኝቶ እኔን ከዳኝ እናም  ። በላሰብኩት ሁኔታ አሳልፎ ሰጠኝ እነሱም ያልሰራውትን ሁሉ እንደሰራው አድርገው ከሰሱኝ በወቅቱ የነበሩት ከፍተኛ ቦታላይ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በገንዘብ ገዝተው ኖሮ ።በጮህ ብለፈልፍ ሰሚ አጣው እና በቁጥጥር ስር አዋሉኝ ። ከዛ በዋላ እስርቤት ወረወሩኝ ያለምንም ፍርድ ለሃያ አመት እዛው ነበርኩ ፡ልጄ ቅስሜ ሁሉ ተሰባብሮ ።ሰው መሆኔን እስክጠላ ነበር ጉዳዩ  ።ብቻ እንደው ስለጠየከኝ እንጂ ማውራትም አልፈልግም ነበር ባጭሩ ግን ለሃያ አመት ያለፍርድ ታስሬ አለው ስፈታ ወደ እናንተ ነበር የመጣውት ግን ከፍለጋ በዋላ የዘውድነሽን አድራሻ ባውቅም ግን ወደእናንተ መቅረብ አቃተኝ ለምን እንደው ፈራው  "አሉ አይናቸውን ሰበር አድርገው ። ድጋሚ ሌላ ጥያቄ ልጠይቃቸው ልናገርስል ስልኬ ጮኽ ብሌን ነበረች
"ሃሉ "አልኩኝ ለምን በፍጥነትእንዳነሳውት ለራሴም ገረመኝ ምን አልባት ዛሬ የሕይወቴ ፍፃሜ ሊሆን ስለነበር ከሷ መለየቴን ፈርቼው ነበር
"ናቲ የኔውድ ሰላም ነህ በጣም ፈርቻለው"አለች
"ምነው ብሌኔ ደና ነኝ ለምንፈራሽ "አልኳት
"እኔ እንጃ ብቻ በጊዜ ነበር የተኛውት እና ደስ የማይል ህልም አየው ስለ አንተ ደና ነህ አይደል እኔ በህልም ምናምን አላምንም ግን ይሄ ያስፈራል "አለች
"ደና ነኝ ብሌኔ ህልም ህልም በይ በቃ "አልኳት ሳላስበው አቃሰትኩ ። ጭንቅላቴን አመም አደረገኝ
"ምንድነው እየዋሸህ ነው አይደል አንድ ነገር ሆነሃል ?መጣው በቃ "አለች ።
"አይ አይ እኔ ....."ስል ስልኩን ዘጋችብኝ ደግሜ ስደውል ይዘጋል ስልኩ ።ተናደድኩ እንዲ ሆኜ እንድታየኝ አልፈለኩም ።በዛ ላይ የአባቴን ታሪክ እውነተኛውን በትክክል ለመስማት ፈልጌያለው ገና የአቤልም ጉዳይ አልተቋጨም ።ብሌን ተጨማሪ ጭንቀት እንድትሆንብኝ አልፈለኩም ።እሷን ደሞ ንነዲነው እንዲያነው እያሉ ለማስረዳት ተጨማሪ አቅም ከየት ላምጣ ።ጭንቅንቅ ስል እናቴ አይታ ።ወደአቤል በመዞር ወደመኝታ ክፍል እንዲገባ ጠቆመችው ፍፁም ተኮሳትራ ነበር ።አባታችን ግን የትም አይሄድም ብሎ ያዘው .......
የአቤል አይን ተቁለጨለጨ ወደሄትም ማምለጥ እንደማይችል ገባው ከአባታችን ጋር ተፋጠጠ.......


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
3.1K viewsTsiyon Beyene, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 11:42:14 "ህያብ ፊቴን አንብበሽ መረዳት ከቻልሽ እባክሽ አሁን ምንም ማውራት አልፈልግም.... እና ካወራሁም በጣም አስከፋሻለሁ ስለዚህ እኔም ተረጋግቼ አንቺም እረፍት አድርገሽ የተለመደው ቦታ ዘጠኝ ሰዓት እንገናኝ... ቻው" መልሴን ሳይጠብቅ ትቶኝ ሄደ። ግራ እንደተጋባሁ ዶርም ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ግን እንቅልፍ ከየት አባቱ ወደ ግራ ወደቀኝ እየተገላበጥኩ አሰብኩ.... አሰብኩ.... አሰብኩ... ግን ትላንትና ማታ ምን እንደተፈጠረ ማስታወስ አቃተኝ

ከቀጠሯችን አስር ደቂቃ ቀድሜ ተገኘሁ... ብዙም አላስጠበቀኝም። እንደመጣ

"በናትህ ቢኒ እኔ ምንም ማስታወስ አልቻልኩም የቀጠሯችን ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ሳልተኛ ብዙ አሰብኩ ግን ምንም ትዝ አይለኝም"

"የእውነት ምንም አታስታውሺም"

" እነሱን አይቼ ተናድጄ ካንተ ጋር እየጠጣሁ ነበር ከዛ እነሱ ወደተቀመጡበት እንደሄድኩ ትዝ ይለኛል ከዛ ውጪ አዎ ምንም አላስታውስም"

"እሺ ጥሩ እንደዛ ከሆነ እኔ ላስታውስሻ....
በጣም ሰክረሽ ነበር ጠርሙሱን ቀምቼሽ ወደ ዶርም እንሂድ ስልሽ  አልሰማሺኝም ተቀብለሽኝ እየተንገዳገድሽ ዮናታንና የትናዬት ወደተቀመጡበት ቦታ ሄድሽ። ሁኔታሽ ስላላማረኝ ተከተልኩሽ... ከዮናታን ውጪ ማንም አልነበረም እናም አንዴ እየሳቅሽ ሲልሽ እያለቀሽ እንዴት እንደምትወጂው ለእናትሽና ለአላማሽ ብለሽ ከሱ እንደራቅሽ ነግረሽው የየትናዬትን ተንኮል እየነገርሺው እያለ ከየት መጣች ሳትባል ፀጉርሺን ጨምድዳ ይዛ በጥፊ መሬት አነጠፈችሽ..."

"ምን ጭራሽ ተደባድቤም ነበር" አሁን የተመታሁ ይመስል ጉንጬን በእጄ ዳበስኩት

"አዎ.... ያም ብቻ ሳይሆን በወደቅሽበት ትንሽ መታሻለች... ብዙም ሳይቆይ ሰዎች አገላገሏችሁ እና እኔ አንቺን ይዤሽ ከዛ ወጣን እና አልጋ ፈልጌ ያዝኩ አንቺን አስተኝቼሽ ትንሽ ቆዬት እንዳልኩ የክፍሉ በር ተንኳኳ ሄጄ ስከፍት ዮናታን በር ላይ ቆሟል..."

"ምን...... ማለት ለምን ነበር የመጣው" ወይኔ ነገሩን ሀሉ በአንድ ቀን ስካር አበላሸሁት ማለት ነው። ቢኒ ለመናገር ሲታሽ አየሁት

"ምንድነው እሱ ቢኒ ንገረኝ እንጂ..."

"ይሄ እኔን ይጎዳኝ ይሆናል አንቺን ስለሚጠቅምሽ ግን ልንገርሽ"ለአፍታ ዝምምም አለ

"ምን ቢኒ" ልቤ ስቅል አለ

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

ይቀጥላል
3.6K viewsአትሮኖስ, 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 11:42:14 #ህያብ
:
:
#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በኤርሚ


አንዳንዶች ለወደዱት ብቻ ጥሩ ይሆናሉ.... አንዳንዶች ደግሞ እንዲሁ በተፈጥሯቸው ጥሩነትን ይታደሉታል። ቢኒ እንደዛ ነው መልካምነትን የታደለ ጥሩ ልብ ያለው ልጅ ነው። ድሀ ወይም ሀብታም፣ ክርስቲያን  ሙስሊም ወይም ሌላ እምነት፣ ቆንጆ ወይም መልከ ጥፉ፣ ቢኒ ጋር መስፈርት አይደሉም። ለሁሉም እኩል ፍቅርና እንክብካቤ ሲሰጥ ታዩታላችሁ..... ግቢ ውስጥም ሆነ ከተማ ውስጥ ያሉ የበጎ አድራጎት ስራዎች አያመልጡትም.....

"ቢኒዬ ግን እርግጠኛ ነህ እዚህ ብሆን አረብሽህም.." እረጅም ሰዓት ተጨቃጭቀን እስከፈለኩ ድረስ ቤቱ እንድኖር ከነገረኝ በኋላ ሀሳቡን ቢቀይር ብዬ ጠየኩት

አጠገቤ መጣና ቁጭ አለ.... እጆቹን ልኮ ሁለት እጆቼን ያዘና አይን አይኔን እያዬ "ህዩ አንቺ ጓደኛዬ ነሽ... ጓደኝነት ውስጥ ደግሞ እኔ የሚባል ነገር የለም በተለይ እኔ ካንቺ እኔን ላስቀድም አልችልም ምክንያቱም......" ከንፈሮቹ ተንቀጠቀጡ።

"ምክንያቱም ምን ቢኒዬ" እጄን ለቆ ተነሳና ጀርባውን ሰቶኝ ከመስኮት ዳር ቆመ።

"ህያብ ጊዜ የነገሮች ጌታ ነው ብዬ አምናለሁ... እናም ሁሉም በጊዜው ሲሆን ደስ ይላል። አሁን ከኔ ምክንያት በላይ ያንቺ ሁኔታዎች ናቸው መስተካከል ያለባቸው...." ክትክት ብዬ ሳቅሁ... የእብደት ሳቅ
ከሳቄ በኋላ

" እስኪ ንገረኝ ምኑን ነው የምታስተካክለው.... እናቴን ልጄን ወይስ ከሀዲው ባሌን ማንን መልሰህ ልታመጣልኝ የምትችል ይመስልሀል..." ድጋሚ አመመኝ... መቋቋም አቃተኝ... በሁለት እጄ ጭንቅላቴን ጥፍንግ አድርጌ ያዝኩት። የሆነ ሽክርክሪት ውስጥ እንዳለሁ ይሰማኛል ዥውውውውውውውው.... ሳቅ ከዛ ደግሞ ዝምምምምታ.... ከዛ ደግሞ ሌላ ሳቅ.... ይሄኛው አለም የተሻለ ይመስለኛል።

የሆነ ሰው አፌ ውስጥ የሆነ ነገር ለማስገባት ታገለኝ አልከለከልኩትም ዋጥኩት ከዛ ሁሉም ነገር ፀጥ አለ።

ምን ሰዓት እንደተኛሁ ባላውቅም ራሴን ጋቢ ለብሼ ሶፋ ላይ ተኝቼ አገኘሁት። ቀና ብዬ ተስተካክዬ ቁጭ ስል ቢኒን ከእግሬ ስር ቁጭ ብሎ መፅሀፍ ቅዱስ ሲያነብ አየሁት።

"ይቅርታ ቢኒ ረበሽኩህ መሰለኝ.." መፅሀፍ ቅዱሱን ዘግቶ ከሳመ በኋላ የኔንም ግንባር ነካ አደረገበትና ተነስቶ አስቀምጦ ተመለሰ።

"ሁለተኛ እንደዚህ እንዳትይኝ ማስቸገር ገለመሌ የሚባል ታሪክ የለም ያራቅሺኝ ነው የሚመስለኝ..."

"እሺ በቃ አይለመደኝም..... ይልቅ እስኪ ንገረኝ የውጪ ቆይታህ እንዴት ነበር የተመለስከውስ መች ነው"

"ቆይታዬን በደፈናው ጥሩ ነበር ልበልሽ መሰለኝ። የተመለስኩት ሁለት ወር አካባቢ ሆነኝ ግን ቀጥታ ቤተሰብ ጋር ክፍለ ሀገር ነው የሄድኩት ከተመለስኩ ገና ሳምንትም አልሞላኝ"

"እና ለምን ልትፈልገኝ ወደ ቤት አልመጣህም..." ክፍት ነው ያለኝ ምንም እንኳን የሱን ስም ሲሰማ ባሌ ቢናደድም ቢኒ ላጣው የማልፈልገው ጓደኛዬ ነው እና እንዴት...

"ወዳንቺ ጋር እየመጣሁ እያለ እኮ ነው መኪና ውስጥ የገባሽብኝ"

"ኦ እሺ እንደዛ ከሆነ"

"አልተዋጠልሽም አይደል ህያቤ ብዙ ጊዜ እንዳልደወልኩልሽ አውቃ..." አቋረጥኩት

"ምን ብዙ ጊዜ ትላለህ ከሄድክ ጀምሮ ሁለቴ ብቻ እኮ ነው የደወልከው.... እናም አልዋሽህም ተቀይሜሀለሁ"

"ምክንያቴን ስታውቂ እንደምትረጂኝ ስለማውቅ ችግር የለውም.... የሆነ ነገር መብላት አለብን ምን ትፈልጊያለሽ..." አለኝ ወደ ኪቺን እየገባ

"ፍላጎትሽን አትናገሪም ካለዛ ዱባ ወጥ ነው የምሰራው ሀ ሀ ሀ" ሽርጡን አገልድሞ ብቅ አለ

" ዱባ ስራና ሶስት ቀን ውጪ አሳድሬ ነው የማበላህ.... አንተ ደግሞ ሼፍ መስለህ የለም እንዴ"

"ነይ አሁን ተነሺ ቢያንስ ዱባውን እንኳን በመክተፍ አግዢኝ" ከስሙ ጭምር እንደምጠላው ስለሚያውቅ እኮ ነው ...ዱባን....

"ሀ ሀ ሀ አንተ እብድ ትቀልድብኛለህ አ" ከረጅም ጊዜ በኋላ ሳቅሁ
......

፨፨፨ ፨፨፨፨ ፨፨፨፨
ጎንደር ዩንቨርስቲ ሁለተኛ አመት

"ቢኒ ዮናታንን እወደዋለሁ ከዚህ በላይ መቋቋም አልችልም እናም እነግረዋለሁ"

"ህያብ ዮናታንን ታውቂዋለሽ.... እሺ አለሽ እንበል ከዛ እነኝህን ሁሉ ሴቶች ትቶ ካንቺ ጋር ብቻ የሚሆን ይመስልሻል"

"አላውቅም ግን እድሌን ልሞክር.."

"ተይ ህያብ ይቅርብሽ"

"አይሆንም ቢኒ እድሌን እሞክራለሁ" ይሄን ሁሉ የምንጨቃጨቀው ዮናታን የሚያመሽበት ጭፈራ ቤት በር ላይ ሆነን ነው። ወደ ውስጥ ገባሁ... አይኔን ዞር ዞር እያደረኩ ፈለኩት ጥግ ሶፋ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር የተሰፋ ያክል ተጣብቋል.... በደንብ ቀረብኳቸው... አንገቱ ስር ስማው ቀና ስትል አይን ለአይን ተገጣጠምን... የትናዬት....

ደንዝዤ አንደቆምኩ የሆነ ሰው እጅ ትከሻዬ ላይ አረፈ "የኔ ቆንጆ በዛኛው በኩል ቦታ አግኝቻለሁ.... እንሂድ አይደል"  ውጪ ቆይ አላልኩትም ነበር.... ቢሆንም ግን ወሳኝ ሰዓት ላይ ነው የደረሰው።

"አየሽ አይደል በራስሽ ላይ ምን እያመጣሽ እንደሆነ"

ሲጀመር እሱን ብቻውን አገኘዋለሁ ብዬ ማሰቤ ነው የኔ ጥፋት እርር ድብን ብሽቅቅቅቅ ብያለሁ እኮ

"አረጋጊው እንጂ ውዷ ጉበትሽን መትፋት አማረሽ እንዴ"

"ተወኝ ባክህ ልጠጣበ" ከነ ጠርሙሱ አንስቼ ለመጠጣት ስሞክር ከእጄ ቀማኝና

"ነይ በቃ እንሂድ ግቢ ይዘጋል" አለኝ

"የትም አልሄድም ተወኝ"

"ይሄንን ነው መፍራት... ኧረ ህያብ በፈጠረሽ..." ጠርሙሱን ተቀብዬው እየተንገዳገድኩ እነሱ ወዳሉበት ቦታ ሄድኩ....

"ህያብ አንቺ ህያብ" የእናቴ ድምፅ መሰለኝ.... እየጠራችኝ ነው።

"አቤት እማ መጣሁ" ብዬ ከተኛሁበት ለመነሳት ስሞክር ሀይለኛ ራስ ምታት አናቴን ይዞ እየፈለጠኝ ነው። ጭንቅላቴን በሁለት እጄ ጥፍንግ አድርጌ ይዤው ከቆየሁ በኋላ አይኔን በደንብ ከፍቼ ሳይ ያለሁት እናቴ ቤት አይደለም....

ከፊት ለፊቴ ቢኒ ተቀምጦ የማደርገውን ነገር ያያል።

"ኡፍፍፍፍ የት ነው ያለሁት ምን ተፈጥሮ ነው.... ቆይ እማዬ የጠራችኝ አልመሰለኝም.."

"ባክሽ እኔ ነኝ የጠራሁሽ ክፍል ልቀቁ እየተባልን ነው ተነሺ..." ቢኒ እንደዚህ አውርቶኝ አያውቅም....

"ምንድነው ቢኒ ችግር አለ እየተነጫነጭክ እኮ ነው ምነው ማታ አስቀየምኩህ እንዴ.... ማታ....ቆይ ቆይ እንዴት ወደዚህ ልመጣ ቻልኩ? ማነው ያመጣኝ? ማለት ምን ተፈጥሮ ነው?..." የጥያቄ መአት አከታተልኩበት

"በመጀመሪያ ተነሽና ታጠቢ ከዛ ወደ ግቢ እንመለስና ዶርም ገብተሽ እረፍት አድርጊ ከዛ ተገናኝተን ጥያቄዎችሽን እመልስልሻለሁ እስከዛው ትዝ የሚልሽ ነገር ካለ ራስሽ ጥያቄሽን መመለስ ትችያለሽ" እንዴ ምንድነው ጉዱ ቢኒ እንደዚ ከረር ብሎ አይቼው አላውቅም ጭራሽ የማላውቀው ሰው ነው የሆነብኝ። ተጨማሪ ጥያቄ ሳልጠይቅ ጭንቅላቴን ደግፌ እየተጎተትኩ መታጠቢያ ቤት ገባሁ።
ሰውነቴ ስብርብር ያለ ያክል እየተሰማኝ ታጥቤ ጨረስኩ

፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨

"አንተ ቢኒ ግን አልተኛህም እንዴ አይንህ እኮ በርበሬ ነው የሚመስለው" ወደ ግቢ እየሄድን ጠየኩት
3.7K viewsአትሮኖስ, 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ