Get Mystery Box with random crypto!

አትሮኖስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የሰርጥ አድራሻ: @atronosee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 159.61K
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።
Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-21 12:37:27 ትንሽ አረፍ በልና ስድስት ሰዓት ወደሳሎን ና ….ሁሉም አንተን ነው ሚጠብቁት፡፡ "አለውና ወጥቶ ሊሄድ በራፍ አካባቢ ከደረሰ በኃላ ወደኃላ ዞር በማለት"ስትመጣ እዛ ቀይ ፔስታል ውስጥ ያለውን ዕቃ ይዘሀው ና..ለልጆቹ ስጦታ ነው።እንዲህ አይነት ነገር ስለለመድ ትሠጣቸዋለህ…ላንተ ልብስ ቁም ሳጥኑ ውስጥ አለልህ…ሳይዝህን በትክክል ስለማላውቅ በግምት ነው የተገዛው..ግን ከውስጡ የሚሆንህ አይጠፋም ብዬ እስባለሁ…በል እንጠብቅሀለን" ብሎት ክፉሉን ሙሉ በሙሉ ለቆ ወጣና ከውጭ ዘግቶለት ሄደ፡፡መንግስቱ የግራ መጋባቱ መጠን በጣም ከፍተኛ ስለነበረ ድክምክም አለው።አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለና መኝታ ቤትህ  ነው የተባለውን   ክፍል እንደ አዲስ አይኖቹን እያዘዋወረ መቃኘት ጀመረ፡፡


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
8.3K viewsTsiyon Beyene, 09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 12:37:26 አሮራ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _4
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
መንግስቱ እግሩን አንቀሰቀሰና ወደ መኪናዋ ፈራ ተባ  በሚል እርምጃ ማዝገም ጀመረ….ከመድረሱ በፊት ገቢናው ተከፈተና አንድ ሰው ከውስጥ ተመዞ ወጣ፡፡እንደእሱ ግዙፍና ፈርጣማ ነው፡፡ፈገግ እያለ ወደእሱ መራመድ ጀመረ….ፈፅሞ አይደለም ከእስር ቤት በወጣ በመጀመሪያው ቀን ይቅርና እድሜ ልክም ዳግመኛ አየዋለሁ ብሎ ያልጠበቀው ሰው ነው፡፡አጎቱ፡፡፡የአባቱ  ታናሽ ወንድም።

"በፈጣሪ ይሄ ሰይጣን ሰውዬ ከየት መጣ?››ብሎ  በውስጡ አጉረመረመ፡፡

አጎቱ ወደእሱ መጓዝ ጀምሯል ...መሀከል መንገድ ላይ ተገናኙ ….እላዩ ላይ ተጠመጠበት።በመንሰፍሰፍ እንደናፈቀው የገዛ ልጁ እያገላበጠ ጉንጮቹን ሳመው፡፡ያለምንም ተቃውሞ እንዳደረገው ሆነለት፡፡እንደዛ መሆን ፈልጎ ሳይሆን እየሆነ ያለው ነገር ፈፅሞ ያልጠበቀውና ያልተዘጋጀበት ስለሆነ ምንም አይነት የተቃውሞም ሆነ የትብብር እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻለም።….

"አንተ በጣም ትልቅ ሰው ሆነህ የለ እንዴ?እንዴ…. ይገርማል..ለማንኛውም ስለተፈታህ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡"አለና እጅን  ትከሻው  ላይ ጣል አድርጎ  አቅፎት ወደ መኪናው ይዞት ሄደ፡፡ወደመኪናው ሲጠጋ ቀድማ እጆቾን በመኪናው መስታወት አውጥታ እያውለበለበች ስትጠራው የነበረች ሴት መኪናውን ለቃ ወረደች፡፡

"ተዋወቃት ባለቤቴ ነች፡፡"

ለስላሳ እጆን ዘርግታ አይኖቾን እላዩ  ላይ  እያንከባለለች፡፡" ውቢት  እባላለሁ፡፡›"አለችው ።ጨበጣትና "መንግስቱ " አላት፡፡
አጎቱ ሻንጣውን ተቀበለና ከኃላውን በራፍ ከፍቶ ከስቀመጠ በኃላ" በሉ ግቡ እንሂድ"አላቸው።
መንግስቱ  የኃላውን በር ሲከፍት‹‹እስኪ ገቢና ከጎኔ ሁን ››አለው፡፡ሚስቱ ወደነበረችበት የኃላ ወንበር ተመልሳ ስትገባ እሱ አጎቱ እንዳለው ዞረና ፊትለፊት ገቢና ገባ ፡፡መኪናዋ ተንቀሳቀሰች፡፡

"ሶስት አመት ስታሰር አንድ ቀን ታሳስቶ እንኳን ያልጠየቀኝ ዛሬ እንዴት ፈለገኝ..?የመፈቻ ቀኔንስ እንዴት አወቀው…..?ወዴት ነው እየወሰደኝ ያለው?፡፡››በውስጡ የተተረማመሱ ካሉ ጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹ ነበሩ…..።ትንሽም የተረጋጋው ሚስቴ ነች ያላት ሴት አብራው ስላላች እንጂ ብቻውን መጥቶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የከፋ ጥርጣሬ በውስጡ ይፈጠር ነገር "ሊያስገድለው ቢሆንስ?"ገንዘብ በጣም እንደሚወድ ያውቃል…ሀብታ ለመሆን የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ ከዚህ በፊት ደጋግሞ አሳይቶታል።የገዛ አባቱ ላይ ብዙ ብዙ ግፍ ሰርቶበታል…..።መአት ብር ከድቶታል….።በዚህም ምክንያት አባቱ ህመምተኛ እንዲሆን ምክንያት ሆኖል ….ህመሙ ደግሞ ወደሞቱ ሸኘቶታል፡፡ያ ማለት በተዘዋዋሪ ይሄ ከጎኑ የተቀመጠው አጎት ተብዬው ሰው የአባቱ ገዳይ ነው፡፡፡እና ዛሬም የሆነ ጥቅም የሚያስገኝለት ከሆነ እሱንም ከማስገደል ወደኃላ እንደማይል እርግጠኛ ነው፡፡፡"ግን እኔን ቢያስገድል ምን ይጠቀማል;?"ብሎ እራሱን ጠየቀ፡፡ከወላጆቹ የወረሰውን ቤት፡፡አዎ ወደደውም ጠላውም…ቀረቤታ ኖረቻውም አልኖራቸውም በአሁኑ ዘንድ በዝምድና ሰንሰለት ለእሱ ከዚህ ከጎኑ ከተቀመጠው ሰውዬ የሚቀርበው ሰው የለም፡፡ስለዚህ እሱ አንድ ነገር ቢሆን   ከወላጀቹ የወረሰውን ቤት ይገባኛል ብለው ከፊት ከሚሰለፉ ሰዎች ዋነኛው ምንአልባትም ብቸኛው ይሄ ሰው ነው፡፡

"ምነው ሀሳብ ውስጥ ገባህሳ…?.አሁን እኮ ሁሉ ነገር አልፏል….መከራዎቹን ሁሉ ከኃላ ጥለሀቸው ወጥተሀል….ይሄንን የነጻነት አየር ተንፍስ››አለው፡፡

"ለጊዜው ምንም አይነት የነፃነት አይር ወደ ውስጤ እየገባ አይደለም….እንደውም መታፈን ነው እየተሰማኝ ያለው።››ሲል መለሠለት።
አይዞኝ ….እስክትለምደው ነው…..ከአንድ ሁለት ቀን በኃላ ሁሉን ነገር አሪፍ ይሆንልህና ማጣጣም ትጀምራለህ… እኔ አጎትህ እንደዛ አይነት የመታፈን ስሜት አንዲሰማህ አላደርግም..እርግጥ በውስጥህ ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ አውቃለሁ….ግን አታስብ ቀስ በቀስ ጥያቄዎችህን ሁሉ እመልስልሀለው….አሁን እቤት ደርሰናል፡፡ቤተሰቡ ሁላ እየጠበቁህ ነው፡፡ልጀቼን አጎታችሁ ከመቀሌ እየመጣ ነው ነው ያልኮቸው።››ሲል ያልጠበቀውን ሌላ ነገር ነገረው።

"ለምን ዋሸሀቸው?››

‹‹ልጆቼ ከእስር ቤት ነው የወጣው ብላቸው….ብዙ ብዙ ጥያቄ ይጠይቁሀል…ምን አልባት እነዛን ጥያቄዎች ለመመለስ አትፈልግም ይሆናል ብዬ አሰብኩ..እናም ለዛ ነው እውነቱን ያልነገርኳቸው።››

"ምን …አንተም ሴት ደፍሮ ነወ የታሰረው ብለህ ታስባለህ እንዴ?"

"አረ በፍፁም….ግን ያው ሆነም ቀረም በሴት ጉዳይ አይደል የታሰርከው፡፡"

"በሴት ጉዳይ አይደለም…በአሮራ ጉዳይ ነው……አሮራ ፍቅሬ ነች ..አሮራ ህይወቴ ነች….ለእሷ ደጋግሜ እታሰርላታለሁ፡፡አባቶ ከእሷ ሊያርቀኝ ሲፈልግ ብሩን ተጠቅሞ የፈጣራ ወንጀል አዘጋጀና ልጄን ሊደፍራት ብሎ ዘብጥያ አስወረወረኝ…..እኔ ግን አሮራን የምደፍርበት ምንም ምክንያት የለኝም….አሮራ እኮ የእኔ ነች..ማለት ውስጤ ነች ፣ልቤውስጥና  ሰርጋ ከነፍሴ ጭምር ተዳብላለች..እራሴን  ሆናለች…ሰው ቢፈልግስ እራሱን እንዴት ሊደፍር ይችላል….?"

"ይቅርታ በወቅቱ ልደርስልህና ከጎንህ ቆሜ ልታገልልህ ባለመቻሌ በጣም ነው የሚቆጨኝ..ግን ሀገር ውስጥ አልነበርኩም ከመጣሁ በኃላ እራሱ  ሁሉ ነገር ከረፈደ በኃላ ነው ስለተፈጠረው ነገር የሰማሁት ..አይዞኝ እክስሀለው፡፡"

"ችግር የለም….በሆነው ነገር ምንም ቅሬታ የለኝም….ግን ከመቀሌ እንደመጣሁ ለምን ነገርካቸው..ማለቴ ከጎንደር ወይም ከሀዋሳ ለምን አላልካቸውም?››ሲል የገረመውን ነገር ጠየቀው፡፡

"አይ  ዩኒቨርሲት የተማርከው መቀሌ ስለሆነ ስለከተማዋ በጣም ታውቃለህ..ምንም ነገር ቢጠይቁህ ሳትጨናነቅ ታስረዳቸዋለህ ...ለዛ ብዬ ነው መቀሌ ያልኳቸው፡፡"

"ጥሩ ነው…..ስለእኔ ይሄን ያህል ማወቅህ አስገርሞኛል።››አለው በዚህን ጊዜ የመኪናዋ የቤታቸው የውጭ አጥር ጋር ደርሳ ክላክስ እያስጮኸች ነበር፡፡

ዘበኛው በራፉን ሲከፍት የቤቱ በረንዳ ሁሉ በሰው ተሞልቶ ነበር…ሁለት መንታ የሚመስሉ ዕድሜያቸው በ15 እና በ16 መካከል ያለ የሚመስል ሴቶች እያተንደረደሩ መጥተው ተጠመጠሙበት..እንዷ ግራ ጉንጪን ስትስም ሌላዋ ቀኝ ጉንጩን ትስመው ነበር….

ምን እየተካሄደ እንዳለ በትክክል መረዳት አልቻለም….ይሄ ሰውዬ የፊልም ዳሬክተር ሆኖ ይሆን እንዴ…?.የሆነ ሪያሊቲ ሾ እየሰራ ያለ ነው የመሰለው፡፡እነዚህን ልጆች አምሰት ወይም ስድስት አመታቸው ላይ አንድ ሁለቴ  እንሱ ቤት መጥተው  ስለነበረ  ትንሽ ትንሽ ትዝ ይሉታል…..ጭራሽ ሳያያቸው ግን አስር አመታት አልፎታል፡፡እነሱ ደግሞ በዛን ወቅት ህፃን ስለነበሩ ሊያስታውሱት እንደማይችሉ እርግጠኛ ነው..ታዲያ ይሄ ሁሉ የናፍቆት የሚመስል የደመቀ አቀባበል ከየት የመጣ ነው?፡፡ደግሞም ምኑም አርቴፊሻል አይመስልም
"እነዚህ ልጆች የዘመድ ረሀብ አለባቸው ይሆን እንዴ?"ሲል በውስጡ አጉረመረመ።

አጎትዬው ሻንጣውን በእጁ አንጠልጥሎ ወደእሱ በመምጣት ከልጆቹ አላቀቀውና…"ልጆች አጎታችሁ ከረጅም ጉዞ ስለመጣ ደክሞታል…ወደክፍሉ ይግባና ሻወር ወስዶ ልብስ ቀያይሮ ተመልሶ ይመጣል..እስከዛ ለምሳ  ዝግጅ እየሆናችሁ ጠብቁት"አለና እጁን ይዞ ወደውስጥ ይዞት ገባ..ሳሎን ሰንጥቀው ከላፉ በሃላ ከኃላ ያሉ ብዙ ክፍሎችን እያለፍ በመሄድ  አንድ የተዘጋ ክፍል ከፍቶ " ግባ ..."እያለው ቀድሞት ገባ፡፡ገዘፍ ያለ የራሱ የሆነ ሻወር ቤት ያለው መኝታ  ክፍል ነው፡፡ ሻንጣውን ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠለትና…". እንግዲህ 30 ደቂቃ እንሰጥሀለን፡፡ሻወር ውሰድ...
7.9K viewsTsiyon Beyene, 09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 21:00:02 #ህያበ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_ኤርሚ

"እሱን እንዳታስቢው ወይም ራስሽ ፈልገሽ አግኝው... ደግሞ አታገኝውም" አማራጭ የለኝም ሻንጣዬን ይዤ ወደኋላ ተመለስኩ።

"እሺ ውሰደኝ አሁን ውሰደኝ"

"አይ አይሆንም ነገ ነው የምንሄደው" በእሽታ አንገቴን ነቀነኩለት።

ወደቀኝ ገልመጥ ብዬ ሳይ የሰርግ ቬሎዬ ተሰቅሏል። ለራሴ ወደኋላ የለም አልኩ...

"አንደርስም እንዴ ደግሞ እኮ አይኔን በጨርቅ አስረህዋል። የት ነው የምንሄደው ራቀብኝ? ያ ውሻ የት ነው ያለው?"

"አይንሽን ከገለጥሽ ከኔ ጋ ትጣያለሽ ማርያምን የምሬን ነው። ታገሽ ትንሽ ነው የቀረን ደርሰናል" ጥቂት ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ መኪናውን አቆመው

"አሁን ጨርቁን ማንሳት ትችያለሽ" ቶሎ ብዬ ፈታሁት... ሰው የሌለበት ቦታ ነው።

"ምንድነው ቢኒ እየቀለድክብኝ ነው" ፊቴን አዙሬ በንዴት አየሁት

"ውረጂ.,. ያውልሽ እዛጋ ይታይሻል...( በወዳደቁ ነገሮች የተሰራች ቤት) እዛ ውስጥ አለልሽ ውረጂና የፈለግሽውን አድርጊው" ሳላቅማማ ወረድኩ። በእልህና ንዴት እየተራመድኩ ወደቤቱ ተጠጋሁ ልገባ ስል

"እባቷ ነኝ ባሏ. ... ሀ ሀ ሀ... ንገሩኝ እስኪ እናቷን አግብቶ ልጁን ያስረገዘ አባት ታውቃላችሁ... አታውቁም? ሙትቻ ለምንድነው የምታፈጡብኝ... መልሱልኝ... ኧረ ተውኝ ኡ ኡ ኡ..." ጩኸቱ አስደንግጦኝ ወደኋላ ተመለስኩ። ትንሽ ተራምጄ ቆምኩና ልጄን አሰብኳት "እገለዋለሁ" ወደ ቤቷ ተመለስኩና ከፍቼ ጎንበስ ብዬ ገባሁ። የቤቱ ጠረን ይገፈትራል ሰው የመጣም አልመሰለው ዝምም ብሎ ልፍለፋውን ቀጥሏል። የማላውቃቸውን ብዙ የሴት ስሞች ይጠራል... ያለቅሳል፣ ይስቃል፣ ይራገማል፣ ድንገት ደግሞ አስደንጋጭ ጩኸቱን ይለቀዋል። ለደቂቃዎች ዝምምም ብዬ ሰማሁት... በብዙው የቤቱ ቀዳዳ በሚገባ ብርሀን አየሁት ከድምፁ ውጪ ምኑም እሱን አይመስልም። ልብሱ ተቀዳዷል፣ ፊቱ ጠቁሮ ከሰል መስሏል፣ ፀጉሩ ተንጨባሯል፣ እላዩ ላይ ተፀዳድቶ መሬቱ ጭምር በሽንትና ሰገራ ተበክሏል። ዮኒ እኔ ልሰጠው ካሰብኩት ሞት በላይ በቁሙ ሞቷል... ልቤን ሽው የሚል የሀዘኔታ ጦር ወጋኝ። ወዲያው ደግሞ ልጄን የከዳኋት መሰለኝ... እየሮጥኩ ከቤቱ ወጣሁ... ልፍለፋው ከኋላዬ ይሰማኛል... እያለቀስኩ መኪናውን ከፍቼ ስገባ

"አደረግሺው ህያብ ገደልሽው" አለኝ

"ሞቷል እኮ ቢኒ የሞተን ሰው ድጋሚ እንዴት እገለዋለሁ" ድፍት ብዬ ተንሰቀሰቅሁ

"ቢኒ እባክህ ምንም ሰላም ሊሰማኝ አልቻለም ዮኒን ሆስፒታል እንውሰደው" ደረቱ ላይ ተኝቼ ለቀናት ከራሴ ጋ ስከራከርበት የነበረውን ሀሳብ ነገርኩት

"እኔ የማውቃትም የምወዳትም ህያብ ይቺ ናት ለጠላቷ ሳይቀር የምትራራ። አታስቢ የኔ ቆንጆ ዛሬውኑ እናደርገዋለን" እዛው ቦታ ተመልን ሄድን። ወደዛች ቤት ገባን አጠገቡ ዳቦ ቁጭ ብሏል። ለነፍሱ ያደረ ሰው እንደሚመግበው ገባኝ። መለፍለፉን አላቆመም እንጂ ተዳክሟል... ይዘናቸው የሄድነው ባለሞያዎች በግድ አንስተው ስትሬቸር ላይ አደረጉት... ከኪሱ የተጣጠፈ ወረቀት ወደቀ፤ ቀልጠፍ ብዬ አነሳሁትና ዞር ብዬ ከፈትኩት በትልቁ ርዕስ "ፀፀት" ይላል። ከስሩ ደግሞ "ለማታዩኝ እኔ ግን በየቀኑ ለማያችሁ ለበደልኳችሁ ሁሉ" ይላል... ትርጉም ያለው ነገር ሊሆን ቢችልም ማንበብ አልፈለኩም... ሌላ ሸክም መሸከም አልፈልግም... እጄ ላይ ያለውን ሶስት ገፅ ወረቀት ቀዳድጄ ዱቄት አደረኩትና ለነፋስ ሰጠሁት ብትትንን... አምቡላንስ ውስጥ አስገብተው ይዘውት ሄዱ። ሰላም ተሰማኝ

አዳራሹ በእንግዶች ጢም ብሎ ተሞልቷል። ቃል የሚያገባቡን ቄስ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል።

"በሀዘን በደስታዋ በህመም በጤናዋ..." ቢኒ ቃል ገባ እሱ ያለውን መልሰው እኔንም አስባሉኝ።

የጋብቻ ቀለበት ጣቴ ላይ አደረገልኝ እኔም እንደዛው አደረኩለት.....
ገና ወደሰውነት ቅርፅ ያልተቀየረው የአምስት ሳምንት ልጄ ደስ ብሏት/ብሎት ይሆን ሆዴን ዳበስኩት። የልጄ አባት ቢኒ ፈገግ ብሎ አየኝ

"ተመስገን" አልኩ በልቤ የማያልፉ የመሰሉኝ ሁሉ አለፉ... ዛሬ ደስተኛ ነኝ... ነገን አምላክ ያውቃል።

ተ ፈ ፀ መ
7.8K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 20:56:56 አሮራ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _3
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ሊሄድ በመነሳቱ ቅር ብሏት"አጎቴ ደግሞ...እዚሁ ምትፈልገውን መጠጥ ያምጡልህ "አለችው።
አልተስማማም"አይ የዚህ ቤት መጠጥ ውስኪ.. ቢራ ምናምን ነው ..እኔ ምፈልገው ካቲካላ ነው።"አላት።
"እሺ ግን በልክ ጠጣ ...አብዝተህ ጠጥተህ ብኃላ  ቢያምህ በጣም እበሳጭብሀለሁ።"
"እቪ ሮሪ "አለና እንደልማድ ቦርሳዋን በመክፈት ...የተወሰኑ ብሮችን መዘዝ አደረገና ኪሱ ከቶ...ግንባሯን ስሞ ወጥቶ ሄደ።እሷም በተቀመጠችበት ቦታ ሆነ በስስት አይኗ ሸኘችው።ከዛ ጠረጴዛው ላይ ትቶት የሄደውን ሲጋራ አነሳችና አንድ መዛ ለኮሰች...ከዛ ማጨስ ጀመረች...የረሳ መስሎ አውቆ ለእሷ ሲል ትቶላት እንደሄደ ታውቃለች።ሁሌ እንደዛ ነው የሚያደርገው።የእሷ ተወዳጅ የልብ አውቃ አጎት።

ከምታጨሰው ሲጋራ ጭስ እየትጎለጎለ ሄዶ በአየር ላይ ሲበተን ማየት ያስደስታታል።እሷም የውስጥ ህመሟና የልብ ሀዘኗ አንድ ቀን እንዲህ ከውስጧ ተመዘ ወጥቶ በአየር ላይ ተበትኖላት ነፃና ደስተኛ ሆነ ለአንድ ወር እንኳን ሰላማዊ ህይወት ኖራ ሰላማዊ ሞት ብትሞት ደስ ይላታል።በውስጧ የተዳፈነው ሚስጥር ውስጧን በልቶ ሊጨርሳት ነው።
ሁል ጊዜ በልባችን አርቀን የቀበርነው ምስጢር ከሌላ ከማንም ሰው ጋር አንስተን ልንነጋገርበት  የማንችለው ስውር ገበናችን እያንዳንዶን ቀን በውስጣችን  የሚኖረው እኛኑ እየበላ ነው።ልባችንን ይቀረጣጥፋታል ነፍሳችንን በስለታም ጥርሱ ያደቃታል...አዎ ሄዶ ሄዶ መፍትሄ ማናገኝለት ከሆነ ሙሉ በሙሉ ይውጠናል።ምናችንንም አያስቀር ነፍሳችንንም ስጋችንንም ሰልቅጦ በመዋጥ ከህልውና መዝገብ ላይ ያጠፋናል።

እናም አሮራ ይሄ በደንብ ይታወቃታል የገዛ ምስጢሯ ማንም እንዳያስተውለው ማንም እንዳይረዳው እታች ጥልቅ ንብርብር ልቧ ውስጥ እንደቀበረችው ብታውቅም ከዛ አፈንግጦ በመውጣት ከአንጀቷ ሙዳ ስጋ ዘንጥሎ ወደቦታው ሲመለስ በደንብ ይታወቃታል በሌላ ቀን ደግሞ ወደጨጓራዋ ሄዶ የላይ ንብርብርና ሻካራ ክፍሉን ሞዣልቆ ሲያነሳውና ሲሠለቅጠው በደንብ ይሰማታል።ድንዛዜውና ቀጠሎ  መፈጠሯን እስክጠላ ያሰቃያታል።ብቻ በአጠቃላይ በውስጧ አውሬ እያሳደገች ነው።እሷን እየተመገበ በማደግ ላይ ያለ አውሬ።እሷ እንዲህ የተሠቃየች አባቷስ እንዴት ነው መኖር የቻለው?ሁል ጊዜ በውስጧ የሚላወስ ጥያቄ ነው።እንደሷ ሲያዝንና ሲተክዝ እንኳን አይታው አታውቅም።ሁል ጊዜ እንደሮጠ ሁል ጊዜ የሆነ ገንዘብ ለማግኘት...የሆነ ኃይል ለመጨበጥ...የሆነ ተልኮ ለማሳካት እንደባከነ ና እንደተዋከበ ነው።ስለውስጥ ህመሙና ስለልብ ስቃዩ ማሰቢያ ጊዜም ያለው አይመስላትም።አረ መታመሙን ራሱ እርግጠኛ ሆና መናገር አትችልም። ከተቀመጠችበት ክፍል ወጣችና ኮሪደሩን አልፋ ታናሽ እህቷ መኝታ ክፍል ሄደች።አንኳኳችን ገፋ አድርጋ ስትገባ እህቷ አልጋዋ ላይ ቁጭ ብላ  የስዕል መሳያ ደብተሯን ዘርግታ የተለያዩ ከለሮችን እየቀባች ነበረ...መጀመሪያ ሞግዚቷ የመጣች መስሎት ቀና አላለችም ነበር
"የእኔ ፅጌረዳ ምን እየሠራሽ ነው?"የሚለውን የእህቷን ድምፅ ስትሰማ ግን እጇ ላይ ያሉትን ከለሮች በትና ደብተሯንም ጥላ ከአልጋዋ ተስፈንጥራ ወረደችን አላዬ ላይ ተጠመጠመችባት።
አሮራም እንጠልጥላ እንዳቀፈቻት ወደአልጋው ወሰደቻትና እሷን አስቀምጣት ከጎኗ ተቀመጠች።

ታናሽ   እህቷ ሳሮን ገና ሰባት አመት ለመድፈን ሁለት ወር ይቀራታል።እናቷ ገና የሁለት አመት ጨቅላ እያለች ነው የሞተችው።በዚህ የተነሳ አሮሯ እንደእህቷ ብቻ ሳይሆን ልክ እንደራሷ ልጅ ነው የምታያት..ከሞግዚቶቹ ጋር በመተጋገዝ በምቾት እንድታድግ የተቻላትን አድርጋለች
ቢያንስ የእናቷ የሙት መንፈስ በእሷ ላይ ያለውን ቅሬታ ሊያለዝብ የሚችልበት አንድ ብቸኛ  የሠራችው ጥሩ ተግባር   ይሄ ታናሽ እህቷን ለማሳደግ የምታደርገው  እንክብካቤ ነው።
ከእህቷ ጋር ብዙ ነገር ከተጫወቱ በኃላ በመሀል የልጠበቀችው አስደንጋጭ ነገር  አንደበቷ ወጣ።
በተኮላተፈ አንደበት"እኔም እንደአንቺ ቶሎ ባድግ ደስ ይለኛል"አለቻት።
አሮሯ ደነገጠችና"የእኔ ውድ ለምንድነው ፈጥነሽ ማደግ የፈለግሽው...?ብዙ ትላልቅ ሰዎች እኮ እንደውም ተመልሰው ልጅ መሆን ነው የሚፈልጉት።"
"እንዴ !!!ልጅ መሆን ምን ሊያደርግላቸው?"
"ትልቅ ስትሆኚ ህይወት እየጠቆረችና እየቆሸሸች ትሄዳለች።ስታድጊ ደስታሽ እየደበዘዘ ሳቅሽ እየፈዘዘ ይመጣል።ትልቅ ስትሆኚ  ሀሳብሽ  በተንኮል የተሞላ ምኞትሽም በራስ ወዳድነት የተሰላ እየሆነብሽ ይሄዳል።"
ትንሽ እህቷ አሮራ ካተናገረቻቸው ነገሮች መካከል አንድም አልገባትም።
"እህቴ ምንድነው ምትይኝ?"
"የተናገርኩትን እርሺው...ለመሆኑ አንቺ እንደእኔ ቶሎ ማደግ የፈለግሽው ለምንድነው?"ስትል መልሳ ጠየቀቻት...የሠማችው መልስ ግን ጭንቅላት የሚያዞር እና ፈፅሞ ያልጠበቀችው ነበር።"አባዬ እንደአንቺ እንዲወደኝ"ነበር ያለቻት።
ይህን ቃል ስትሰማ በአእምሮዋ ደማሚት ነገር ነው የፈነዳው...በጦር ጎንን የመወጋት አይነት  ስቃይ ያለው ስሜት።
ብዙም እርግጠኝነት በማይገለፅበት የድምፅ ቅላፄ "እንዴ ?አባዬ እኳ አንቺን ነው ከእኔ በላይ የሚወድሽ "አለቻት።
"አይ አይደለም...ግን እንደአንቺ ባድግ ካንቺ እኩል ይወደኛል... አብሬው እንድተኛም ይፈቅድልኛል።"ስትላት
ሽምቅቅ አለች።ኩምትርትር አድርጎ ውስጥን የሚቆራርጥና የሚሸረካክት መሠነጣጠቅ።
ትንሽዬ ተወዳጅ እህቷን...የእናቷን አደራ የተሰጠቻት እህቷን ወደራሷ ስባ አቀፈቻት።የእኔ ውድ በደንብ እንድትስሚኝ እፈልጋለሀ
"..እኔ  የራሴ መኝታ ቤት የሌለኝ እና አባቴ መኝታ ክፍል የምተኛው አባቴ ከአንቺ በላይ ስለሚወደኝ ሳይሆን እኔ ስለሚያመኝና ለሊት ተነስቼ መድሀኒት መውስድ ስላለብኝ ሰዓቱን ጠብቄ እንድነሳ አባቴ ስለሚያግዘኝ ነው።እንጂ እንደውም እኔ እንደአንቺ የግሌ የሆነ የሚያምር መኝታ ክፍል   ቢኖረኝ በጣም ደስተኛ እሆን ነበር"አለቻት።አዎ ልትነግራት የምትችለው ይሄንን ብቻ ነው።ይሄንን ምክንያት የኮረጀችው ከአባቷ ነው።ብዙውን ጊዜ እቤቱ ውስጥ ላሉ ሰዎች ደጋግሞ ይሄንን የመድሀኒት ታሪክ ሲያወራ ሰምታለች።እናም እሷም ያንን ምክንያት ደግማ ማውራት ከጀመረች ቆይታለች።እርግጥ ከልብ በሽተዋ ጋር ተያይዞ ብዙውን ጊዜ በተከታታይ የምትወስደው መድሀኒት አላት።ግን አንደኛ መድሀኒቱን ከመተኛቷ በፊት መወሰድ የሚትችለው  ነው።እንደው ለሊት የሚወሰድ ቢሆንም እንኳን አሮራ በፈለገችው ሰዓት በመነሳት የፈለገችውን ነገር የማድረግ ችግር የለባትም።እሱም እንደሚያወራው በዚህ ጉዳይም ረድቷት አያውቅም።
ታናሽ እህቷም መጨናነቋል አውቃ"በቃ ገብቶኛል..ግን አንዳንዴ እኔ ጋር ብተኚ ለሊት ቀስቅሼሽ መድሀኒትሽን አውጥሻለሁ"አለቻት።
"የእኔ ውድ አውቃለሁ..እንዳልሺውም አልፎ አልፎ አብረን የምንተኛበት ሁኔታ እናመቻቻለን... አሁን  ተነሽ ወደሳሎን እንሂድና እራታችንን እንብላ"አለቻት።እየተሳሳቁ ተያይዘው ወደሳሎን ሄድ

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
6.8K viewsTsiyon Beyene, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 21:00:03 ሰው እንዴት ይህን ያክል ሰውን ሊወድ ይችላል እንዴትስ ሁሉ ነገሩ ፍቅር ብቻ ይሆናል ፍቅር... ፍቅር... አሁንም ፍቅር.... አንተጋ ያለው ፍቅር ብቻ ነው እኔጋ ደግሞ ላንተ ያለኝን ፍቅር ሊፈታተን የሚችል የበቀል ጥም አለ። ያንተ ፍቅር እና የኔ በቀል ጥም ተጣጥመው ሊሄዱ አይችሉም ስለሆነም ጥሜን ልቆርጠው ፍቅርህን መሸሽ መርጫለሁ። ያጣሁት ልጄን... ማያዬን... እንቁዬን... ሁሉ ነገሬን ነው። ገዳይዋን ሳልገድል እረፍት እይሰማኝም። አዝናለሁ ቢኒ...

አፈቅርሀለሁ ግን ልሄድ ነው። ትቼህ ልሄድ ነው... ጠንካራ ነህ ትወጣዋለህ።

ደህና ሁን
ህያብ"

ደብዳቤውን ፅፌ ከጨረስኩ በኋላ አጥፌ ፊት ለፊት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጥኩትና ሻወር ልወስድ ገባሁ። ቢኒ ቶሎ እንደማይመጣ ስለማውቅ ዘና ብያለሁ... ታጥቤ ፎጣዬን እንዳሸረጥኩ ስወጣ ቢኒን አልጋ ላይ ቁጭ ብሎ አገኘሁት በእጁ የፃፍኩትን ደብዳቤ ይዟል።

"ምንድነው ፍቅር? ድጋሚ ወደኋላ... ለምን እኔንስ ታደክሚኛለሽ አላሳዝንሽም" አለኝ አጠገቤ መጥቶ አይን አይኔን እያየኝ

"ልጄን በህልሜ አየኋት ቢኒ... አድኚኝ እያለች ስትጮህ አየኋት... ልጄ ከመሬት ስር ተቀብራ...(ሳግ አነቀኝ) አፈር ተጭኖባት እሱ ግን እየተነፈሰ ነው። እፈልገዋለሁ እናም በእጄ እገለዋለሁ" እልሄ ልኩን አለፈ... ፎጣዬን ጥዬ ልብሴን ለባበስኩና ሻንጣዬን ይዤ ልወጣ ስል።

"ዮኒን አግኝቼዋለሁ" አለኝ። ባለሁበት ቀጥ ብዬ ቆምኩ

"ምን?"

"ይሄን በቀል የተውሽ መስሎኝ ነበር ግን ከፈለግሽ አብሬሽ እሄዳለሁ ያለበትንም አሳይሻለሁ ስትገይውም ቆሜ አይሻለሁ።"

"የት ነው ያለው ቦታውን ብቻ ንገረኝ ብቻዬን እሄዳለሁ"

"እሱን እንዳታስቢው ወይም ራስሽ ፈልገሽ አግኝው... ደግሞ አታገኝውም" አማራጭ የለኝም ሻንጣዬን ይዤ ወደኋላ ተመለስኩ።

"እሺ ውሰደኝ አሁን ውሰደኝ"

"አይ አይሆንም ነገ ነው የምንሄደው" በእሽታ አንገቴን ነቀነኩለት።

ወደቀኝ ገልመጥ ብዬ ሳይ የሰርግ ቬሎዬ ተሰቅሏል። ለራሴ ወደኋላ የለም አልኩ...

ይቀጥላል
7.1K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 21:00:02 #ህያብ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በኤርሚ



#ከጊዜያት_በኋላ

"ንገሪኝ እስኪ ህያብ ሀኪም እንዲያይሽ ባትፈልጊም ህመምሽን ለኔ ንገሪኝ ዝምምም ብዬ እሰማሻለሁ። ስለ ልጅሽ ስለ ዮኒ ስለተፈጠረው ሁሉንም ንገሪኝ" ሶስት ወራትን በዝምታ ስለዚህ ነገር ሳያነሳብኝ ሳላወራው በየጊዜው የአእምሮ ህመሜ እየተነሳ ከኔው እኩል ሲሰቃይ አሳልፈናል። ትዕግስቱ እንክብካቤው ፍቅሩ ድሮ ከማውቀው የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ግን ምን ዋጋ አለው ፍቅር አንዳንዴ ፍትሀዊ አይደለም ቢሆንማ ኖሮ የማፈቅረው ዮኒን ሳይሆን ቢኒን ነበር። ወደ መኝታ ቤት ሄድኩ... ተከተለኝ... በሩን ከፍቼ ገባሁና ቤቴ ሄደን ካመጣናቸው እቃዎች መሀል አነስተኛውን ሻንጣዬን አወረድኩት... ከፈትኩት... ውስጡ ያለው ሁሉም የልጄ ማስታወሻ ነው። ለአዲስ አመት የሳለችልኝን አበባ አገኘሁት... እሱን አቅፌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ

"የኔ ልጅ... የኔ እንቁ... ናፈቅሽኝ እኮ" ቢኒ አጠገቤ ብርክክ ብሎ ትከሻዬን ያዘኝ ከዛም ወደራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ። ህመሜ ሳይነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን አረጋጋሁና ከእቅፉ ወጥቼ ከመፅሀፍ መሀል አጣጥፌ ያስቀመጥኩትን ደብዳቤ አወጣሁት... ከባዱን መርዶ ያረዳኝን... መራራውን እውነታ የጋተኝን ደብዳቤ አወጣሁና ለቢኒ ሰጠሁት። ግራ በተጋባ ፊት ካየኝ በኋላ ከፈተው... ደጋግሜ ከማንበቤ የተነሳ እያንዳንዱን ቃል እንደ ውዳሴ ማርያም የሸመደድኩትን ደብዳቤ እሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያነበው ከፈተው... እንዲህ ነው የሚለው...

"ማሚ ከበደል ሁሉ የቱ እንደሚከፋ ታውቂያለሽ... አባቴ የምትይው ሰው በስሜት ጦዞ ጭንሽን ሊከፍት ሲታገል ማየቱ...... ማም እውነቱ ይገልሻል አውቃለሁ ...ግን እንደዛ ጠንካራ ስነ ልቦና እንዲኖራት አድርገሽ ያሳደግሻት ልጅሽ ለምን ራሷን አጠፋች? የሚለው ጥያቄም ይገልሻል። ማም እውነቱን እወቂው..... መጀመሪያ የውሸት ቆይቶ ደግሞ የእውነት አባት የሆነኝ ዮኒ የውሸት አባቴ እያለ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ደፍሮኛል። ታስታውሻለሽ ያኔ ፔሬድ አሞኝ ነው ብዬሽ የተኛሁ ጊዜ... ለመጀመሪያ ጊዜ የደፈረኝ ቀን ነበር። አንቺ ውስጥ እያለሽ ሊጠይቀኝ ሲመጣ ፊቴን አዙሬበት ነበር አይደል? ከዛ አንቺ ወጣሽ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ 'በሶስተኛው ቀን መድገም አለብን ካላዛ ተደፍነሽ ትቀሪያለሽ' አለኝ። እናም በሶስተኛው ቀን መኝታ ቤቴ ድረስ መጣ... መከላከል ደከመኝ እና በዝምታ አየሁት ሳይራራልኝ እላዬ ላይ ጨፍሮ ሄደ... ያንኑ ድርጊቱን የአባትነት እውነታው እስከሚታወቅ ድረስ ደጋገመው። በተለይ ፊልድ መውጣትሽ ለሱ ምቹ ሁኔታ ለኔ ደግሞ ስቃይን ፈጠረ

ካንቺ ፊት ላይ የየሁትን ደስታ እኔ ጋር ፈልጌ አጣሁት። ማም እንዴት ልደሰት... አባቴን አገኘሁ ብዬ እንዴት ደስ ይበለኝ...? አባትነቱን እኮ ጭኔ መሀል ቆፍሮ ቀብሮታል። እናም አባቴ አይደለም ሊሆንም አይችልም ብዬ በዝምታ ተሸብቤ ቁጭ ብዬ እያለ ሌላ ክስተት ተፈጠረ። በየጊዜው እየመጣ ይቅርታ ብሎኝ 'አደራ ለናትሽ እንዳትነግሪያት' ከሚለኝ ከህሊናቢሱ አባቴ የስምንት ሳምንት ነብሰ ጡር እንደሆንኩ ሆስፒታል አረጋገጥኩ። ያኔ በራሴ ላይ ወሰንኩ... ታሪክ ራሱን አይደግምም... ማም አንቺ አባት እንደሌለኝ እያሰብሽ ወልደሽ እሳደግሺኝ... የኔ ልጅ አባት ግን አባቴ ነው... እናም በራሴ ላይ እና ባልወለድኩት የአባቴ ልጅ ላይ የሞት ፍርድ ወሰንኩ።

ማሚዬ ለኔ ስትይ ጠንክረሽ ኑሪ እወድሻለሁ።
እድለቢሷ ልጅሽ"

ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ ቢቆይም እንባ ከአይኖቹ እየወረደ ፍዝዝ ብሎ ተቀምጧል።

"ይህን ደብዳቤ ሳገኘው ቢኒ ጊዜው ረፍዷል... የልጄ ገዳይ አጠገቤ አልነበረም... ትቶኝ ሄዶ ነበር... ፈለኩት በየሆስፒታሉ በየሆቴሉ ግን አጣሁት... ባገኘው በአደባባይ ስጋውም ዘልዝዬ ለአሞራ እሰጠው ነበር"። እያለቀሰ መጥቶ አቀፈኝ ረጅም ሰአት ተቃቅፈን ተላቀስን...።

"እባክሽ አንድ ነገር እሺ በይኝ የስነልቦና ሀኪም ይይሽ እባክሽ ለኔ ስትይ" ለብዙ ጊዜ ደጋግሞ ቢጨቀጭቀኝም እምቢ ነበር መልሴ

"እሺ ደስ ያለህ ሀኪም ጋ ውሰደኝ"

።።።።። ።።።።። ።።።። ።።።።። ።።።

የስነ ልቦና ህክምናዬን ከጀመርኩ አንድ ሳምንት ቢያልፈኝም ለዶክተሬ ምንም የነገርኩት ነገር አልነበረም። የሆነ ቀን ግን ልክ ከዚህ በፊት ያለውን ታሪክ እንደሚያውቀው ሁሉ

"ዮኒን ብቻ ጥፋተኛ አድርጌ እንዳልፈርድ የሚያደርገኝ እንደዚህ ያሳመመኝ ብዙ ፀፀት ውስጤ አለ። ብዙ ቢሆን ኖሮ.... ብዙ.... ብዙ....

•ከመጀመሪያው ታሪኬን ነግሬው ቢሆን ኖሮ

•ስራ ስራ ማለቴን ትቼ ለልጄ ጊዜ ሰጥቻት ቢሆን ኖሮ

•እንደዛ ሆና እያየኋት ትንሽ እንኳን ለምን አልተጠራጠርኩም... አሁን እኔ ዶክተር እባላለሁ...

ከሁሉም በላይ ፀፀቱ በልቶ ጨረሰኝ... መገጣጠሚያ አጥንቴ እስከሚታይ ከሳሁ... ጠቆርኩ... ታመምኩ... አበድኩ ...ግን ትርጉም አልነበረውም... እኝህ ሁሉ የኔን እንቁ አይመልሱልኝም ባዶ... አንተስ የኔን እንቁ ትመልስልኛለህ? አየህ እዚህ መጥቼ መፋጠጣችንም ትርጉም የለውም ባዶ..." አልኩት። ዝምምም ብሎ ካየኝ በኋላ ከወንበሩ ተነስቶ መጥቶ ፊት ለፊቴ ሶፋ ላይ ተቀመጠ

ከስድስት ወራት ያላሰለሰ የህክምና ክትትል በኋላ ወደራሴ ተመለስኩ ወደ ስራየም ጭምር። ከቢኒ ጋር ደስ የሚል የፍቅር ግንኙነት ጀመርኩ... ህይወት ድጋሚ ቀጠለች። ያለፈው ባይረሳም ህመሙ ቀንሷል... የልቤ በልቤ ተቀብሮ መሳቅ ቻልኩ።

ከቢኒ ጋ ልንጋባ ነው ማለትም ከሁለት ወር በኋላ እንጋባለን። ለፊርማው እንጂ የምንኖረው አንድ ቤት የምንተኛው አንድ አልጋ ላይ ከተጋባን ቆይተናል ለማለት ነው። ልንጋባ መሆኑን ያወቀው ሀብታሙ ካለበት ሀገረ አሜሪካ የሚያምር ቬሎና ሱፍ ልኮልናል። ለቢኒ ሚዜ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ።

የሆነኛው ሌሊት ላይ ተኝቼ ልጄን በህልሜ አየኋት... ብቻዋን አይደለም ዮኒ ሲደፍራት "ድረሽልኝ" እያለች ስትጮህ... ጮኬ ከእንቅልፌ ነቃሁ... አጠገቤ የተኛው ቢኒ ጩኸቴ አስደንግጦት

"ምንድነው ፍቅር አይዞሽ ቅዠት ነው" አለና እቅፉ ውስት ከተተኝ... እኔ ግን የበቀል ጥሜ ድጋሚ አንሰራራ... እፈልገዋለሁ እናም እገለዋለሁ... እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።

ለቀናት በሀሳብ ተብሰከሰኩ እናም ወሰንኩ ይህን ነገር ከስሩ መንግዬ መጣል ይኖርብኛል። ተቆርጦ ባቆጠቆጠ ቁጥር ህመሙ እየባሰ ነው የሚሄደው ስለዚህ እ ገ ለ ዋ ለ ው

#አሁን

ትቼው ልሄድ ነው። በቃ ልሄድ ነው የመጨረሻ ውሳኔዬን ወስኛለሁ የምሄደው እንደ ሌላው ጊዜ ጥላቻንና ክህደትን ሽሽት አይደለም... ፍቅርን እንጂ።
እናም በሀሳብ እየዋዠኩ ደብዳቤ ልፅፍለት ወሰንኩ ቢያንስ ምክንያቴን ማሳወቅ አለብኝ አይደል... ደግሞ ጠፋች ብሎ ሀገር ምድሩን ነው የሚያምሰው...

መፃፍ ጀመርኩ

"አንዳንዴ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ይሆንብኛል። ፍቅርህ፣ ስስትህ፣ እንክብካቤህ፣ አንተን ትተህ ለኔ ደስታ መድከምህ፣ ከቃላት ጋጋታ ይልቅ በተግባር የምታሳየኝ መውደድህ በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህን መቋቋም ያቅተኛል።
6.2K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 12:17:55 የለም።መልሶ ፊቱን ወደሴትዬዎ አዞረ።አሁንም ጥሪዋን አላቋረጠችም... እጆቹን አንከረፈፈና ጣቶቹን ወደደረቱ  በመጠቆም "እኔን ነው?"የሚል   ምልክት አሳያት።
እሱን እንደሆነ ግንባሯን በመነቅነቅ አረጋገጠችላት።መልኳ በግልፅ እየታየው ስላልሆነ ማንነቷን ፈፅሞ ማወቅ አልቻለም።
እግሩን አንቀሳቀሰ ።... ፈራ ተባ በሆነ እርምጃ ወደ መኪናዋ ማዝገም ጀመረ።


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
6.2K viewsTsiyon Beyene, edited  09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 12:17:55 አሮሯ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _ሁለት
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

መንግስቱ ዛሬ ከሶስት አመት የእስር ቆይታ በኃላ ከእስር  የሚወጣበት የነፃነቱ ቀን ነው።ለዛም እየተዘጋጀ ነው ።ለብሶት ያደረውን ቢጃማ አወለቀ። ከወገብ በላይ እራቁቱን ሆኖ ከአሮጌ ሻንጣው ውስጥ የተሻለ ያለውን ልብስ እየመረጠ ነው።መንግስቱ እስር ቤት ከመግባቱም በፊት ዘለግ ያለ ቁመትና ፈርጠም ያለ ሰውነት ያለው የ31 ዓመት ወጣት ሲሆን እስር ቤት ከገባ በኃላም ያንን ሰውነት በእስፓርት ፈርጣማና በጡንቻ የዳበረ እንዲሆን አድርጓታል።በዛ የደረጀ ሰውነቱ ላይ ደረቱ አካባቢ ወደ ግራ ልብ ዘንበል ያለ የሴት  ምስል ተነቅሶበታል ።ከጀርባው ደግሞ ከመቶ ሜትር ርቀት በሚነበብ ድምቀትና መጠን "አሮራ ፍቅር"የሚል ሌላ ንቅሳት አለበት።ይህቺ አሮሯ የልብ ሰው ነች።ክፍኛ ያፈቀራት የውስጥ እሳቱና የልብ ትኩሳት  ነች።ሶስት አመት የታሰረላት ሴት ። ልብሱን ለብሶ ሲጨርስ ሻንጣውን መልሶ ዘጋጋና ዝግጅቱን አጠናቀቀ።
መቼስ ለማንም ሰው ቢሆን ከእስር  መለቀቅ የተለየ አይነት ስሜት መጫሩ የሚጠበቅ ነው። ግን  ሶስት አመት በእስር ቆይቶ ከሚለቀቅ ሰው ይልቅ ሶስት ሳምንት ታስሮ ሊፈታ ያለ ሰው የበለጠ  እንደሚደሠትና በመፈታቱ ፈንጠዝያ ተሰምቶት አምላኩን እንደሚያመሠግን  ብዙ ሰው አያውቅም።አንድ ሰው ሶስት ሳምንት እስር ቤት ቢያሳልፍ እስር ሳይሆን እረፍት ነው ሚሆንለት።አዲስ ልምድ ያገኝበታል ፣ጥቂት ማሰቢያ ጊዜ... የተወሰነ መረጋጊያ ስፋራ  አግኝቶ  ከነበረበት የህይወት  ግርግር ገለል በማለት ከራሱ ጋር ስብሰባ እንደተቀመጠ ነው የሚቆጠረው እና ከዛ  ሲለቀቅ ከሞላ ጎደል ሁሉን ነገር በተወበት ቦታ  እንደነበረው ነው የሚጠብቀው።።እንዲህ እንደ መንግስቱ ሶስት አመት የታሰረ  ሰው ግን ትፈታለህ ሲባል ጭው የሚያደርግ ብዠታ ውስጥ ነው የሚገባው። "ተፈትቼስ እንዴት ነው የምሆነው?ምን ሰርቼስ እኖራለሁ?"ሲል ይጠይቃል።አዎ  አሁን  መንግስቱ ደጋግሞ በአእምሮ እያመላለሳት ያለውን ጥያቄ ብዙዎቹ የእሱ ቢጤ ከረጅም እስር በኃላ የሚፈቱ ታራሚዎች ሁሉ ይጠይቁታል።
መንግስቱ  ሶስት አመት በእስር በማሳለፉ ምክንያት ከስራ ተፈናቅሏል።አሁን ከእስር እንደወጣ የድሮ መስሪያ ቤቱ ሄዶ ወደስራዬ መልሱኝ ብሎ ቢጠይቅ ከመልሳቸው ቀድሞ ሳቃቸው እንደሚያመልጣቸው እርግጠኛ ነው።ለአመታት ባንክ ደብተሩ ላይ አጠራቅሞት የነበረውን ብርም አንድ ሁለት እያለ አውጥቶ ጨርስታል።በተለይ በተከሰሰበት ወንጀል ከ10-15 አመት  እንዲቀጣ ትግል ያደረግበት የነበረውን በአሮራ አባት የተቀጠረው የከሳሽ ጠበቃን  በመፋለም ከተራዘመ አሰልቺ ክርክር  በኃላ ወደ አምስት አመት እስር ዝቅ አስደርጎ ለማስወሰን በአመክሮም በሶስት አመት ለመውጣት  ላስቻለው  ጠበቃው ከፍተኛ የሚባል ገንዘብ  ከፍሏል።

አሁን  ይህን ሁሉ እያሰበ ያለው እስር ቤት ግቢ ውስጥ  ሆኖ ሻንጣውን  በቀኝ ጎኑ አስቀምጦ በእጅ ላይ ያለውን የአሮሯን ፎቶ እያሻሸና  በአትኩሮትና በናፍቆት እያየ" ፓሊሶቹ ናና ውጣ" እስኪሉት በመጠበቅ ላይ እያለ ነው።ይህን ፎቶ ለአንድ ሚሊዬን ጊዜ  ነው  እያየው ያለው ።አሮሯ የጥቁር ፈርጥ ዕንቁ መልክ ያላት ዝነኛ እና ቆንጆ ልጅ ነች። ብዙ ጊዜ ኮስታራ ግን ደግሞ ከቀናቶች አንድ ቀን እንደው ተሳስታ ፈገግ ስትል የጥርሶቾ ንጣት ከፊቷ ጥቁረት ጋር  እና ከአይኖቾ ፍካት ጋር ያለቸው ህብራዊ ስምምነት እንደው ልብን ድንዝዝ ወይም ፍስስ የሚያደርግ ልዩና አጠቃላይ ሁለንተናውን  የማቅለጥ ኃይል ያላት አስማት የሆነች ወጣት ነች።
ይሄን ሁሉ ስለእሷ መልክና ቁመና ያጠናው ፍቅረኛው አድርጎ ቀርቦትና  እርቃን እሷነቷን እያገላበጠ ስላየ   አይደለም። በርቁ ስለሚያፈቅራት ነው።ባታስበውም ያለማቋረጥ ስለሚናፍቃት ነው።የለሊት ህልሙና የመላ ህይወቱ እቅድ ስለሆነች ቀኑንም ሆነ ሌቱን በአእምሮ እየተገለባበጠች ስለምታሳልፍ ነው።

አሁን በኪሱ ጥቂት ገንዘብ አለው።ይሄን ገንዘብ  እዚሁ ወህኒ ቤት የእንጨት ስራ በመስራት ካገኘው ገንዘብ የቆጠበው ነው።ይሄንን ሞያ እዚሁ እስር ቤት የተማረው ነው።ሲወጣም ምን አልባት እራሱን ሊያኖርበት የሚችለው   የተሻለው ተስፋው ይሄ ሞያ ነው። ዘመዶቹም ጓደኞቹም ከታሰረ በኃላ ለስድስት ወር ያህል እንደነገሩ በተንጠባጠበ ሁኔታ ከጠየቁት በኃላ ቀስ በቀስ እግራቸውን ሰብሰብ አድርገው ጠፍተዋል።እናም እረስተውታል። እናትና አባቱም ከረጅም ጊዜ በፊት ነው የሞቱት።በዚህም የተነሳ  አሁን የሚያስታውሰውና እየናፈቀ ያስቸገረው አንድም ሰው በምናብ የለም።ከአሮሯ በስተቀር ሁሉንም ረስቷቸዋል።አዎ አሮሯ ህመሙ ነች።አሮሯ ናፎቆቱ ነች።አሮሯ ረሀብ ነች።አሮሯ በህይወቱ የሆነ ጎኑ እንዲበሰብስበት ያደረገች ..የሆነ ገኑን ደግሞ  ሻማ ለኩሳ የሚንቦገቦግ ብርሀን በውስጡ እንዲረጭ ያደረገች  ሴት ነች..አሮራ።እና ከዚህ እስር ቤት በመውጣቱ ደስ የሚሰኝበት አንድና ብቸኛ ምክንያት  ለመጨረሻ ጊዜ የዛሬ ከሶስት አመት ከመታሰሩ በፊት አይቷት የነበረውን አሮሯን  ዳግመኛ ለማየት ብቻ ነው።እርግጥ እሷ ባለችበት አካባቢ 500 ሜትር በላይ እንዳይቀርባት  በፍርድ ቤት  የተጣለበትን  ገደብ አሁንም አልተነሳለትም።ቢሆንም ከዚህ ይውጣ እንጂ   ለዛ የሆነ መፍትሄ ያበጅለታል።"አሁን ምን ያህል አድጋ  ?ምን ያህልስ ወፍራ ወይም ከስታ ይሆን?"ሲል እራሱን ጠየቀና ፈገግ አለ።

"መንግስቱ ኃይሉ ...መንግስቱ ኃይሉ..."የሚል የፓሊስ የጥሪ ድምፅ  ከትካዜው አባነነው።
"አቤት"
"ዕቃህን  ያዝና ተከተለኝ...ልትወጣ ነው።"ሲል ማይቀረውንና አስፈሪውን የምስራች አበሰረው።ቶሎ አለና ፎቶውን ደረት ኪሱ በመክት ሻንጣውን ይዞ የስር ቤት ጓደኞቹን በየተራ እያቀፈ ለመጨረሻ ጊዜ ተሠናብቶ  ሻንጣውን በመያዝ ፓሊሱን ተከትሎ ወጣ። ወደአስተዳደር ቢሮ ነው ያመሩት።ከእስር ነፃ መለቀቁን የሚገልፅ ደብዳቤ ተቀበለና ከግቢው እንዲወጣ ተደረገ።
አሁን እዚህ ቦታ ሄዳለሁ የሚለው የተለየ ስፍራ የለውም። ወደድሮ ሰፈሩም የሚሄድበት ምንም ምክንያት እየታየው አይደለም። ከወላጇቹ የወረሰውንም እቤት ከመታሰሩ በፊት ነው በረጅም ጊዜ ኮንትራት ያከራየው።ስለዚህ ለጊዜው የእሱ አይደለም። አሁን ማድረግ የሚችለው ባገኘው በመጀመሪያው ታክሲ ወይም ባጃጅ ውስጥ ገብቶ ይሄን ሰፈር መልቀቅ ፤ከዛ ታክሲው በሚቆምበት የመጀመሪያው ወይም ሁለተኛ ፌርማታ ላይ መውረድና በአካባቢው ዞር ዞር ብሎ ኪሱን የሚመጥን ቤርጎ ፈልጎ መከራየት ...ከዛ አንድ ሁለት ቀን አርፎ መረጋጋት፣አሮሯን አፈላልጎ በሩቁም ቢሆን ማየት ... ከዛ ስራ ፈልጎ መቀጠር...እንደዛ እንደዛ እያለ ቀስ በቀስ ህይወቱን በአዲስ መልክ  ማስተካከል ...አዎ እቅድ እንደዛ ነው።

ከማረሚያ ቤቱ ቅፅር ግቢ መቶ ሜትር ተጓዘና ታክሲዎች እና  ባጃጆች የሚራኮቱበት ስፍራ ደረሰ።ወደ ታክሲ  ልግባ ፈይስ ወደ ባጃጅ ?እያለ ከራሱ ጋር ሙግት ገጥሞ ባለበት ሰዓት ከወደቀኝ በኩል  ደመቅ ያለ የመኪና ክላክስ  ጥሪ ሰማ።ሳያስበው ዞር ብሎ እይታውን ወደዛ ሲልክ  በመቶ ሜትር ርቀት አጥር ታካ የቆመች የተወለወለች አዲስ አይጥማ ከሮላ መኪና ተመለከተ።በመኪናው የኃላ ገቢና የተቀመጠች አንድ ብስል ቀይ ሴት  አንገቷን በመስኮት አስግጋ በማውጣት  እጆቾን ወደእሱ እያርገበገበች ወደ መኪናዋ  እንዲመጣ ምልክት እያሳየችው ነው።ግራ ገባው።ወደጀርባው ዞር ዞር  አለና ሌላ ሰው ይሆን እንዴ የምትጠራው? የሚለውን ጥርጣሬ ለማረጋገጥ ሞከረ።ማንም ከጀርባው
6.1K viewsTsiyon Beyene, 09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-17 21:00:03 "መነጋገር ያለብን አይመስልሽም" አለኝ። ወደ ስራ ለመሄድ እየተጣደፍኩ እያለ   "አስቤበታለሁ ማውራት አለብን ግን አሁን አይደለም... ሆስፒታላችን የልምድ ልውውጥ ሌላ ከተማ ሊልከኝ ነው። ከአስራ አምስት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ያኔ እናወራለን" መኪናዬን አስነስቼ ወጣሁ

ሳሎን ቁጭ ብለን ከታሪኬ ሀ ጀመርኩለት
"የአስራ ሶስት አመት ልጅ እያለሁ ነው........." ሁሉንም አንድ በአንድ ዘርዝሬ ነገርኩት ከሱ ግን ያላሰብኩትን ነገር ሰማሁ

"እና ያኔ የደፈርኩት አንቺን ነበር"

"ምን? ምንድነው የምታወራው?"

"ብርቄን ታውቂያታለሽ? ጎረቤታችሁ ናት መሰለኝ"

"አዎ ብርቄን ከነ ነገሯ የማያውቅ አለ እንዴ... ግን አንተ እንዴት?"

"የዩንቨርስቲ ተማሪ እያለሁ እናቴ የማልወዳት አክስቴ ጋ መልዕክት ይዘህ ሂድ ብላ ላከችኝ... እረፍት ስለነበርንም እየተነጫነጭኩ ብርቄ ጋ መጣሁ።
በዛውም ከአክስቴ ጎረቤት ልጅ ዘመናይ ጋር ተዋወቅሁ። በሁለት ቀን ውስጥ ተዋደን ሴክስ አደረግን( አውቃታለሁ አገር ያወቃት ወንድ አሳዳጅ ናት አልገረመኝም ) የዛን እለት ግን እዛ የጭቃ ቤት ውስጥ እያለን ወደኛ የሚመጣ ሰው ድምፅ ሰማን እና እሷ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደች እኔ ግን እዛው ቀረሁ። በወሲብ ስሜት ጦዤ ስወጣ አንቺን ከሩቅ አየሁሽ እና ጠራሁሽ.... ያ ሁሉ ነገር ተፈጠረ" ከነገረኝ ታሪክ ውስጥ አንድ አስደሳች ነገር አገኘሁ... የእንቁን እውነተኛ አባት

"አክስቴ እኔ እንደደፈርኩሽ ስታውቅ... ማንም ሳያየኝ በሌሊት ሀገሩን ለቅቄ እንድሄድ ድጋሚም እንዳልመለስ አስጠንቅቃ ወደ እናቴ ላከችኝ። በሶስት ቀን ቆይታዬ ብዙ ታሪክ ፈጥሬ ተመለስኩ"
' ሳትፈልግ ማን ሊነካት' እያለች ስታወራ የነበረችውን ብርቄን አሰብኳትና ተገረምኩ ወዲያው ደግሞ ደስ የሚለውን ሁኔታ አሰብኩት

"ደስ ሲል" ሳላስበው ቃል ከአፌ ወጣ

"ምኑ ነው ደስ የሚለው የኔ አንቺን መበደል ድሮ እንደጀመረ ማወቅሽ ነው" ግራ ግብት ብሎት ያየኛል

"እንቁ እውነተኛ አባቷን ማግኘቷ"

"ማለት...? ምን እያልሽን ነው? ምናሴ የኔ ልጅ... አይ አይሆንም... ማለት ተደፍረሽ ነው የወለድሻት...? አይ ውሸትሺን ነው።"

መልስ ሳልሰጠው እየሮጥኩ እንቁ መኝታ ቤት ገባሁ ቁጭ ብላ እያነበበች ነው። ስገባ ቀና ብላ አየችኝ

" ምን ተገኘ ማሚ ፊትሽ እኮ በፈገግታ ሊፈነዳ ነው"

"የተገኘውማ አባትሽ ነው"

"የእውነት...(እንባዋ ኮለል ብሎ ወረደ ሰፍ ብላ አፍ አፌን አየችኝ) የት ነው ያለው ማሚ... የኔ አባት የት ነው?( ሳግ አነቃት) ማሚ በተለይ በዚህ ሰዓት አባቴን በጣም እፈልገዋለሁ... እማ ንገሪኛ..."

"ዮኒ እውነተኛ አባትሽ ነው" አንገቷን ወደኔ አስግጋ ሁለመናዋ ጆሮ ሆኖ በአይኗ ሳይቀር ስትማፀነኝ የነበረችው ልጄ ከኣካሏ እኩል ስብር ስትል አየኋት

"እሱ አባቴ አይደለም... ትክክለኛ አባቴን የአብራኩ ክፋይ የሆንኩትን ሰው ነው የምፈልገው" አለችኝ እንዳቀረቀረች

"አዎ የኔ እንቁ አንቺ የዮኒ የአብራኩ ክፋይ ነሽ ታሪኩን እነግርሻለሁ። የአስራ ሶስት አመት ልጅ እያለሁ..." ዝምምም ብላ ሰማችኝ... ምንም አይነት እንቅስቃሴም ሆነ ንግግር አላደረገችም... ዝምምምም.... አውርቼ ስጨርስ

"ደስ አይልም የኔ እንቁ" አልኳት እንባዋ ገደቡን ጥሶ ወረደ 'ምንድነው እንቁ ለምንድነው የምታለቅሺው'

"ደስ ብሎኝ ነው እማ... የደስታ እምባ ነው። ነይ እቀፊኝ" ተቃቀፍንና

"በቃ ይሄን ቀን ፏ አድርገን እናከብረዋለን ነይ ተነሺ" እጇን ይዤ አስነሳኋትና ወደ ሳሎን ሄድን ዮኒ የለም... መኝታ ቤት አየሁት የለም... ቤት ውስጥ የለም... ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ለሳምንታት የለም...

የሆነኛው ቀን ሌሊት ላይ ስልክ ተደውሎልኝ ዮኒ ያለበትን ቦታ ነገሩኝ... ጭፈራ ቤት ነው። ስሄድ ከሁለት ሴቶች ጋ አብሮ እያበደ ነው... ምንም ሳልል ወደቤቴ ተመለስኩ... ለራሴ ግን አንድ ውሳኔ ወስኜ ነበር 'ተመልሶ እዚህ ቤት አይረግጥም'። ብቸኝነት ተሰማኝ... ቅዝቃዜው አንዘፈዘፈኝ.. እናም ብቸኛዋ እንቁዬ ጋ ልሸሸግ ወደሷ መኝታ ቤት ሄድኩ። በሩን ከፍቼ ስገባ ግን የኔ እንቁ መሬት ላይ ተዘርራ አየኋት ጮኩ። እልፍነሽ ስትሮጥ መጣች... ከመሬት አንስተን አልጋ ላይ ካደረግናት በኋላ የልብ ምቷን አየሁት... ቆሟል... አፏን አሸተትኩት ገዳይ መርዝ ጠጥታለች። ሰውነቷን ነካሁት ከበረዶ ቀዝቅዛለች...
የኔ እንቁ የለችም... ትታኝ ሄዳለች...

ይቀጥላል
6.3K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-17 21:00:03 #ህያብ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በኤርሚ


"ባልሽን አሳርፊው ልንማር እንጂ ልንሸረሙጥ አልመጣንም ቴሌግራም ላይ ሙሉ መረጃውን ታገኛለሽ" ይላል። እየተጠራጠርኩ ቴሌግራም ከፈትኩ ፊት ለፊት የመጣልኝን መልዕክት ስከፍተው
ፎቶ እና አጭር ቪድዮ.....  ዮኒ ከሌላ ሴት ጋር....

እየሰሙ አለማመን ያለም የሚጠበቅም ነው። እያዩ አለማመን ግን ምን ይባላል። በአካል መጥተው ዮኒ ከእከሊት ጋር ማገጠብሽ ቢሉኝ አይደለም እሱን ልጠራጠር ከነገረኝ ሰው ጋር ልጣላ እችላለሁ። አሁን ግን እውነታ ነው ቁጭ ያለልኝ... ከምወደው ባሌ ጋር እርቃን ገላዋን አብራው የምታብድ ሴት እያየሁ ነው። የአንዷ አልበቃ ብሎ ከሌላ ሴት ጋር ደግሞ ከንፈሯ ላይ ተጣብቆ ያለ ፎቶ እያየሁ ነው... ግን አንድ ነገር ብቻ ነው የምለው። "የኔ ዮኒ አያደርገውም" አድርጎታል እኮ ...ግን ይህንን ማመን ያልፈለገ ውስጥ አለኝ... እናም እውነታውን እያየ ግግም ብሎ አላምን አለኝ። አንደኛው ውስጤ ደግሞ ፍቅርን ሳይቀር ወደጎን ብሎ በቀልን ፈለገ። ቢችል አሁን ያለበት ሄዶ ስጋውን ቢዘለዝለው ተመኘ። የማያምነው ውስጤ ገኖ ወጣና
"ዮኒ አያደርገውም" በጩኸት ቤቱን አደበላለኩት። ሰራተኛዬ እልፍነሽ መኝታ ቤቴን ከፈት አደረገችና

"ሰላም ነው ህያብ" አለችኝ

"ሰላም ነው እልፌ ወደ ስራሽ ተመለሽ" በሩን ዘግታ ተመለሰች። ረጅም ደቂቃ ዝምምም ብዬ ስልኬ ላይ አፈጠጥኩ

ሀሳቡ አደከመኝ ያየሁት እውነት አራደኝ በዛ ላይ ሰሞኑን የተለየ ኬዝ ስለነበረ ያለ እንቅልፍ ሆስፒታል ነበርኩ። ስልኬን ዘግቼ ያስቀመጥኩት መሰለኝ... ከዛ ወደ አልጋዬ ተራመድኩ.... አንድ.... ሁለት..... ጭልም አለብኝ።

"እናት ኧረ ንቂ የኔ ፍቅር" ይሄን ጥሪ ከሰማሁት ስንት አመት ሆነኝ.... ሁለት.... ሶስት... ብቻ በዛ መሀል... አሁንስ ለምንድነው እየሰማሁት ያለሁት... ሁሉም ነገር ከረፈደ... ካለፈበት በኋላ ለምን?... አይኔን ሳልገልጥ እንቅስቃሴውን እየተከታተልኩ ነው።

"ንገሪኝ እስኪ እናት ማነው ጥፋተኛ እኔ ወይስ አንቺ? በእርግጥ የኔ ጥፋት ሚዛን ይደፋል... ምክንያቱም ካየሽው ውጭ እንኳን ብዙ ጥፋቶችን ሰርቻለሁ ግን ባንቺ ጥፋት ላይ ተመርኩዤ ነው። ታውቂያለሽ ከቢኒ ጋር ድሮም እጠረጥርሽ ነበር እና ጥርጣሬዬን የሚያረጋግጥልኝ ነገር ሳገኝ እውነት አይደለም ብዬ ማመን አቃተኝ። ልታስረጅኝ ስትሞክሪ ውሸቷን ነው ብዬ አልሰማም አልኩሽ እናም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ ማገጥኩብሽ... ግን እናት ያሁኑ በደሌ በዛ..... (ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ እና ትንሽ ዝም ካለ በኋላ ቀጠለ) ከስንት ጊዜ በኋላ በአንዲት ልጅ ምክንያት ራሴን አዳመጥኩት። አብረሽኝ ካልተኛሽ ውጤትሽን አበላሸዋለሁ ብዬ አስፈራራኋት.... ብዙ ለመነችኝ... ልመናው አልሰራ ሲላት ግን ያንቺን አድራሻ ፈልጋ ሆስፒታል መጣችና አየችሽ። ስለትዳራችን ሳይቀር ብዙ መረጃ ሰበሰበች ከረፈደ ቢሆንም  ንግግሯ ከእንቅልፌ አነቃችኝ... ትልቁን በደሌን የሰራሁ እለት ከእንቅልፌ ነቃሁ

'ሚስትህ ነፍሷን ሳትሰስት ትሰጥሀለች... አንተ ማመን ባልፈለከው ውሸት ውስጥ ተደብቀህ በሀጢያት ተጨማልቀሀል... ለሷ አትገባትም ምክንያቱም ንፁህ ናት... ግን እግዜር ይቅር የማይለው የለም አምላክህንም ሚስትህንም ይቅርታ ጠይቀህ ወደራስህ ተመለስ። ለውጤቴ ስል አብሬህ ላድር አልፈልግም በተለይ ያቺ ሚስኪ ላይ ይሄን ላደርግ አልችልም። ከፈለግህ ኤፍ አድርገው ህሊናዬን አላቆሽሽም'  ብላኝ ስላንቺ እንዴት እንዳወቀች ሁሉንም ነገር አብራራችልን እና ለአመታት ከተኛሁበት እንቅልፍ ዛሬ ቀስቅሳኝ ሄደች። ያሰብኩት ለሀያ ደቂቃ ብቻ ነው። ወደራሴ ተመለስኩ... እውነታውን ማየት ቻልኩ... በንግግሮቼም ሆነ በተግባር ብዙ እንደገፋሁሽ አወቅሁ... በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን እንዴት እንደምትጠነቀቂልኝ... ምን ያክል እንደምትወጂኝ ተረዳሁ። ወደዚህ ለመምጣት እየተጣደፍኩ ስወጣ ቢሮ በር ላይ ከዚህ በፊት በውጤት አስፈራርቻት አብሪያት የተኛሁትን ልጅ አገኘኋት እናም ቪዲዮና ምስል ላንቺ እንደላከችልሽ ነገረችኝ። ምንም ሳልል ወደዚሁ መጣሁ ወድቀሽ አገኘሁሽ።
ህያቤቴ እየሰማሽኝ እንደሆነ አውቃለሁ። ይቅር በይኝ አልልሽም በተለይ በአንድ ጉዳይ ያንቺ ይቅርታ አይገባኝም... ብቻ አይንሽን ግለጪና የፈለግሺውን ቅጪኝ" አይኔን ገለጥኩ ከወገቤ ቀና አልኩና ትራስ ተደግፌ ቁጭ አልኩ። ለረጅም ደቂቃ በዝምታ አፈጠጥኩበት

"ደስ ያለሽን አድርጊኝ የፈለግሺውን ቅጪኝ " አንደበቴ ሊናገር ቢፈልግ እንኳን ውስጤ ዝምምምም ብሏል የሚያስፈራ ዝምታ

"ደግሞ አሁን እሰማሻለሁ ከቢኒ ጋር ያደረጋችሁትን ንገሪኝ እኔ እንደተናዘዝኩ ተናዘዢልኝ.... ይቅር ተባብለን  አብረን ባንቀጥልም ጥያቄዎቼን እንድትመልሽልኝ እፈልጋለሁ... የምናሴ አባት ማነው። ህያብ አንቺም እኮ ድብቅ ነሽ ከኔ የደበቅሺው ብዙ ሚስጥር አለሽ" ዝምምምም

"እንቁን አሟት ነበር ልያት" ከመኝታ ቤታችን ወጥቼ ወደሷ ስሄድ

"እወቂ ለዚህ ሁሉ ነገር ያንቺም እጅ አለበት....ወይኔ አምላኬ ምንድነው ያደረኩት" ሰማሁት ግን ባልሰማ ወደ ልጄ ክፍል ሄድኩ

በሩን ከፈት አድርጌ ሳያት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝታለች ወደ ውስጥ ገባሁና ቀስ አድርጌ ዘጋሁት። የአልጋዋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብዬ የትኛችውን እንቁዬን አየኋት ግንባሯ ላይ ቸፈፍ ያለ ላብ አለ። ፎጣ አንስቼ ስጠርግላት እጄን ለቀም አድርጋ ወረወረችውና

"እባክህ አትንካኝ እባክህ" ከእንቅልፏ ደንግጣ ነቃች

"ምንድነው ልጄ ማንን ነው አትንካኝ የምትይው"

"አይይ እእ....እ

"የምን እእ ነው ምንድነው ንገሪኝ" ለአመታት ስቃዥ የነበረው ትዝ አለኝ... አይ አይሆንም

"በህልሜ የሚያስፈራ ሰው ገደል ውስጥ ሊከተኝ ሲል አየሁ" ኡፍፍፍፍ.... እኔ ደግሞ ስንቱን አሰብኩት

"አሁን እንዴት ነው ቁርጠቱ ተሻለሽ" ዮኒ በሩን ከፍቶ ገባ

"ምን ሆነሽ ነው ምናሴ ብዙ አመመሽ እንዴ ጠዋት እኮ ረፍዶብኝ ሳላይሽ ሄድኩ" የቅድሙን የተፀፀተ ፊት ሳይሆን ፍም እሳት የሚተፋ አይኑን አየሁት... እንቁ ፊቷን አዙራ ተኛች

"ምንድነው አንቺ ባለጌ ለአባትሽ መልስ ስጪው እንጂ" ፊቷን እንዳዞረች

"ደና ነኝ ተሽሎኛል" አለችው። ተነሳሁና ትቻቸው ወጣሁ። ሳሎን ሶፋ ላይ ቁጭ ብዬ ቲቪው ላይ አፈጠጥኩ..... ሀሳቤ ግን ሩቅ ሄዶ ነበር። መች ነው ይሄን ክፍተት የፈጠርኩት... ለራሴ ደግሜ ልነግረው አልፈልግም የምለውን ያን የመደፈር ታሪኬን ከመደበቅ... አዎ ከዛ ነው የጀመርኩት... ከዛ  የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ አልኩት... ከዛ... ከዛ... ከቢኒ ጋር እንኳን ምንም ግንኙነት የለንም... እሱም እንዳስረዳው እድሉን አልሰጠኝም።

ቢዘገይም ነገሮችን አጥርቼ መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ እና ታሪኬን ከአንድ ጀምሬ እነግረዋለሁ ብዬ ወሰንኩ... ግን አሁን አይደለም።

ህያብን ምን ይጨንቃታል ብትሉ ሰውን ተጣልቶ ማኩረፍ እላችኋለሁ። በህይወቴ እንደመኮራረፍ የምጠላው ነገር የለም አኩርፌ ማደርም አልችልም... በቃ ከሰው ጋ ተጋጨሁ አይደል ወይ እዛው ጋ ችግሩን እነግረዋለሁ ወይም ዝም ብዬ አልፈዋለሁ... ብቻ ያስከፋኝም ላስከፋውም ድጋሚ ሳገኘው ያንን ሰው አዋራዋለሁ። ከዮኒጋ በአንድ ጣራ ስር... አንድ አልጋ ላይ እየተኛን በየቀኑ እያየሁት ለማኩረፍ ሞከርኩ ግን አልተሳካልኝም በደሉን ባልረሳውም ሳላስበው አዋራሁት።
6.3K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ