Get Mystery Box with random crypto!

አሮራ (ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል) ምዕራፍ _4 ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ /// መንግ | አትሮኖስ

አሮራ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _4
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
መንግስቱ እግሩን አንቀሰቀሰና ወደ መኪናዋ ፈራ ተባ  በሚል እርምጃ ማዝገም ጀመረ….ከመድረሱ በፊት ገቢናው ተከፈተና አንድ ሰው ከውስጥ ተመዞ ወጣ፡፡እንደእሱ ግዙፍና ፈርጣማ ነው፡፡ፈገግ እያለ ወደእሱ መራመድ ጀመረ….ፈፅሞ አይደለም ከእስር ቤት በወጣ በመጀመሪያው ቀን ይቅርና እድሜ ልክም ዳግመኛ አየዋለሁ ብሎ ያልጠበቀው ሰው ነው፡፡አጎቱ፡፡፡የአባቱ  ታናሽ ወንድም።

"በፈጣሪ ይሄ ሰይጣን ሰውዬ ከየት መጣ?››ብሎ  በውስጡ አጉረመረመ፡፡

አጎቱ ወደእሱ መጓዝ ጀምሯል ...መሀከል መንገድ ላይ ተገናኙ ….እላዩ ላይ ተጠመጠበት።በመንሰፍሰፍ እንደናፈቀው የገዛ ልጁ እያገላበጠ ጉንጮቹን ሳመው፡፡ያለምንም ተቃውሞ እንዳደረገው ሆነለት፡፡እንደዛ መሆን ፈልጎ ሳይሆን እየሆነ ያለው ነገር ፈፅሞ ያልጠበቀውና ያልተዘጋጀበት ስለሆነ ምንም አይነት የተቃውሞም ሆነ የትብብር እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻለም።….

"አንተ በጣም ትልቅ ሰው ሆነህ የለ እንዴ?እንዴ…. ይገርማል..ለማንኛውም ስለተፈታህ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡"አለና እጅን  ትከሻው  ላይ ጣል አድርጎ  አቅፎት ወደ መኪናው ይዞት ሄደ፡፡ወደመኪናው ሲጠጋ ቀድማ እጆቾን በመኪናው መስታወት አውጥታ እያውለበለበች ስትጠራው የነበረች ሴት መኪናውን ለቃ ወረደች፡፡

"ተዋወቃት ባለቤቴ ነች፡፡"

ለስላሳ እጆን ዘርግታ አይኖቾን እላዩ  ላይ  እያንከባለለች፡፡" ውቢት  እባላለሁ፡፡›"አለችው ።ጨበጣትና "መንግስቱ " አላት፡፡
አጎቱ ሻንጣውን ተቀበለና ከኃላውን በራፍ ከፍቶ ከስቀመጠ በኃላ" በሉ ግቡ እንሂድ"አላቸው።
መንግስቱ  የኃላውን በር ሲከፍት‹‹እስኪ ገቢና ከጎኔ ሁን ››አለው፡፡ሚስቱ ወደነበረችበት የኃላ ወንበር ተመልሳ ስትገባ እሱ አጎቱ እንዳለው ዞረና ፊትለፊት ገቢና ገባ ፡፡መኪናዋ ተንቀሳቀሰች፡፡

"ሶስት አመት ስታሰር አንድ ቀን ታሳስቶ እንኳን ያልጠየቀኝ ዛሬ እንዴት ፈለገኝ..?የመፈቻ ቀኔንስ እንዴት አወቀው…..?ወዴት ነው እየወሰደኝ ያለው?፡፡››በውስጡ የተተረማመሱ ካሉ ጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹ ነበሩ…..።ትንሽም የተረጋጋው ሚስቴ ነች ያላት ሴት አብራው ስላላች እንጂ ብቻውን መጥቶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የከፋ ጥርጣሬ በውስጡ ይፈጠር ነገር "ሊያስገድለው ቢሆንስ?"ገንዘብ በጣም እንደሚወድ ያውቃል…ሀብታ ለመሆን የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ ከዚህ በፊት ደጋግሞ አሳይቶታል።የገዛ አባቱ ላይ ብዙ ብዙ ግፍ ሰርቶበታል…..።መአት ብር ከድቶታል….።በዚህም ምክንያት አባቱ ህመምተኛ እንዲሆን ምክንያት ሆኖል ….ህመሙ ደግሞ ወደሞቱ ሸኘቶታል፡፡ያ ማለት በተዘዋዋሪ ይሄ ከጎኑ የተቀመጠው አጎት ተብዬው ሰው የአባቱ ገዳይ ነው፡፡፡እና ዛሬም የሆነ ጥቅም የሚያስገኝለት ከሆነ እሱንም ከማስገደል ወደኃላ እንደማይል እርግጠኛ ነው፡፡፡"ግን እኔን ቢያስገድል ምን ይጠቀማል;?"ብሎ እራሱን ጠየቀ፡፡ከወላጆቹ የወረሰውን ቤት፡፡አዎ ወደደውም ጠላውም…ቀረቤታ ኖረቻውም አልኖራቸውም በአሁኑ ዘንድ በዝምድና ሰንሰለት ለእሱ ከዚህ ከጎኑ ከተቀመጠው ሰውዬ የሚቀርበው ሰው የለም፡፡ስለዚህ እሱ አንድ ነገር ቢሆን   ከወላጀቹ የወረሰውን ቤት ይገባኛል ብለው ከፊት ከሚሰለፉ ሰዎች ዋነኛው ምንአልባትም ብቸኛው ይሄ ሰው ነው፡፡

"ምነው ሀሳብ ውስጥ ገባህሳ…?.አሁን እኮ ሁሉ ነገር አልፏል….መከራዎቹን ሁሉ ከኃላ ጥለሀቸው ወጥተሀል….ይሄንን የነጻነት አየር ተንፍስ››አለው፡፡

"ለጊዜው ምንም አይነት የነፃነት አይር ወደ ውስጤ እየገባ አይደለም….እንደውም መታፈን ነው እየተሰማኝ ያለው።››ሲል መለሠለት።
አይዞኝ ….እስክትለምደው ነው…..ከአንድ ሁለት ቀን በኃላ ሁሉን ነገር አሪፍ ይሆንልህና ማጣጣም ትጀምራለህ… እኔ አጎትህ እንደዛ አይነት የመታፈን ስሜት አንዲሰማህ አላደርግም..እርግጥ በውስጥህ ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ አውቃለሁ….ግን አታስብ ቀስ በቀስ ጥያቄዎችህን ሁሉ እመልስልሀለው….አሁን እቤት ደርሰናል፡፡ቤተሰቡ ሁላ እየጠበቁህ ነው፡፡ልጀቼን አጎታችሁ ከመቀሌ እየመጣ ነው ነው ያልኮቸው።››ሲል ያልጠበቀውን ሌላ ነገር ነገረው።

"ለምን ዋሸሀቸው?››

‹‹ልጆቼ ከእስር ቤት ነው የወጣው ብላቸው….ብዙ ብዙ ጥያቄ ይጠይቁሀል…ምን አልባት እነዛን ጥያቄዎች ለመመለስ አትፈልግም ይሆናል ብዬ አሰብኩ..እናም ለዛ ነው እውነቱን ያልነገርኳቸው።››

"ምን …አንተም ሴት ደፍሮ ነወ የታሰረው ብለህ ታስባለህ እንዴ?"

"አረ በፍፁም….ግን ያው ሆነም ቀረም በሴት ጉዳይ አይደል የታሰርከው፡፡"

"በሴት ጉዳይ አይደለም…በአሮራ ጉዳይ ነው……አሮራ ፍቅሬ ነች ..አሮራ ህይወቴ ነች….ለእሷ ደጋግሜ እታሰርላታለሁ፡፡አባቶ ከእሷ ሊያርቀኝ ሲፈልግ ብሩን ተጠቅሞ የፈጣራ ወንጀል አዘጋጀና ልጄን ሊደፍራት ብሎ ዘብጥያ አስወረወረኝ…..እኔ ግን አሮራን የምደፍርበት ምንም ምክንያት የለኝም….አሮራ እኮ የእኔ ነች..ማለት ውስጤ ነች ፣ልቤውስጥና  ሰርጋ ከነፍሴ ጭምር ተዳብላለች..እራሴን  ሆናለች…ሰው ቢፈልግስ እራሱን እንዴት ሊደፍር ይችላል….?"

"ይቅርታ በወቅቱ ልደርስልህና ከጎንህ ቆሜ ልታገልልህ ባለመቻሌ በጣም ነው የሚቆጨኝ..ግን ሀገር ውስጥ አልነበርኩም ከመጣሁ በኃላ እራሱ  ሁሉ ነገር ከረፈደ በኃላ ነው ስለተፈጠረው ነገር የሰማሁት ..አይዞኝ እክስሀለው፡፡"

"ችግር የለም….በሆነው ነገር ምንም ቅሬታ የለኝም….ግን ከመቀሌ እንደመጣሁ ለምን ነገርካቸው..ማለቴ ከጎንደር ወይም ከሀዋሳ ለምን አላልካቸውም?››ሲል የገረመውን ነገር ጠየቀው፡፡

"አይ  ዩኒቨርሲት የተማርከው መቀሌ ስለሆነ ስለከተማዋ በጣም ታውቃለህ..ምንም ነገር ቢጠይቁህ ሳትጨናነቅ ታስረዳቸዋለህ ...ለዛ ብዬ ነው መቀሌ ያልኳቸው፡፡"

"ጥሩ ነው…..ስለእኔ ይሄን ያህል ማወቅህ አስገርሞኛል።››አለው በዚህን ጊዜ የመኪናዋ የቤታቸው የውጭ አጥር ጋር ደርሳ ክላክስ እያስጮኸች ነበር፡፡

ዘበኛው በራፉን ሲከፍት የቤቱ በረንዳ ሁሉ በሰው ተሞልቶ ነበር…ሁለት መንታ የሚመስሉ ዕድሜያቸው በ15 እና በ16 መካከል ያለ የሚመስል ሴቶች እያተንደረደሩ መጥተው ተጠመጠሙበት..እንዷ ግራ ጉንጪን ስትስም ሌላዋ ቀኝ ጉንጩን ትስመው ነበር….

ምን እየተካሄደ እንዳለ በትክክል መረዳት አልቻለም….ይሄ ሰውዬ የፊልም ዳሬክተር ሆኖ ይሆን እንዴ…?.የሆነ ሪያሊቲ ሾ እየሰራ ያለ ነው የመሰለው፡፡እነዚህን ልጆች አምሰት ወይም ስድስት አመታቸው ላይ አንድ ሁለቴ  እንሱ ቤት መጥተው  ስለነበረ  ትንሽ ትንሽ ትዝ ይሉታል…..ጭራሽ ሳያያቸው ግን አስር አመታት አልፎታል፡፡እነሱ ደግሞ በዛን ወቅት ህፃን ስለነበሩ ሊያስታውሱት እንደማይችሉ እርግጠኛ ነው..ታዲያ ይሄ ሁሉ የናፍቆት የሚመስል የደመቀ አቀባበል ከየት የመጣ ነው?፡፡ደግሞም ምኑም አርቴፊሻል አይመስልም
"እነዚህ ልጆች የዘመድ ረሀብ አለባቸው ይሆን እንዴ?"ሲል በውስጡ አጉረመረመ።

አጎትዬው ሻንጣውን በእጁ አንጠልጥሎ ወደእሱ በመምጣት ከልጆቹ አላቀቀውና…"ልጆች አጎታችሁ ከረጅም ጉዞ ስለመጣ ደክሞታል…ወደክፍሉ ይግባና ሻወር ወስዶ ልብስ ቀያይሮ ተመልሶ ይመጣል..እስከዛ ለምሳ  ዝግጅ እየሆናችሁ ጠብቁት"አለና እጁን ይዞ ወደውስጥ ይዞት ገባ..ሳሎን ሰንጥቀው ከላፉ በሃላ ከኃላ ያሉ ብዙ ክፍሎችን እያለፍ በመሄድ  አንድ የተዘጋ ክፍል ከፍቶ " ግባ ..."እያለው ቀድሞት ገባ፡፡ገዘፍ ያለ የራሱ የሆነ ሻወር ቤት ያለው መኝታ  ክፍል ነው፡፡ ሻንጣውን ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠለትና…". እንግዲህ 30 ደቂቃ እንሰጥሀለን፡፡ሻወር ውሰድ...