አትሮኖስ — የቴሌግራም ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የሰርጥ አድራሻ: @atronosee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 268.45K
ተመሳሳይ ቻናሎች ያልተመደበ
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩ ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል። Contact. @atronosebot please dont touch the leave button.😔😳😳

የቻናል ስታትስቲክስ
0.7% የተሳትፎ መጠን
1,900 እይታዎች / ልጥፍ
0 ልጥፎች / ቀን

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

15 jaan 2023
‹‹ሪች አመሰግናለሁ…..ታውቂያለሽ እኔም ወደሻለሁ…ግን ዳግመኛ እቴቴን አንገት ከማስደፋ እኔ አንገቴን ቀንጥሼ ቢያበቃልኝ እመርጣለሁ….እና ቀድመሽ እዚህ ውሳኔ ላይ ስለደረሽም ሆነ ወደሀገርሽ ተመልሰሽ ለመኖር ስለወሰንሽ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ አታውቂም፡፡ብዙ ነገር ነው ያቃለልሺልኝ፡፡››

‹‹ለማንኛውም የፊታችን እሁድ ሁላችንም እንመጣለን….የዛን ጊዜ ቀሪውን እናወራለን››

‹‹እሺ ሪች ደህና እደሪ…ተአምርን ሳሚልኝ›
‹‹እሺ ደህና እደርልኝ›ስልኩ ተዘጋ…..የሆነ ዥው ነው ያለብኝ፡፡ከሪች የሰማዋቸው ነገሮች ሁሉ ያልጠበቅኮቸውና በጣም ያስደሰቱኝ ናቸው…ከማውቃት የተለየች በሳል ሴት ሆና ነው ያገኘኋት፡፡ሰው በስድስት አመት ይሄን ያህል ይቀየራል….?እኔስ በእሷ መጠን በስዬ ይሆን?.እራሴን የጠየቅኩት ጥያቄ ነበር?መልሱ አኔ እንጃ ነው፡፡

ይቀጥላል
2.2K viewsአትሮኖስ, 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
15 dets 2022
"ሐመር ላይ ሴት ልጅ ማህፀኗ ባዶ ከሆነ አፏ አለብላቢት እንደበላች ፍየል ሰውን ይረብሻል ቅስም ሰባሪ ተስቦ በሽታዋ ሁሉንም ተአጠገቧ ያርቀዋል ከዚያ ተከብቱም ተሰውም በረት ርቃ
ብቻዋን ሆና እህል የማያበቅል እማይጠጣ እንደ በረዶ እየቀዘቀዘ
በመንዠቅዠቅ የማያባራ
ዝናም ላይዋ ላይ እየወረደ ጥርሷን እያፋጨች ስትንቀጠቀጥ እናቷ እንኳ አትደርስላትም"

መከራዋን ስታዳምጥ
ማንጎራጎሩን ከልቦናዋ ትረሳዋለች የኢቫንጋዲ ዳንሱ ትዝታ ሙልጭ ብሎ ይጠፋል . ያን ጊዜ ካርለቴ
የኩራት ክብሩ ቀርቶ ሆደ ባሻነት እንደ ሰንበሌጥ ሣር በውስጥሽ በቅሎ በቅሎ ይውጥሻል" ለሐመር ሴት እውነተኛው ለቅሶ እንደ
አባቷ መፎከሪያ በሬ እየተፎገራች ግረፉኝ ስትል እየተንጠራራ ጎረምሳ በባራዛ አርጩሜ ጀርባዋን ሲሸነቁጣት ሰንበሩ እንደ እባብ ጀርባዋ ላይ ተጋድሞ: ደም ፍጭጭ ሲል ከዐይኗ የሚፈሰው እንባ አይደለም ያማ ስቃይሽን እንዲያጠፋ በአባትሽ ደንብ ከተሞላው
ልብሽ የሚደፋ የሥቃይ ማጥፊያ ውሃ እንጂ ለቅሶ አይደለም ካርለቴ! የኔ እህት  ለቅሶ ማለት የውስጥ ቃጠሎ ነው" ውስጥሽ
የሚንቀለቀልን እሳት ማጥፋት ሲቸግርሽ ነው ወደ እሳቱ የምትደፊው የእንባ ውሃ ስታጭ ነው ..." ሳግ ተናነቃት ጎይቲ
ውስጧ ጤሶ ተቀጣጠለ ካርለት ደነገጠች

"ኦ! ጎይቲ ካርለት ጎይቲ እንዲህ አዝና ተስፋ ቆርጣ አይታት አታውቅም
ሃዘኗ አሸበራት ፊቷ እንደ በሰለ ቲማቲም ቀላ አንጀቷ በኃዘን ተላወሰ ጎይቲ ንፍጧን ተናፍጣ እንባዋን
በአይበሉባዋ ጠርጋ

"እንዲያ ታያ ደልቲና ተጎረምሶች ጋር በየጫካው ስቃበጥ ጓደኞቼ ማህፀናችንን እንፈትሸው' ሲሉ እኔ ውበቴ ጠላት ሆኖኝ
ጨረቃን እያየሁ: እየተጠነቀቅሁ መቅበጥ እንጂ ልቤን ደፍኖኝ
ለማርገዝ አልሞከርኩም ነበር ... ስትል ካርለት ንግግሯን አቋርጣት,

"ጎይቲ ምንድን ነው ደግሞ ማህፀን መፈተሽ'? አለቻት
ጎይቲ ወዘናው በቀነሰ ፈገግታ ፈገግ ብላ "ይእ  አንች ሰው! ምኒቱ
ልብ አድርቅ ነሽ እቴ! ይህን ይህን ታላወቅሽ እህ እሱን ጭሮሽሽን አስደፍኝና ቦርጆን እንዳሁላ
አብቅልልኝ ብለሽ ሳዳጎራሽን አገልድመሽ ተወንዶች ጋራ አደን ውረጂያ!"

"አትሰልችኝ ጎይቲ! ስለማላውቀው እኮ ነው  የምጠይቅሽ?" አለች ካርለት ለጥናቷም ትልቅ ፍንጭ በማግኘቷ ባንድ በኩል ደስ እያላት

"ይእ! አታምርሪ የኔ ሸጋ  ጨዋታየን እንጂ እንኳን ይህን አያ ደልቲና አንች ጫካ ስትገቡ … ብለሽስ
ጠይቀሽኝ መልሸልሽ
የለ ላላወቀ ደግሞ መመለሱ ምኑ ያሰለቻል
ደንብ ነው!" ብላ

"ማህፀን መፈተሽ ማለት ማርገዝ  ማለት ነው በሐመር ልጃገረድ ቀብጣ ስታረግዝ አትጠነቀቅም
ነበር ተብላ ላይ ላዩን
ብትወቀስም ማርገዟ ግን ጥቅም አለው
አባቷንም የሚያስደስት
ፅንሱን ብታስወርድም ማህፀኗ የተቀደሰ ነው' ትባላለች ባልም
እጮኛ ሊያረጋት ይሽሎኮሎካል ያን ጊዜ አባቷ ጥሎሹን ጨምሮ
ይጠይቅባታል፤ ጥሎሽ ከፋዩም ማህፀኗ የተቀደሰ ስለሆነ ይሁን ብሎ ይስማማል" ያን ነው ልጃገረዶች ማህፀን መፈተሽ የሚሉት" ብላ
እሷ ያን ባለማድረጓ መበሳጨቷን እጅዋን በእጅዋ እየደበደበች
አሳየች ካርለት ዐይን ዐይኗን ስታያት ቆይታ

"ጎይቲ መሃን ሴት በምን ትታወቃለች?" አለቻት"

"ይእ! በቀንዷ!" ብላ ጎይቲ ቀለደችና ስትስቅ  ካርለትም
አብራት ሳቀች

"ጎይቲ እየቀለድሽብኝ ነው?"

"ይእ! እህ ምናባቴ ላርግ ካርለቴ  ሴቱ ሁሉ የሚያውቀውን
አንች አዲስ ሆነሽ ስትጠይቂኝ መቀለድሽ አይደለ?"

"የለም ጎይቲ  አልቀለድሁም ቁም ነገር እየተጫወትን
አልቀልድም "

"ይእ! ምን ነበር እቴ የጠየቅሽኝ?"

"መሃን ሴት በምን ትታወቃለች?"

"… በጥንት ጊዜ ቦርጆ እዚሁ እቅርብ ተሐመሮች ጋር ነበር አሉ የሚኖረው" ታዲያልሽ አንድ ጊዜ ከአንዲት ሴት ጋር ይጣሉና
ሴቷ ቦርጆን በጋሊ አርጩሜ ትደበድበዋለች እና በጥፋቷ ያዘነው
ቦርጆ መሐን ሁኝ ብሎ ረገማትና የሐመር ወንዶችን ሰብስቦ  አብሬያችሁ በመኖሬ እየተናናቅን ነው
ዝናብ ስትፈልጉ
ተሰብስባችሁ ጥሩኝ እርስ በርሳችሁ አትጣሉ
ከተጣላችሁ ደግሞ
ሽማግሎች ያስታርቋችሁ
በቡድን ሁናችሁ አትጣሉ
ያገኛችሁትን ተካፍላችሁ እንድትበሉ በራችሁ ቀን ከሌሊት አይዘጋ ካለበለዚያ
ዝናብ አልሰጣችሁም"
ሁሉም ሴቶቻችሁ አይወልዱም
ከብቶቻችሁም አይራቡም በሽታም እልክባችኋለሁ  ብሎ ነው አሉ ርቆ ሰማይ ላይ የወጣው" እና  መሐን ሴት ቦርጆን : ደብድባ
የተረገመች ናት ስትሞት እንኳ ነፍሷ መጀመሪያ እሳት ውስጥ ተዚያ ተተከማቸ ትል ውስጥ ነው አሉ ስትባዝን የምትኖረው ንግግሯን አቋርጣ  ጎይቲ | ስቅስቅ  ብላ  አለቀሰች ካርለት  ጎይቲ ባለችው ባታምንም
“እምነቷ ምን ያህል
እንደረበሻትና ባለመውለዷም የሚጠብቃትን ጣጣ አስታውሳ ለእሷና ለሌሎችም መሐኖች አዘነች" ካርለት   የምታውቀውን ለጎይቲ እንዴት እንደምታስረዳት ስታስብ ቆየችና

"ጎይቲ መሐንነት የትም አገር አልፎ አልፎ አለ ችግሩ ግን
ከሴቷ ብቻ ሳይሆን ከወንዱም ሊመጣ ይችላልኮ" ስትላት ጎይቲ
ቅንድቧን ሽቅብ ሸብሽባ

"ይእ! የባሰው መጣ!
ኧረ ዝም በይ ያገር መሳቂያ
እንዳትሆኝ. የዘራሽው እህል
ባይበቅል ችግሩ ተመሬቱ
ነውዐኸዘሪው?  አንች እውነትም ዝናብ በዝቶበት ፍሬ ያልያዘ ማሽላ ነሽ"
አለቻት" ካርለት በምን ዘዴ እንደምታስረዳት ጨንቋት መላ ፍለጋ መሬቷ ላይ አፈጠጠች

ይቀጥላል
1.6K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ

ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

ስለ አትሮኖስ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

አትሮኖስ 268.45K ተመዝጋቢዎች ያሉት የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ ግምገማዎች፣ ደረጃ እና ዝርዝር ስታቲስቲክስ ይገኛሉ።
በዚህ ገጽ ላይ "ወደ ቻናል ይሂዱ" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ ወይም @atronosee ን በቴሌግራም መተግበሪያ ውስጥ ይፈልጉ። እንዲሁም የቻናሉን የተጠቃሚ ስም ገልብጠው በቴሌግራም መፈለጊያ ውስጥ መለጠፍ ይችላሉ።
አዎ፣ አትሮኖስ ነፃ የቴሌግራም ቻናል ነው። ሁሉንም ልጥፎች ያለምንም ክፍያ መከታተል እና ማንበብ ይችላሉ።
የአትሮኖስ ቻናል በአሁኑ ጊዜ 268.45K ተመዝጋቢዎች አሉት። የተመዝጋቢዎች ቁጥር በመደበኛነት ይዘመናል።
አትሮኖስ ይዘቱን በዋናነት በአማርኛ ቋንቋ ያትማል። መልእክቶቹን ለማንበብ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ ቻናሉን በቴሌግራም ይክፈቱ።
አዎ፣ ተመሳሳይ የያልተመደበ ቻናሎችን ከታች "ተመሳሳይ ቻናሎች" በሚለው ክፍል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ። ተዛማጅ የቴሌግራም ቡድኖችን፣ ቦቶችን እና ተለጣፊዎችንም እናሳያለን።
መልእክቶቹ በቴሌግራም ውስጥ ይነበባሉ፦ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ አትሮኖስ ን ይክፈቱ። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ የተመዝጋቢዎች ብዛት፣ ግምገማዎች እና ስታቲስቲክስ ያገኛሉ።
አትሮኖስ avatar
አትሮኖስ @atronosee
በቴሌግራም ይክፈቱ