Get Mystery Box with random crypto!

አትሮኖስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የሰርጥ አድራሻ: @atronosee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 159.61K
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።
Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-20 18:41:34
• BETTING መበላት ላማረራችሁ ምርጥ ቻናል እንሆ

JOIN ብለዉ ይቀላቀሉን
1.3K viewsEnfalot◢, 15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 08:40:48 አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ልዩ ከመድህኔም ሆነ ከጊፍቲ ጋር በአካልም ሆነ በሰልክ  ከተገናኘች ሁለት ወር ተቆጠረ፡፡ሰሞኑን የምርቃት ሽር ጉድ ላይ ስለሆነች ሀሳቧን ለጊዜውም ቢሆን ከእነሱ ላይ አንስታለች… የሚቀጥለው እሁድ የምረቃ ፕሮግራም አለባት…ነገሩ በገዛ ሴራዋ ድብልቅልቅ ባታደርገው ኖሮ ቀለበቷም ጭምር የሚደረግበት ቀን ነበር፡፡በዚህ ሀሳብና…»
05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 08:40:37 ‹‹ምን አልሺ ጊፍቲ…?››ልዩ ነች ጠያቂዋ
‹‹ሰሞኑን ጥሩ ያልሆኑ ስሜቶች እየተሰሙኝ ስለነበረ ወደእዚህ ከመምጣቴ በፊት ሆስፒታል ሄጄ ተመርምሬ ነበር….እንዳረገዝኩ ነገሩኝ››ብላ ከኪሷ የተሰጣትን የማስረጃ ወረቀት አውጥታ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችው…..ከዛ በኃላ ማንም መናገር የደፈረ አልነበረም…‹‹.ወይኔ ጉዴ መድህኔ ቀድሞኝ በአቆራጭ የልጅ አባት ሊሆን ነው፡፡›ልዩ በውስጧ  በደስታ እየተፍለቀለቀች ያሰበችው የሽሙጥ መሳይ ሀሳብ ነበር ፡፡‹‹ይሄ ለእኔ ያልጠበቅኩት ቦነስ ነው፡፡እነዚህ ሰዎች ከአሁን ወዲህ ከመጋባት ውጭ ምንም ምርጫ የለቸው…፡፡ቃልም ከእኔ ውጭ ሌላ አፅናኝ ከወዴት ያገኛል….?ከየትም፡፡›ስትል በውስጧ በማሰብ በስኬቷ ተመፃደቀች፡፡

ቃልም አውጥቶ አይናገረው እንጂ በሰማው ዜና በውስጡ ተደስቶል ፤‹‹አሁን የጊፍቲን የወደፊት ህይወት በትክክለኛው አይሮፕላን ላይ መሳፈሩን እርግጥ ሆኖል ››አለ..አሁን እነሱን ገፋፍቶ ወደትዳር እንዲገቡ ማድረግ ለእሱ በጣም ቀላል ስራ ነው…ከዛ በገባው ቃል መሰረት እራሱን ሙሉ ለሙሉ ከመሰወሩ በፊት ልዩን ከሌብነት አመሏ ማላቀቅ ብቻ ነው የሚቀረው ለዛ ደግሞ በቂ የሚባል ጊዜ አለው…‹‹ጊፍቲና መደህኔ ላይ በሰራችው የብልጠት ሴራ  ቅጣቷን የምተታገኝ ቢሆንም በእሷ ስህተት ባልሆነ ጉዳይ ከገባችበት የሌብነት  ጣጣ ግን መፈወስ አለባት›› ሲል በማሰብ ቀድሞ ውሳኔውን ዳግም አፀደቀ ፡፡
ጊፍቲና መድሀኔ ግን ዜናውን ተከትሎ ምን እየተሰማቸው እንደሆነ ?እያዘኑ ይሁን ወይስ እየተደሰቱ? እራሳቸውም አያውቁትም…ሁለቱም ደንዝዘው እርስ በርስ በፍዘት  እየተያዩ ነው፡፡

ይቀጥላል
2.7K viewsአትሮኖስ, 05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 08:40:36 #ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ልዩ ከመድህኔም ሆነ ከጊፍቲ ጋር በአካልም ሆነ በሰልክ  ከተገናኘች ሁለት ወር ተቆጠረ፡፡ሰሞኑን የምርቃት ሽር ጉድ ላይ ስለሆነች ሀሳቧን ለጊዜውም ቢሆን ከእነሱ ላይ አንስታለች…

የሚቀጥለው እሁድ የምረቃ ፕሮግራም አለባት…ነገሩ በገዛ ሴራዋ ድብልቅልቅ ባታደርገው ኖሮ ቀለበቷም ጭምር የሚደረግበት ቀን ነበር፡፡በዚህ ሀሳብና ሁኔታ ላይ እያለች ነበር ትናንት ማታ ቃል ደውሎ ነገ በስድስት ሰዓት እሱ ቤት እንድትመጣ የነገራት።ምክንያቱን ስትጠይቀው ‹‹ስትመጪ ትደርሺበታለሽ›› አላት። በዚህም የተነሳ ልቧ እንደተንጠለጠለ መሽቶ ነጋ።

ሁል ጊዜ ቃል ፈልግሻለሁ ባላት ቁጥር ለምንድነው ልቧ   የምትቅበዘበዘው? ሁሌ የማይገባት ጉዳይ ነው… አምስት  ተኩል ሲሆን ነው አምራና ተሸቀርቅራ እቤት የደረሰችው....እቤቱ የቀጠራት የፍቅር ጥያቄ ሊጠይቃት እንደሆነ 90 ፐርሰንት እርግጠኛ ነች...እሱ ደፍሮ ባይጠይቃት እንኳን ትንሽ ፍንጭ ካሳያት እሷ ገፍታበት የውስጧን ዘክዝካ ልትነግረውና የዘላለም ፍቅረኛዋ እንዲሆን ልትጠይቀው አስባበትና ተዘጋጅታበት ነው የመጣችው፡፡ ስትደርስ ቤቱ በምግብ ሽታ ታውዷል "ስትገባ በሞቀ ፈገግታና  ሠላምታ ተቀበላት የሚሰራውን ምግብ ገና ስለነበረው ታግዘው ጀመር..እየተዘጋጀ ያለው የምግብ ብዛት ግን ለሁለቱ ብቻ አልመስል አላትና ደባሪ ስጋት በእምሮዋ ሽው አለባት…እሱን ጠይቃ ለማረጋገጥ ግን አልፈለገችም፡፡ስድስት ሰዓት ሲሆን በራፍ ተቆረቆረ..‹‹ ሂጂና ክፈቺ ››አለት፡፡ የቃል የቤት አከራዮ ናቸው በሚል ግምት ቂው ቂው እያለች ሄዳ ስትበረግደው  ፊቷ የተጋረጠው ሰው ያልጠበቀችው ነበር..ልክ እንደናፈቀ ሰው  ተንደርድራ ልትጠመጠምባት ነበር.. ለጥቂት ነው ትውስታው በአዕምሮዋ ብልጭ ሲል  እራሷን የገታችውና..እንደመመናቀር ብላ በራፋን በመልቀቅ ወደውስጥ የተመለሰችው...፡፡እሷ ካለች ቃላ ላሰበችው ነገር እንዳልጠራት አወቀችና በጣም ተከፋች….

"ማነው?"ጠየቃት ቃላ..አልመለሰቸለትም ዝም አለችው   ..ቃል ግን ወዲያው ገባውና  የሚሰራውን ምግብ አቋሞ ወጣ ""ጊፍቲ..እንኳን በሰላም መጣሽ" "ብሎ ተጠመጠመባት ..አገላብጦ ሳማት...ጊፍቲ ቅዝቅዝና ቅዝዝ ባለ ስሜት አፀፋዋን መለሰች ..ወስዶ ምግብ የተደረደረበት ጠረጴዛ አካባቢ አስቀመጣትና ትኩር ብሎ አያት ..ባለፈው ካያትም በላይ ጉስቁልና ጥቁርቁር ብላለች…ውስጡ አዘነ..ፊቱን አዙሮ ወደ ልዩ እየተራመደ ሳለ  በራፉ ዳግመኛ ተቆረቆረ...ልዩ ባለችበት ግራ ተጋባች ‹‹ዛሬ ምንድነው .? ›ስትል አጉረመረመች….ሄዶ ከፈተው።

"ኦ መድሀኔ ...እንኳን በሰላም መጣህ… ግባ›› ሲል ልዩ ሠማች ባለችበት ሽምቅቅ ነው ያለችው፡፡

‹‹ወይ ጉዴ ጭራሽ ያን ሁሉ የለፋሁበትን ነገር ገደል ከተተው..ይሄ ልጅ ምን እየሠራ ነው? ። እንዲህ በድንገት አንድ  ቤት የሠበሰበን ሊያቧቅሰን ነው ወይስ ሊያስታርቀን?ሊያስታርቀን ከሆነ በምን መልኩ።እንደድሮችን እንድንጣመር ወይስ በአዲስ አሰላለፍ...?››በደቂቃ ውስጥ አእምሮዋ ውጥርጥር አለ።
ከዛ የተሰራው ምግብ ሁሉ ጠረጴዛው ላይ ቀረበ...ሁሉም በተኳረፈ ስሜት ቢሆኑም ጠረጴዛውን ከበው ተቀመጡ.የቀረበውን ምግብ በልተው አጠናቀቁና የተበላበትን ሰሀኖች ተገጋዘው በማንሳት መልሰው በጠረጴዛው ዙሪያ ተቀመጡ።በዛ በውጥረት ውስጥ የመናገር  ቅድሜያውን የወሰደው  ቃል ነው።

ያው እንግዲህ  ሁላችንንም  እዚህ  ለምን እንድንገናኝ እንደፈለኩ ታውቃላችሁ።ባታውቁም መገመት አይከብዳችሁም፡፡ በመካከላችን ደስ የማይል ነገር ተፈጥሯል። እንደድሮችን እርስ በርስ አንገናኝም፤አንደዋወልም ይሄ ከዛሬ ጀምሮ በዚህ አይነት ሁኔታ መቀጠል የለበትም።

ልዩ ጣልቃ ገባች"ቃል እነሱ በእኛ ላይ የፈፀሙት በደል እኮ መቼም ይቅርታ የሚያሰጥ አይደለም" ተንዘረዘረች.አዎ በተቻላት አቅም ነገሩን ከመጀመሩ በፊት ልታስቆም እየጣረች ነው፡፡

ቃል ግን ቀድሞውንም ይሄን ገምቶ የተዘጋጀበት ጉዳይ ስለነበር በጥንካሬ ተጋፈጣት‹‹አይ… ይቅርታ የማያሰጥ አንድም በደል  የለም...ደግሞ በግንኙነት ውስጥ አንድ በአንድ ነገር ሲበድል  ሌላው ደግሞ በሌላ መበደሉ አይቀሬ ነው...ስለዚህ እሱ የበደለው ይቅር እንዲባልለት እሱ ቀድሞ  የጓደኛውን በደል  ይቅር ማለት አለበት።ጊፉቲ  አንቺ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ሰው እንደሆንሽ ታውቂያለሽ  ።ለሁለታችንም ግንኙነት ብዙ ብዙ መስዋአትነት ከፍለሻል..አንቺ በጣርሺው መጠን እኔ አልጣርኩም.. በዛም በጣም አዝናለሁ...እባክሽ  በውስጥሽ ለፈጠርኩት መጥፎ ስሜት በአጠቃላይ ከልብሽ ይቅር እንድትይኝ እፈልጋለሁ"በማለት ከመቀመጫው ተነሳና በተቀመጠችበት እዛው ይዞ ጉልበቷ ላይ ተደፋ...እሷም እጇን ጭንቅላቱ ላይ አድርጋ ፀጉሩን እያሻሸች ትነፈርቅ ጀመር..

መድሀኔ እንደፈዘዘ ነው። ልዩ ግራ ገብቶታል‹‹ ምንድነበር የተፈጠረው?ማን ነው ማንን ይቅርታ መጠየቅ ያለበት.....?እኔም ተነስቼ መድሀኔ እግር ስር ልደፋ እንዴ?›እያለች ስትብሰለስል በድንገት መድሀኔ ከተቀመጠበት ተነሳና መጥቶ እግሯ ስር ድፍት አለ"እባክሽ ልዩ በተፈጠረው ነገር በጣም አፍሬለሁ።እንዴት እንደዛ እንዳደረኩ አላውቅም ።በእውነት በዛ ስካርና የእብደት ቀን ከተፈጠረው ውጭ እምልልሻለሁ በእኔና በእሷ መካከል ምንም የለም...አንቺ መስለሺኝ እሷንም ያሳሳትኳት እኔ ነኝ።በዚህም ሶስታችሁም ይቅር እንድትሉኝ እፈልጋለሁ።

"በቃ ተነስ ይቅር ብዬሀለው ....ከአሁን ጀምሮ ግን ንፅህ ጓደኛሞች ነን"አለችው ፈርጥም ብላ..ፈጥና ይቅር ያለችው ሆነ ብላ የቃልን ትኩረት ለመሳብ ስለፈለገች ነው፡፡ባለፈው ከቃል ጋር ስለዚህ ጉዳይ ሲያወሩ እንዲ እንድታደርግ ስለነገራት ምን ያህል የእሱን ቃል አክባሪ እንደሆነች እንዲያቅላት ስለፈለገች ነው

መድሀኔ ግን ከፊል በሆነው ይቅርታዋ እርካታ አልተሰማውም.በልመናው ገፈበት"እባክሽ ልዩ እኔ እኮ በጣም ነው የማፈቅርሽ በዛ ላይ የሁለታችንም ቤተሠቦች ለሠርጋችን እየተዘጋጅ እኮ ነው።ይቅር ብለሺኝ እንደበፊቱ ካልሆን ምን ልንላቸው ነው።"

"አይ እንደዛማ ፍፅም አይሆንም...እኔ ለቤተሠቦቼ አንተን እንደማላገባ ነግሬቸው ዝጎጅታቸውን አቋርጠዋል...አንተም ጊዜውና ሳይረፍድ ዛሬውኑ ለቤተሠቦችህ ንገራቸው።

"ምን ብዬ.ቀለበቱን እንኳን እንዲቀር ለማድረግ ስንት ነገር ቀባጥሬ ነው…ከእነጭራሹ ሰርጉም ጭምር ቀርቷል ብላቸው ኸረ በስመአብ?"ዘገነነው

"እሱ ያንተ ችግር ነው..."

"ቃል አረ አንድ ነገር በላት...ቆይ አንተ ጊፍቲን በፍቅረኝነት አትቀበላትም።"ሲል አንጀት በሚበላ ድምፅ ጠየቀው

ልዩ የቃልን መልስ ለመስማት አይኖቾን አፍጥጣበት በጉጉት ትጠብቅ ጀመር..የፈራችውን አይነት መልስ መለሰ"ለምን አልቀበላትም የይቅርታ ግማሽ የለውም እኮ"

በቃል ንግግር ወሽመጧ ብጥስ አለ‹‹...ምን አይነት ሀሞት የሌለው ሰው ነው...የወራት ልፋቴን በጠቅላላ ገደል ሊከተው እኮ ነው.. አሁን እሺ ምን ላድርግ?።›በውስጧ አብሰለሰለች.ሀሞትና ከርቤ ቀላቅላ እንደተጋተ ሰው .አፏን መረራት…፡፡መድህኔ ተፍለቀለቀ...ግን የልዩ ብስጭት ሆነ የመድሀኔ ደስታ ለሽርፍራፊ ሰከንድ ብቻ ነው መቆየት የቻለው።ድንገት የመብረቅ ብልጭታ በሚመስል ክስተት ታአምር መሳይ ዜና ከጊፊቲ አንደበት ዱብ አለ"አርግዤለሁ"አለች...መድህኔ በተንበረከከበት ዝርፍጥ ብ ሎ መሬት ያዘ
2.7K viewsአትሮኖስ, 05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 08:25:33 አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ይሄን ሁሉ ወሬ ያወሩት አንድ ሬስቶራንት ገብተው እራት እየበሉ ነው።ሰዓቷን ስታይ 2:30 ሆኗል።መኪና ስለያዘች ወደቤት ለመሄድ ሰዓቱ ገና ነው..ግን መሄድ አልፈለገችም.....፡፡ "ቃልዬ ...ዛሬ አንተ ጋር ማደር እችላለሁ?"ስትል ጠየቀችወ፡፡ "ችግር የለውም ...ግን እቤት ቅር እንዳይላቸው፡፡››አላት፡፡ ‹‹አይ .እሱን…»
05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 18:00:05 #ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ይሄን ሁሉ ወሬ ያወሩት አንድ ሬስቶራንት ገብተው እራት እየበሉ ነው።ሰዓቷን ስታይ 2:30 ሆኗል።መኪና ስለያዘች ወደቤት ለመሄድ ሰዓቱ ገና ነው..ግን መሄድ አልፈለገችም.....፡፡
"ቃልዬ ...ዛሬ አንተ ጋር ማደር እችላለሁ?"ስትል ጠየቀችወ፡፡
"ችግር የለውም ...ግን እቤት ቅር እንዳይላቸው፡፡››አላት፡፡
‹‹አይ .እሱን እኔ አስተካክላለሁ… ችግር የለውም››አለችው፡፡
ከሆነ እሺ ›አለና ተያይዘው ወደ ቃል ቤት አመሩ፡፡
እራታቸውን ውጭ ስለበሉ ቀጥታ ወደ መኝታ ቤት ነው ያመሩት።ያው እንደ ለማዳነቷ አልጋው ላይ ተቀመጠች.. ቃል ቀጥታ ወደ ቁምሳጥኑ ሄደና ከፍቶ ልብሶችን እያነሳ እየጣለ‹‹ ...የእኔን ቢጃማ ብሰጥሽ ይደብርሻል...ከታጠበ በኃላ አለበስኩትም" አለት.፡፡.
ግን.‹‹ወይ አለመተዋወቅ›አለች በውስጧ ቃል ያላወቀው እንደውም ለብሶት ሙሉ በሙሉ ጠረኑ እንደተጣበቀበት ቢሆን እርካታዋ ወሰን አልባ ይሆን እንደነበረ ነው...‹‹ምን ያደርጋል ይሄንን ግን እሱ አይረዳለኝም›ስትል በውስጧ አማረች፡፡በጣም በጥልቀት እንደሚረዳትና ግን ደግሞ አውቆ ያልተረዳት እያስመሰለ እንደሆነ ቢገባትስ ምን ትል ይሆን?፡፡
"አረ ችግር የለውም ..ስጠኝ ደስ ይለኛል"አለችው..ነጭ ቢጃማ ሱሪ ከነአላባሹ አቀበላት ...ተቀበለችና ጎኗ አስቀመጠችው"አሁን እንዴት ነው የለበስኩትን አውልቄ ይሄን የምለብሰው ...ቀሚስ ለብሼ ቢሆን እንኳን ቀላል ነው ...ግን አሁን የለበስኩት ሱሪ ነው...ቃል ፊት ሱሪዬን አውልቄ በፓንት ቆሜ ቢጃማ መልበስ...‹አይ ወደ መታጠቢያ ክፍል ልግባና እዛ ልቀይር›ብላ በማሰብ ወሰነችና...መልሳ ሀሳቧን ሰረዘችው፡፡
‹‹እዚሁ እሱ ፊት ነው መቀየር ያለብኝ...እኔ በገዛ እጮኛው ባሌን የተነጠቅኩ እና ልቤ የተሠበረ ንክ ነኝ ...ቢያንስ እሱ እንደዛ ነው የሚያውቀው እና ምንም ነገር ባደርግ በሀዘኔታ ከማየት ውጭ ምን ማለት ይችላል...?ለዛውስ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች እየተጠቀምኩ ልብን ካልሸራረፍኩ እንዴት ነው ትልቁ እቅዴ ጋር የምደርሰው፡፡››በማለት እራሷን አበረታታችና ተነሳች፡፡ ቆመች፡፡ በአንድ ሜትር ርቀት ፊት ለፊቷ ነው ያለው...የጂንስ ሱሪዋን ቁልፍ ፈታ ዚፑን ወደታች ሳታንሸራትት እሱ እጅ ላይ ያለውን ሌላ ሰማያዊ ቢጃማ ይዞ ፊቱን አዙሮ ወደሚቀጥለው ክፍል ገባ....እንግዲህ ይሄ ማለት አልማችሁ ልትተኩሱ ቃታውን ስትስብ ቃ..ቃ ብቻ ብሎ ሲከሽፍባችሁ የሚሠማችሁን ስሜት በሉት።‹‹አይ ቃል አሁን የእኔን ከፊል እርቃን ላለማየት ካልሆነ በስተቀር የአንተንማ...እያንዳንድን የሠውነት አካሉን ማንም ሌላ ሰው ካየው በላይ አገላብጪ አይቼዋለሁ...እድሜ እዚህ ክፍል ለቀበርኳት ስውር ካሜራ ...የማርያም ስሞሽ ጥቁር ነጥብ ምልክት የት የት ጋር እንዳህ...በሰውነትህ ላይ ያለው ፀጉር የት ጋር እንደሚበዛ እና የት ጋር እንደሚሳሳ... የደረትህን መጠነ ስፋት እና የእንብርትህን ጉዶጓድ ጥልቀት ጭምር አውቃለሁ....እናም ይበልጥ ሚስጥራዊ ስለሆኑ የሠውነት ክፍሎቹም ርዝመትና እጥረት፤ ውፍረትና ቅጥነት በዝረዝር መናገር እችላለሁ...ቃል ግን ይሄንን ቢያውቅ ምን ይላል..." እያለች ስለራሷ የሚስጥር ጎተራነት በኩራት እያሰበች ባለችበት በዛው ደቅቃ ቃልም የእሷን እያንዳንዷን እርቃን የሰውነት ክፍሏን በተለያየ ቀን ክፍሉ ተቀምጦ ላፕቶፐ ላይ እየመጣለት ደጋሞ ያየውንና ያጠናውን በምልስት እየከለሰ በፈግታ ተሞልቶ ነበር ልብሱን እየለበሰ ያለው..
ሲጨርስ የመኝታ ቤቱን በራፍ አንኳኳ..
"ቃል ግባ ጨርሼያለሁ"አለችው፡፡ከፍቶ ገባ...ጨርሳ ከውስጥ ገብታ ተኝታ ነበር...
"ተኛሽ እንዴ?"
‹‹አዎ…ምነው?›› ምነው አባባሎ .ከመተኛቷ በፊት እንድታደርግለት ወይም እንድትሰጠው የሚፈልገው ነገር ካለ ብላ ነው፡፡
"አይ ምንም›› አለና እሱም እንደእሷው ተኛ .. በመሀከላችን የአንድ ክንድ ክፍተት ቢኖርም እሷም ወደ እሱ ዞራ እሱም ወደእሷ ዞሮ ፊት ለፊት እየተያየን ነበር የተኙት፡፡
"እንዴት ነው አሁን ተረጋጋሽ?›
‹‹ አዎ..ዕድሜ ላንተ ምንም አልል "አለችው…
‹‹ እጅሽን ስጪኝ ?››አለት.
ለምን እንደፈለገው ግራ ቢገባትም ቀኝ እጇን ሰጠችው.. በግራ እጅ ጨበጠው…‹‹ ያኛውንም›› አላት …በተመሳሳይ ሰጠችው… በሌለኛው እጅ ጨበጠው....ሰውነቷን ውርር አደረገው....ዛሬ ነገሮች መልካቸውን ሊቀይሩ ነው ስትል በውስጧ አሰበች ..ግን ወዲያው ነበር ሀሳቧ የተወላገደና የተሳሳተ መሆኑን የተረዳችው..."ከመተኛታችን በፊት በቀን ውሎችን ስላተሰጠን በጎ ነገር ሁሉ እንድናመሠግን ፈልጌ ነው"አለ
"ተኝተን?"
"ችግር የለውም …ዎናው ልባችን አለመተኛቱ ነው"
‹‹እሺ እንዳልክ ››አለችና እራሷን ዝግጅ አደረገች...አይኖቹን ጨፈነና ማነብነብ ጀመረ.. ከተወሰኑ ደቂቆች በኃላ የሚላቸውን ነገሮች በግልፅ መስማት አቁማ ነበር ... የሆነ የሚያንሳፍፍ አይነት መመሰጥ ውስጥ ገብታ እየቀዘፈች ነው። ሰውነቷ ሲላቀቅና ሲፍታታ፤ እናም ክብደት አልባ ሲሆን እየታወቀት ነው።አእምሮዋ ውስጥ የሆኑ የብርሀን ፍንጥርጣሪዎች ሲደንሱ ይሰማታል፡፡
...ቃል የምስጋና ፀሎቱን አጠናቆ እጆቾን ቢለቃቸውም እሷ ግን ቀጥላለች...አይኖቾ እንደተጨፈኑ አንደበቶም እንደተዘጋ ቢሆንም ውስጧ ግን እያነበነበ ነው።
‹‹…ቃልዬ አንተን መተዋወቄን እንደመባረክ ነው የምቆጥረው..አንተ ውስጤ ተደፍኖ የኖረውን እሳት የምታወጣልኝ የፍቅሬ ነዳጅ ነህ..አሁን እየተነፈስክ ያለኸው ትንፋሽህ ወደ ውስጤ ሰርጎ ሲገባ ኃይለኛ የኤሌክትሪክ ሞገድ በውስጤ ፈጥሮ ሲያንዘፈዝኝ ይታወቀኛል...ከንፈርህ ከንፈሬ ላይ ባይጣበቅም በጥልቀት ነፍስህ ድረስ ጠልቄ እየሳምኩህ ነው።እጆችህ እርቃን ሰውነቴ ላይ አርፈው እየዳበሱኝ ባይሆንም እኔ በፍቅርህ ቅልጥልጥ ብዬ እየተዝለፈለፍኩ ነው... ቢጃማዬንና ፓንቴን አውልቀህ ጥለህ ጭኔን ፈልቅቆ ውስጤ ለመግባት ባትሞክርም እግሮቼ ተከፋፍተው ሴትነቴ ረጥቦልህ እየቃተትኩ ነው...እንዲህ አይነት ፍቅር ማንንም አፍቅሬ አላውቅም.. እንዲህ አይነት ወሲብ ከማንም ተዋስቤ አላውቅም ...እንዲህ አይነት ስጋንም ነፍስንም በአንዴ ከፀባኦት አድርሶ የመመለስ አይነት የጦዘ እርካታ ማንም እንድረካ አድርጎኝ አያላውቅም..ወደፊትም ማድረገግ አይችልም…፡፡አንተ ግን..አንተ ግን...አንተ ግን ለስንት ጊዜ እንደደጋገመችው አታውቅም…ሰውነቷን ተርገፈገፈ..ጭው አለባት...ለአስር ደቂቃ በኃላ አይኖቾን መግለጥ ቻለች ...ቃል ርቀቱን እንደጠበቀ ጭልጥ ያለ ሠላማዊ እንቅልፍ ውስጥ ነው...እሷ ግን ምን ውስጥ ገብታ ነው የወጣችው ?የምታውቀው ነገር አልነበረም‹‹ቆይ አንድ የሚወድትን ሰው አጠገብ ተኝተው ግን ደግሞ ጫፍን ሳይነኩት በሀሳብ እያለሙ ብቻ ፍቅር መሰራት…ከዛም በተግባር የመጨረሻውን እርካታ መርካት ይቻላል እንዴ?እንዲህ አይነት ተአምር የትኛውም የፍቅር ፊልም ላይ ሆነ መፅሀፍ ሊይ አላነበብኩም….አሁን ቃል ምን አስቤ ምን እንደሰራው ቢያውቅ እንዴት ይታዘበኛል...?››ስትል ራሷን ጠየቀች…ፊቷን ከእሱ መለሰችና ጀርባዋን ሰጥታው ጥቅልል ብላ ተኛች...ደስ የሚል ሠላማዊ እንቅልፍ።


ይቀጥላል
6.0K viewsአትሮኖስ, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 23:57:02 መንታ ልቦች :
አፍቃሪ ሆነክ ይሄ ቻናል ከሌለክ እመነኝ አንተ እውነተኛ አፍቃሪ አይደለህም
125 viewspetelare Stay true, 20:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 23:46:05 የፍቅረኛችሁን   ሰው   ስም   የመጀመርያ ፊደል   በመጫን   የምታገኙትን   የፍቅር ቻናል   ተጋበዙልኝ ︎


ዳይ ለሁላችሁም ነው እንዳያመልጥዎ!!
219 viewspetelare Stay true, 20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 23:42:31
የምትወዳትን ልጅ ስታገኝ የምታወራው ይጠፋብሀል


ከስር ነበብ ነበብ አርገህ ፍጠንባት

ወንድ እስከሆንክ ድረስ ቀልጠፍ ማለት አለብህ


ከስር  view የሚለውን በመጫን ያገኙታል
113 viewspetelare Stay true, 20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 23:17:34
እርግጠኛ ነኝ ፎቶ ለመነሳት ፈልገው የአነሳስ style ጠፍቶብዎት  ተቸግረው ያውቃሉ።የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው
https://t.me/+t6zF26yaxWUxNmE0
56 viewspetelare Stay true, 20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ