Get Mystery Box with random crypto!

#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ልዩ ከመድህኔም | አትሮኖስ

#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ልዩ ከመድህኔም ሆነ ከጊፍቲ ጋር በአካልም ሆነ በሰልክ  ከተገናኘች ሁለት ወር ተቆጠረ፡፡ሰሞኑን የምርቃት ሽር ጉድ ላይ ስለሆነች ሀሳቧን ለጊዜውም ቢሆን ከእነሱ ላይ አንስታለች…

የሚቀጥለው እሁድ የምረቃ ፕሮግራም አለባት…ነገሩ በገዛ ሴራዋ ድብልቅልቅ ባታደርገው ኖሮ ቀለበቷም ጭምር የሚደረግበት ቀን ነበር፡፡በዚህ ሀሳብና ሁኔታ ላይ እያለች ነበር ትናንት ማታ ቃል ደውሎ ነገ በስድስት ሰዓት እሱ ቤት እንድትመጣ የነገራት።ምክንያቱን ስትጠይቀው ‹‹ስትመጪ ትደርሺበታለሽ›› አላት። በዚህም የተነሳ ልቧ እንደተንጠለጠለ መሽቶ ነጋ።

ሁል ጊዜ ቃል ፈልግሻለሁ ባላት ቁጥር ለምንድነው ልቧ   የምትቅበዘበዘው? ሁሌ የማይገባት ጉዳይ ነው… አምስት  ተኩል ሲሆን ነው አምራና ተሸቀርቅራ እቤት የደረሰችው....እቤቱ የቀጠራት የፍቅር ጥያቄ ሊጠይቃት እንደሆነ 90 ፐርሰንት እርግጠኛ ነች...እሱ ደፍሮ ባይጠይቃት እንኳን ትንሽ ፍንጭ ካሳያት እሷ ገፍታበት የውስጧን ዘክዝካ ልትነግረውና የዘላለም ፍቅረኛዋ እንዲሆን ልትጠይቀው አስባበትና ተዘጋጅታበት ነው የመጣችው፡፡ ስትደርስ ቤቱ በምግብ ሽታ ታውዷል "ስትገባ በሞቀ ፈገግታና  ሠላምታ ተቀበላት የሚሰራውን ምግብ ገና ስለነበረው ታግዘው ጀመር..እየተዘጋጀ ያለው የምግብ ብዛት ግን ለሁለቱ ብቻ አልመስል አላትና ደባሪ ስጋት በእምሮዋ ሽው አለባት…እሱን ጠይቃ ለማረጋገጥ ግን አልፈለገችም፡፡ስድስት ሰዓት ሲሆን በራፍ ተቆረቆረ..‹‹ ሂጂና ክፈቺ ››አለት፡፡ የቃል የቤት አከራዮ ናቸው በሚል ግምት ቂው ቂው እያለች ሄዳ ስትበረግደው  ፊቷ የተጋረጠው ሰው ያልጠበቀችው ነበር..ልክ እንደናፈቀ ሰው  ተንደርድራ ልትጠመጠምባት ነበር.. ለጥቂት ነው ትውስታው በአዕምሮዋ ብልጭ ሲል  እራሷን የገታችውና..እንደመመናቀር ብላ በራፋን በመልቀቅ ወደውስጥ የተመለሰችው...፡፡እሷ ካለች ቃላ ላሰበችው ነገር እንዳልጠራት አወቀችና በጣም ተከፋች….

"ማነው?"ጠየቃት ቃላ..አልመለሰቸለትም ዝም አለችው   ..ቃል ግን ወዲያው ገባውና  የሚሰራውን ምግብ አቋሞ ወጣ ""ጊፍቲ..እንኳን በሰላም መጣሽ" "ብሎ ተጠመጠመባት ..አገላብጦ ሳማት...ጊፍቲ ቅዝቅዝና ቅዝዝ ባለ ስሜት አፀፋዋን መለሰች ..ወስዶ ምግብ የተደረደረበት ጠረጴዛ አካባቢ አስቀመጣትና ትኩር ብሎ አያት ..ባለፈው ካያትም በላይ ጉስቁልና ጥቁርቁር ብላለች…ውስጡ አዘነ..ፊቱን አዙሮ ወደ ልዩ እየተራመደ ሳለ  በራፉ ዳግመኛ ተቆረቆረ...ልዩ ባለችበት ግራ ተጋባች ‹‹ዛሬ ምንድነው .? ›ስትል አጉረመረመች….ሄዶ ከፈተው።

"ኦ መድሀኔ ...እንኳን በሰላም መጣህ… ግባ›› ሲል ልዩ ሠማች ባለችበት ሽምቅቅ ነው ያለችው፡፡

‹‹ወይ ጉዴ ጭራሽ ያን ሁሉ የለፋሁበትን ነገር ገደል ከተተው..ይሄ ልጅ ምን እየሠራ ነው? ። እንዲህ በድንገት አንድ  ቤት የሠበሰበን ሊያቧቅሰን ነው ወይስ ሊያስታርቀን?ሊያስታርቀን ከሆነ በምን መልኩ።እንደድሮችን እንድንጣመር ወይስ በአዲስ አሰላለፍ...?››በደቂቃ ውስጥ አእምሮዋ ውጥርጥር አለ።
ከዛ የተሰራው ምግብ ሁሉ ጠረጴዛው ላይ ቀረበ...ሁሉም በተኳረፈ ስሜት ቢሆኑም ጠረጴዛውን ከበው ተቀመጡ.የቀረበውን ምግብ በልተው አጠናቀቁና የተበላበትን ሰሀኖች ተገጋዘው በማንሳት መልሰው በጠረጴዛው ዙሪያ ተቀመጡ።በዛ በውጥረት ውስጥ የመናገር  ቅድሜያውን የወሰደው  ቃል ነው።

ያው እንግዲህ  ሁላችንንም  እዚህ  ለምን እንድንገናኝ እንደፈለኩ ታውቃላችሁ።ባታውቁም መገመት አይከብዳችሁም፡፡ በመካከላችን ደስ የማይል ነገር ተፈጥሯል። እንደድሮችን እርስ በርስ አንገናኝም፤አንደዋወልም ይሄ ከዛሬ ጀምሮ በዚህ አይነት ሁኔታ መቀጠል የለበትም።

ልዩ ጣልቃ ገባች"ቃል እነሱ በእኛ ላይ የፈፀሙት በደል እኮ መቼም ይቅርታ የሚያሰጥ አይደለም" ተንዘረዘረች.አዎ በተቻላት አቅም ነገሩን ከመጀመሩ በፊት ልታስቆም እየጣረች ነው፡፡

ቃል ግን ቀድሞውንም ይሄን ገምቶ የተዘጋጀበት ጉዳይ ስለነበር በጥንካሬ ተጋፈጣት‹‹አይ… ይቅርታ የማያሰጥ አንድም በደል  የለም...ደግሞ በግንኙነት ውስጥ አንድ በአንድ ነገር ሲበድል  ሌላው ደግሞ በሌላ መበደሉ አይቀሬ ነው...ስለዚህ እሱ የበደለው ይቅር እንዲባልለት እሱ ቀድሞ  የጓደኛውን በደል  ይቅር ማለት አለበት።ጊፉቲ  አንቺ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ሰው እንደሆንሽ ታውቂያለሽ  ።ለሁለታችንም ግንኙነት ብዙ ብዙ መስዋአትነት ከፍለሻል..አንቺ በጣርሺው መጠን እኔ አልጣርኩም.. በዛም በጣም አዝናለሁ...እባክሽ  በውስጥሽ ለፈጠርኩት መጥፎ ስሜት በአጠቃላይ ከልብሽ ይቅር እንድትይኝ እፈልጋለሁ"በማለት ከመቀመጫው ተነሳና በተቀመጠችበት እዛው ይዞ ጉልበቷ ላይ ተደፋ...እሷም እጇን ጭንቅላቱ ላይ አድርጋ ፀጉሩን እያሻሸች ትነፈርቅ ጀመር..

መድሀኔ እንደፈዘዘ ነው። ልዩ ግራ ገብቶታል‹‹ ምንድነበር የተፈጠረው?ማን ነው ማንን ይቅርታ መጠየቅ ያለበት.....?እኔም ተነስቼ መድሀኔ እግር ስር ልደፋ እንዴ?›እያለች ስትብሰለስል በድንገት መድሀኔ ከተቀመጠበት ተነሳና መጥቶ እግሯ ስር ድፍት አለ"እባክሽ ልዩ በተፈጠረው ነገር በጣም አፍሬለሁ።እንዴት እንደዛ እንዳደረኩ አላውቅም ።በእውነት በዛ ስካርና የእብደት ቀን ከተፈጠረው ውጭ እምልልሻለሁ በእኔና በእሷ መካከል ምንም የለም...አንቺ መስለሺኝ እሷንም ያሳሳትኳት እኔ ነኝ።በዚህም ሶስታችሁም ይቅር እንድትሉኝ እፈልጋለሁ።

"በቃ ተነስ ይቅር ብዬሀለው ....ከአሁን ጀምሮ ግን ንፅህ ጓደኛሞች ነን"አለችው ፈርጥም ብላ..ፈጥና ይቅር ያለችው ሆነ ብላ የቃልን ትኩረት ለመሳብ ስለፈለገች ነው፡፡ባለፈው ከቃል ጋር ስለዚህ ጉዳይ ሲያወሩ እንዲ እንድታደርግ ስለነገራት ምን ያህል የእሱን ቃል አክባሪ እንደሆነች እንዲያቅላት ስለፈለገች ነው

መድሀኔ ግን ከፊል በሆነው ይቅርታዋ እርካታ አልተሰማውም.በልመናው ገፈበት"እባክሽ ልዩ እኔ እኮ በጣም ነው የማፈቅርሽ በዛ ላይ የሁለታችንም ቤተሠቦች ለሠርጋችን እየተዘጋጅ እኮ ነው።ይቅር ብለሺኝ እንደበፊቱ ካልሆን ምን ልንላቸው ነው።"

"አይ እንደዛማ ፍፅም አይሆንም...እኔ ለቤተሠቦቼ አንተን እንደማላገባ ነግሬቸው ዝጎጅታቸውን አቋርጠዋል...አንተም ጊዜውና ሳይረፍድ ዛሬውኑ ለቤተሠቦችህ ንገራቸው።

"ምን ብዬ.ቀለበቱን እንኳን እንዲቀር ለማድረግ ስንት ነገር ቀባጥሬ ነው…ከእነጭራሹ ሰርጉም ጭምር ቀርቷል ብላቸው ኸረ በስመአብ?"ዘገነነው

"እሱ ያንተ ችግር ነው..."

"ቃል አረ አንድ ነገር በላት...ቆይ አንተ ጊፍቲን በፍቅረኝነት አትቀበላትም።"ሲል አንጀት በሚበላ ድምፅ ጠየቀው

ልዩ የቃልን መልስ ለመስማት አይኖቾን አፍጥጣበት በጉጉት ትጠብቅ ጀመር..የፈራችውን አይነት መልስ መለሰ"ለምን አልቀበላትም የይቅርታ ግማሽ የለውም እኮ"

በቃል ንግግር ወሽመጧ ብጥስ አለ‹‹...ምን አይነት ሀሞት የሌለው ሰው ነው...የወራት ልፋቴን በጠቅላላ ገደል ሊከተው እኮ ነው.. አሁን እሺ ምን ላድርግ?።›በውስጧ አብሰለሰለች.ሀሞትና ከርቤ ቀላቅላ እንደተጋተ ሰው .አፏን መረራት…፡፡መድህኔ ተፍለቀለቀ...ግን የልዩ ብስጭት ሆነ የመድሀኔ ደስታ ለሽርፍራፊ ሰከንድ ብቻ ነው መቆየት የቻለው።ድንገት የመብረቅ ብልጭታ በሚመስል ክስተት ታአምር መሳይ ዜና ከጊፊቲ አንደበት ዱብ አለ"አርግዤለሁ"አለች...መድህኔ በተንበረከከበት ዝርፍጥ ብ ሎ መሬት ያዘ