Get Mystery Box with random crypto!

‹‹ምን አልሺ ጊፍቲ…?››ልዩ ነች ጠያቂዋ ‹‹ሰሞኑን ጥሩ ያልሆኑ ስሜቶች እየተሰሙኝ ስለነበረ ወደ | አትሮኖስ

‹‹ምን አልሺ ጊፍቲ…?››ልዩ ነች ጠያቂዋ
‹‹ሰሞኑን ጥሩ ያልሆኑ ስሜቶች እየተሰሙኝ ስለነበረ ወደእዚህ ከመምጣቴ በፊት ሆስፒታል ሄጄ ተመርምሬ ነበር….እንዳረገዝኩ ነገሩኝ››ብላ ከኪሷ የተሰጣትን የማስረጃ ወረቀት አውጥታ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችው…..ከዛ በኃላ ማንም መናገር የደፈረ አልነበረም…‹‹.ወይኔ ጉዴ መድህኔ ቀድሞኝ በአቆራጭ የልጅ አባት ሊሆን ነው፡፡›ልዩ በውስጧ  በደስታ እየተፍለቀለቀች ያሰበችው የሽሙጥ መሳይ ሀሳብ ነበር ፡፡‹‹ይሄ ለእኔ ያልጠበቅኩት ቦነስ ነው፡፡እነዚህ ሰዎች ከአሁን ወዲህ ከመጋባት ውጭ ምንም ምርጫ የለቸው…፡፡ቃልም ከእኔ ውጭ ሌላ አፅናኝ ከወዴት ያገኛል….?ከየትም፡፡›ስትል በውስጧ በማሰብ በስኬቷ ተመፃደቀች፡፡

ቃልም አውጥቶ አይናገረው እንጂ በሰማው ዜና በውስጡ ተደስቶል ፤‹‹አሁን የጊፍቲን የወደፊት ህይወት በትክክለኛው አይሮፕላን ላይ መሳፈሩን እርግጥ ሆኖል ››አለ..አሁን እነሱን ገፋፍቶ ወደትዳር እንዲገቡ ማድረግ ለእሱ በጣም ቀላል ስራ ነው…ከዛ በገባው ቃል መሰረት እራሱን ሙሉ ለሙሉ ከመሰወሩ በፊት ልዩን ከሌብነት አመሏ ማላቀቅ ብቻ ነው የሚቀረው ለዛ ደግሞ በቂ የሚባል ጊዜ አለው…‹‹ጊፍቲና መደህኔ ላይ በሰራችው የብልጠት ሴራ  ቅጣቷን የምተታገኝ ቢሆንም በእሷ ስህተት ባልሆነ ጉዳይ ከገባችበት የሌብነት  ጣጣ ግን መፈወስ አለባት›› ሲል በማሰብ ቀድሞ ውሳኔውን ዳግም አፀደቀ ፡፡
ጊፍቲና መድሀኔ ግን ዜናውን ተከትሎ ምን እየተሰማቸው እንደሆነ ?እያዘኑ ይሁን ወይስ እየተደሰቱ? እራሳቸውም አያውቁትም…ሁለቱም ደንዝዘው እርስ በርስ በፍዘት  እየተያዩ ነው፡፡

ይቀጥላል