2023-04-09 20:50:38
#ባል_አስይዞ_ቁማር››
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
‹‹ምነው…ፒያሳ ይሻላል እንዴ?››ልዩ ነች የጠየቀችው፡፡
‹‹አይ የሆነች ጉዳይ ሳላለችብኝ ነው… ደረስ እንልና እንደውም እዛው ኢሊሊ ራት በልተን ከዛ ወደምትፈልጉበት ጭፈራ ቤት እንሄዳለን..››
ጊፍቲ ፈገግ አለች….ቀጥታ ፒያሳ ወደሚገኙ መደዳ ወርቅ ቤቶች ነበር ይዟቸው የሄደው..ልዩ እራሱ ያልጠበቀችው ነገር ስለሆነ ግራ ተጋባች…እሱ ራሱ ቀድሞ ያሰበበት ጉዳይ አልነበረም..ሰጥሀለው የምትለዋ ቃል ከአንደበቷ ተስፈንጥራ ስትወጣ በውስጡ በተፈጠረ ፍንጠዛና በምርቃና ድንገት ብልጭ ያለለት ሀሳብ ነው፡፡
‹‹ምነው ምን መጣ..?››ጠየቀችው፡፡
‹‹ቀለበታችን ሳንመርጥ የቀለበቱ ቀን ደረሰ እኮ?››
‹‹እንዴ ገና ሁለት ወር ይቀረናል እኮ››
‹‹ሁለት ወር ምን አላት….አይደል ጊፍቲ፡፡›› አለ ወደ እሷ ዞሮ ድጋፍ እድትሰጠው በሚፈልግ ንግግር…
እሷ የሰማችው አይመስልም ቅዝዝ ብላ ጭልጥ ያለ ሀሳብ ውስጥ ገብታለች
‹‹ጊፍቲ፡፡››
‹‹እ..ታድላችሁ…አዎ ትክክል ነው..ሁለት ወር በጣም አጭር ጊዜ ነው…››አለችና ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡ…ተገቢውን ቀለበት አማርጦ ለመግዛት ከሰላሳ ደቂቃ በላይ ነው የፈጀባቸው….በመጨረሻ እንደውም ጊፍቲ አሪፍ ነው ብላ ያሳየቻቸውን የዳይመንድ ፈርጥ ያለበት ቀለበትን ነው ሁለቱም በአንድ ድምፅ ተስማምተው የተገዛው..የሁለቱንም ቀለበት ሰጣትና ቦርሳዋ ውስጥ በመክተት እየተሳሳቁ ተያይዘው ወጡ…
እንዳአለውም ኢልሌ ሆቴል ጎራ አሉና እራታቸውን በልተው ሲወጡ ሶስት ሰዐት አልፎል…
‹‹አሁን ጭፈራ ቤት ለመሄደ ትክክለኛው ሰዓት ነው››አለ መድሀኔ…ፍንድቅድቅ ባለ ድምፅ፡፡
‹‹አዎ ግን እናንተ ብትሄዱ ይሻላል ..ከዚህ በላይ ካመሸው አከራዬቼ የውጭ በራፍ አይከፍቱልኝም…››አለች ጊፍቲ
‹‹እኛም አይከፍቱልንም››ሲል መለሰላት መድህኔ
‹‹አይ ቢሆንም እናንተ የራሳችሁ ማለቴ የወላጆቻችሁ ቤት ነው..ጨክነው አይጨክኑባችሁም እኔ ግን ኪራይ ቤት..››
ክንዷን ያዘችና ‹‹ነይ ባክሽ እስከአራት እስከ ከአምስት ሰዓት ዘና እንልና አዲሱ ቤታችን ሄደን ነው የምናድረው…አይደል መድህኔ?››
‹‹እ አዎ..ጥሩ ሀሳብ ነው….››አለ…..እሱም ያላሰበው አዲስ ሀሳብ ነው ያመጣችው፡፡
መኪና ውስጥ ገብተው መድሀኒ መንዳት ከጀመረ በኃላ…‹‹እንዴ አዲስ ቤት ተከራያችሁ እንዴ ?›› ስትል ጠየቀች
‹‹ አይ የእኔ ፍቅር አሪፍ ቤት ገዝቶ ሰርፕራይዝ አደረገኝ፣››አለችና መልስ ሰጠቻት፡፡ ለቤት ያላትን ፍቅር እሷም ሆነች ቃል ደጋግመው ነግረዋታል፡፡ለዛም ነው አይን አይኗን እያየች አድምቃ እያወራች ያለችው፡፡
‹‹ለእናንተ እኔ ደስ ብሎኛል አለች››የንግግሯ መዝረክረክ ግን ደስ እንዳላላት ያስታውቅባታል፡፡
‹‹ሰዎች የተለየ ሀሳብ አለኝ››ልዩ ነች ተናጋሪዋ፡፡
‹‹ምንድነው?››
‹‹ለምን የሚስፈልገውን መጠጥ ገዝተን ቀጥታ ወደቤታችን አንሄድም…..ግርግሩ ብቻ ነው የሚቀርብን …ሙዚቃው እንደሆነ እቤት አለ …እንቀውጠዋለን…››
መድህኔ ሁለቱንም እያፈራረቀ አያቸው…
‹‹ወይ በቃ ለካ ጊፍትዬ ጭፈራ ቤት ትወዳለች…››አለች ልዩ..አውቃነው እሷን ይሉኝታ ውስጥ ለመጨመር አስባ ይህቺን አረፍተ ነገር የሰነዘረችው፡፡
‹‹አረ በፍፅም.. አሪፍ እና የተለየ ሀሳብ ነው ያመጣሽው..እንደውም ጭፈራ ቤት አድሬ ነገ ጥዋት ተነስቼ ቢሮ መግባት ይከብደኛል.. እያልኩ እያሰብኩ ነው…››
መድህኔ ‹‹እንግዲያው ወደቤት ነዳሁት…››አለና አቅጣጫውን አስተካከለ…
ከሀያት ሪል እስቴት ወደተገዛው ግዙፍ ቪላ ነው የነዳው..መንገድ ላይ ቆሞ ሴቶቹን መኪና ውስጥ አስቀምጦ መአት አይነት መጠጦችንና የተወሰኑ የሚበሉ ነሮችን ገዝቶ ተመለሰ….እቤት ሲደርሱ አራት ሰዓት ተቃርቦ ነበር..የመኪናውን ጡሩንባ ቢያንጣጣም በቀላሉ ሊከፈት አልቻለም..ወርዶ በእጁ ጭምር መቀጥቀጥ የግድ ሆኖበት ነበር..ከዛ ዘበኛው በድንጋጤና በማለክለክ መጥቶ ከፈተና በተደናገጠ ደምፅ..‹‹ጋሺዬ ይመጣሉ ብዬ ስላላሰብኩ እንቅልፊቱ ጣለችኝ፣እንደው ይቅርታ››ተሽቆጠቆጠ፡፡
‹‹…ችግር የለውም…››ብሎ አረጋጋው…ኮፈኑን ከፈተና
‹‹ይህቺን እቃ ወደሳሎን ውሰድልኝ›› አለው…ዘበኛው በታዛዥነት አንከብክቦ ወደሳሎኑ ከነፈ…ጊፍቲ በግቢው ውበት ፈዛ ከግራ ወደቀኝ አይኗን እያስወነጨፈች ታያለች…የምታደርገውን እየተካታተለ እንዳልሆነ ሰው ችላ ብላ ክንዷን ያዘችና ወደቤት ይዛት ገባች…ከሳሎኑ ጀምራ እያንዳንዱን መኝታ ቤት…መታጠቢያ ቤቶችን… ኪችኑን አስጎበኘቻት….
‹‹እንግዲህ ልጅ እስኪመጣ ድረስ ለእኛ ይበቃናል?››አለቻት
‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል?››
‹‹ምን እቀልዳለው..እኔና እናቴ ከሰራተኞቻችን ጋር የምንኖርበት ቤት እኮ የዚህን ሶስት እጥፍ ይሆናል…ከዛ ወጥቶ እዚህ መኖር..ብቻ ይሁን አሪፍ ነው››
‹‹እና ከሁለት ወር በኃላ ልትጋቡ ነዋ››ጠየቀቻት፡፡
‹‹አይ ከሁለት ወር በኃላ ምርቃቴ ስለሆነ ቀለበቴ ነው በደባልነት የሚደረገው ሰርጋችን ከሶስት ወር ነው….ምን ይታወቃል… አብረን አንሞሸር ይሆናል?››
‹‹አይ!! ብለሽ ነው?››አለቻት… ትክዝና ቅዝዝ ብላ….፡፡አዎ የፈለገችውም እንዲህ ውስጧን መበጣጠስና ተስፋ ማስቆረጥ ….ወይንም ማስጎምዠት ነበረ…‹.እርግጠኛ ነኝ ይሄኔ ስንቴ ምን አለ ይሄ ቤት የግሌ በሆነ ብላ ተመኝታለች..እንግዲህ ይሄን ቤት ከፈለገች..የቃልዬን እጅ ለቃ የመድህኔን እጅ መያዝ አለባት ማለት ነው…ያንን እንደምታደርግ ደግሞ ከዛሬ ጀምሮ ምልክት ልትሰጠኝ ይገባል….ጊዜ የለንም፡፡››ስትል እሷን ከጎኗ አቁማ በውስጧ አብሰለሰለች፡፡
ጉብኝታቸውን ጨርሰው ወደሳሎን ሲመለስ መድህኔ ጠረጳዛውን በመጠጥና በሚበሉ ቀለል ባሉ ምግቦች ሞልቶት ግዙፍ እስፒከር ያለውን ቴፕ አዘጋጅቶ ጠበቃቸው…
‹‹የእኔ ፍቅር ምርጥ እኮ ነህ›› ብላ ተንጠልጥላበት ጉንጩን ሳመችው፡፡ ‹‹መቼስ ዛሬ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ቁልትልት ብዬበታለሁ……››ስትል እራሷን ታዘበች
ጊፍቲ ሶፋ ላይ ቁጭ አለች……
‹‹ምን ልቅዳለችሁ?›› መድሀኔ ጠየቀ፡፡
‹‹ወይን ቢሆን ደስ ይለኛል…››መረጠች ጊፍቲ፡፡…
‹‹አዎ ከቀላል እንጀምር ለእኔም ወይን››ልዩም ከጊፍቲ ምርጫ ጋር ምርጫዋን አስማማች፡፡
እንግዲያው ቆንጆ የፈረንሳይ ወይን አለኝ….አለና ከተኮለኮሉት ጠርሙሶች መካከል አንዱን መዞ በእያንዳንዳቸው ብርጭቆ ቀዳላቸው …እና የራሱንም ይዞ ከፊት ለፊታቸው ቁጭ አለ፡፡
መጠጡ በወይን ቢጀመርም..ወደውስኪ ሲሸጋገር አንድ ሰዓት አልፈጀበትም። ስድስት ሰዓት ላይ ተኪላ ነበር ሻት እየተደረገ የነበረው ...ዳንስ ..ጭፈራው ቅውጥ ያለ ነበር፡፡ ልዩም ዛሬ እንደው የእነሱን ያህል ችሎታው እንደሌላት ብታወቅም ቁብ ሳይሰጠት ከእነሱ እኩል ስትቀውጠው አመሸች...ልዪነቱ መጠጡ ላይ እየጠጣች በማስመሰል ስትደፍው ..አንዳንዴ ወደእነሱ ስትገለብጥ በተቻለኝ መጠን የሰከረች በመምሰል ግን ሳትሰክር እራሷን ለማቆየት የተቻላትን ጣረች..እናም ተሳክቶላት ሰባት ሰዓት ሲሆን ሁለቱም በዳንስ ብዛት ውልቅልቅ ብለው በላብ ወርዝተው ከላይ የለበሱትን እያወለቁ ጥለው እሱ በነጭ ፓክ አውት እሷ ደግሞ በጥቁር ጡት ማስያዣ ነበሩ...ልዩም ያው እነሱን ለማበረታት በጡት መያዠ ብቻ ቀርታለች...በዳንሱ ሞቅታ መካከል ሁለቱንም አቅፍቸውና አንድላይ አጣብቃ ወዳራሷ ትጨምቃቸዋለች…እንደዛ ሲሆን እርስ በርስ አንዲፍተጉ እያደረገች ቅርበታቸውን እያጠናከረች ነው፡፡..አንዳንዴ ሞቅ ብሏቸው የጋለ የእርስ በርስ
1.5K viewsአትሮኖስ, 17:50