2023-04-15 21:07:20
#ባል_አስይዞ_ቁማር
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
ከክስተቱ በኃላ መድህኔ ልዩ ቤት ድረስ አይኑን በጨው አጥቦ ሊያናግራትና ይቅርታ ሊጠይቃት መጥቶ ነበር..የመኝታ ቤቷን በራፍ ግን ልትከፍትለት አልፈቀደችም…ለእናቷም የሰርግ ዝግጅቱን እንዲያቆሙና ከመድህኔ ጋርም ፍፅም እንደማትጋባ ስትነግራቸው. መጀመሪያ በጊዜያዊ ንዴት ተገፋፍታ የተናገረችው ነው ብለው ትኩረት አልሰጡትም ነበር…ውሎ አድሮም ምንም አይነት የመርገብም ሆነ የመረጋጋት ሁኔታ ስላልታየባት እየደነገጡ ሄዱ….ከዛ ምክንያቱን እንድትነግራቸው አምርረው ጨቀጨቋት…‹‹ከጓደኛዬ ጋር ሲማግጡ አንድ አልጋ ላይ ያዝኳቸው›› ብላ እቅጩን ነገረቻቸው…ባለማመን እራሱ መድህኔ ጋር ደውለው ጠየቁት…አላደረኩትም ብሎ ሊክዳቸው አልቻለም...ከዛ እሷቸውም እጥፍ በሆነ ምሬት መድሀኔን ተቀየሙት… እሷን መጨቅጨቁንም ሆነ የሰርጉን ወሬ እርግፍ አድርገው በመተው ልጃቸው ብቻ በብስጭት አንድ ነገር እንዳትሆንባቸው በስስት መከታተላቸውን ቀጠሉ፡፡
ስለጊፍቲ ሁኔታ ደግሞ ቃል አንድ ሁለት ቀን እቤቷ ድረስ በመሄድ እንዳገኛትና ያለችበት ሁኔታ የከፋ የሚባል እንደሆነ ነገሯታል….መድሀኔና ጊፍቲም ተገናኝተው እንደማያውቁ ሲነግራት ስጋት ውስጥ ገብታለች።
‹‹በዚህ የቃል ሀዘኔታ ጊፍቲ እግሩ ላይ ወድቃ ይቅርታ ብትጠይቀው አይኑን ሳያሽ ነው ይቅር የሚላት።››ስትል ስጋት ውስጥ ነች፡፡ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ተጋብታለች፡፡
ጊዜ ተለዋዋጭ ነው…በተለያ ሁኔታ ውስጥ ሊለጠጥና ሊኮማተር ሊረዘምና ሊያጥር ይችላል፡፡ጊዜ በተለያዩ የሰማይ አካላት ላይ ባላቸው ፍጥነት መጠን ልክ የተለያየ መጠን አለው፡አንድ ዓመት ርዝመት በምድር ላይ እና በማርስ ላይ በጠጣም የተለያየ ነው…
በፍጥነት በሚጓዙ .የሰማይ አካላት ላይ ሰዓት ሲኮማተር ዝግ በሚሉ ብለው በሚጓዙት ላይ ደግሞ ጊዜ ይለጠጣል ወይም ይረዝማል፡፡
አልበርት አንስታይን በቴኦሪ ኦፍ ሪላቲቪቲ መሰረት የአንድ ቁስ ጉዞ ከብርሀን ፍጥነት በላይ በሚሆንበት ጊዜ ወደ ትናንና ይጓዛል የሚለውን አረጋግጧል..ይሄ ማለት የታይም ትራቭለር ሀሳብ በዚህ ስሌት የሚሰላ ነው ፡፡
ይሄን ያሰበችው ቃልን ከማግኘቷ በፊት ያሳለፈችው ጊዜ ሲቆጠር ረጅም አሰልቺ አይነት ሲሆን አሱን ካገኘች በኃላ ያሳለፈችው በሚዛኑ የቀኝና የግራ ሰሀን ላይ ቢቀመጥ የትኛው በልጦ ይገኛል? ፡፡
ከቃል ጋር እያወራች ነው..እራሱ ደውሎ ነው ከቤት እንድትወጣ ያደረጋት..ምክንያቱም በጣም ልቧ ተሰብሯል…ምክንያቱም የእሱ ጓደኛና እጮኛ የእሷን እጮኛ አማግጣባታለች...ወይንም እርስ በረሻቸው ተመጋግጠዋል….ስለዚህ አፅናኝ ትፈልጋለቸ፡፡ይሄው አሁን ቃል እያደረገ ያለውም ያንን ነው፡
‹‹ልዩ የምሬን ነው በጣም ነው ያዘንኩት ..ልብሽ እንዲሰበር ስላደረኩ ይቅርታ›› አላት አንጀት በሚበላ አሳዛኝ ንግግር፡፡
"አንተ ምን አደረክ...?እንደውም ከእኔ እኩል ተጠቂ ነህ።"
"አይ የእኔና ያንቺ አንድ አይደለም .›አላት፡፡
.‹‹ምን? የእኔ የራሴ ጥፍት ነው"ምን ለማለት እንደፈለገ ግልፅ አልሆነላትም‹ምን ማለትህ ነው?›ስትል ጠየቀችው፡፡
"ኃላፊነቴን ባለመወጣቴ ምንም ነገር ብታደርግ በእሷ ላይ ጣቴን የመቀሰር ሞራል የለኝም..ብቻ ከአንቺ እጮኛ ጋር ለምን እንዳደረገችው ነው ሊገባኝ ያልቻለው?"
"ከእኔ እጮኛ ጋር ሆነ ከሌላ ጋር ምን ለውጥ አለው ..ክህደት ያው ክህደት ነው?"
"አይ እኔ ከድታኛለች ብዬ አላስብም...ጊፍቲ መቼም እኔን ልትከዳኝ አትችልም...ግን ከእኔ የምትጠብቀውን ለዘመናት ጠብቃ ስላጣች..ያደረገችውን ማድረጓ ያንስባት እንደሆነ እንጂ አይበዛባትም፡፡"
"እና አሁን ወደአንተ መጥታ ይቅርታ የምትጠይቅህ አይመስልህም"
"ይቅርታ..."
የመደነጋገር ስሜት ታየበት..‹‹ጊፈቲና መድህኔ ተበዳይ እእጂ በዳይ እይደሉም..ይቅርታ መጠየቅ ያለብን እኔና አንቺ ነን..››በማለት በውስጡ አያሰበ በአንደበቱ ግን"አይ ይቅርታ የምጠይቃት እኔ ነኝ...... ጥፋተኛው እኔ ስለሆንኩ ላባከንኩት ጊዜዋ፤ላልከሰከስኩት ተስፋዋ፤ለሁሉም ነገር ይቅርታ እጠይቃታለሁ።"አላት፡፡
ልዩ ሰውነቷ ሁሉ በፍርሀት መንዘርዘር ጀምሯል...ያ ሁሉ ልፋቷ ያ ሁሉ ጥረቷ በዚህ ሰው አጉል የዎህነት ገደል ሊገባባት እንደሆነ ታሰባትና ውስጧ በንዴት ተቃጠለ።እንዲህማ አያደርገኝም....፡፡
"እና ይቅርታህን ከተቀበለች በኃላ እንደድሯችን እንሁን ብትልህ እሺ ትላለህ?"
"ምን አልሽ? እንደውም እንደድሯችን መሆን አንችልም ካለቺኝ ነው እሺ ማልላት...እንደዛ መቼም አይሆንም፡፡"
"እንዴ ይሄ ምን የሚሉት ግራ የተጋባ ነገር ነው...ከእኔ ባል ጋር ፍቅር ይዞት ከሆነስ ...?እሱን ለማግባት ፈልጋለሁ ብትልህስ?›› ስትል ጭርጭር በሚያደርግ የንዴት ጠየቀችው፡፡
"እሱን ማለቴ አይደለም... እንዳልሽው እሱን ታፍቅረውም ለማግባት ትሞክርም.. የእሷ የራሷ መብቷ ነው። ያንን ምርጫዋን ሆነ ውሳኔዎን አከብርላታለሁ።ግን እሺ ማልላት ጓደኝነታችንን እናበላሽ ካለቺኝ ነው።…አዎ ሲሆን ሲሆን ይቅር ብላኝ ብታገባኝ ደስ ይለኛል.ከልሆና እንዳልሺው አሱን ወዳውም ከሆነ ችግር የለም ዋናው የእሷ ምቾት ነው››አላት…ቃል ንግግሩን ሆነ ብሎ የልዩን የአሸናፊነትና የስኬት ስነልቦና ለመናድ አልሞ ነው እየሰነዘረ ያለው.. እናም ደግሞ ተሳክቶለታል..ልዩ በተሸናፊነት መንፈስ እየተናጠችና በፍርሀት ስሜት እየተንቀጠቀጠች ነው፡፡
‹‹እና አንተን ጥላ መድሀኔንም አግብታ ቢሆን እንደበፊቱ ጓደኛዋ ሆነህ የመቀጠል ፅናቱ ይኖርሀል።››
"እንደዛ ካላደረኩ እኮ መጀመሪያውኑ አልወዳትም ነበር ማለት ነው"አለትና አስደመማት።
ዝም አለች..."እኔ አሁን የመድህኔ መሳሳት የእኔ ስውር እጅ ስላለበት ይሉኝታ ይዞኝ ትንሽ ቀዝቀዝ አልኩ እንጂ ከእኔ እውቅና ውጭ ወስልቶብኝ ቢሆን ኖሮ ዘልዝዬ አልበላውም ነበር?›ስትል በውስጧ እራሷን ጠየቀች..፡፡
" እኔ ግን መቼም ቢሆን መቼም ይቅር ልለውና መልሼ እንደድሮችን ልቀበለው አልችልም።››ስትል ፍርጥም ብላ አቋሟን ለቃል ነገረችው፡
"እንደእጮኛ ተቀበይው ብዬ ላስገድድሽ አልችልም...ግን ከእዚህ በፊት እንዳጫወትሺኝ ከሆነ መድህኔ ፍቅረኛሽ ከመሆኑ በፊት የልጅነት ጓደኛሽ ነው። በጓደኝነት ህይወታችሁ ብዙ መልካም ቀናትን… ብሩህ የሆኑ ትዝታዎችን አሳልፋችኋል...እና እሱን ከውስጥሽ እስከወዲያኛው ፈንቅለሽ ስትጥይ የራስሽንም መልካም ትዝታዎችንና ወርቃማ ትናንቶችሽን ነው አብረሽ የምትደመስሼያቸው... እሱን በጎዳሽው መጠን አንቺም ተጎጂያለሽ፡፡.››
"እና ምን እያልከኝ ነው?"
ከደረት ኪሱ እስኪረሪብቶና ብጣሽ ወረቀት አወጣና ሰጣት.::ግራ በመጋባት‹‹ምን ላድርገው?››ብላ ጠየቀችው፡፡
‹‹የምነግርሽን ነገሮች ለመፃፍ ተዘጋጂ››አላት፡፡
ምን ሊለኝ ነው በሚል ጉጉት እስኪርብቶውን ወረቀቱ ላይ ቀስራ መጠባበቅ ጀመርረች፡፡
‹‹መድህኔ በህይወት ጉዞዬ ጎደኛዬ በነበርክ ጊዜ…››
ቀና ብላ አየችው..
‹‹ፃፊው…፡፡››
‹‹መድህኔ በህይወት ጉዞዬ ጎደኛዬ በነበርክ ጊዜ››ብላ ፃፈች፡
1.4K viewsአትሮኖስ, 18:07