Get Mystery Box with random crypto!

ሰው እንዴት ይህን ያክል ሰውን ሊወድ ይችላል እንዴትስ ሁሉ ነገሩ ፍቅር ብቻ ይሆናል ፍቅር... ፍ | አትሮኖስ

ሰው እንዴት ይህን ያክል ሰውን ሊወድ ይችላል እንዴትስ ሁሉ ነገሩ ፍቅር ብቻ ይሆናል ፍቅር... ፍቅር... አሁንም ፍቅር.... አንተጋ ያለው ፍቅር ብቻ ነው እኔጋ ደግሞ ላንተ ያለኝን ፍቅር ሊፈታተን የሚችል የበቀል ጥም አለ። ያንተ ፍቅር እና የኔ በቀል ጥም ተጣጥመው ሊሄዱ አይችሉም ስለሆነም ጥሜን ልቆርጠው ፍቅርህን መሸሽ መርጫለሁ። ያጣሁት ልጄን... ማያዬን... እንቁዬን... ሁሉ ነገሬን ነው። ገዳይዋን ሳልገድል እረፍት እይሰማኝም። አዝናለሁ ቢኒ...

አፈቅርሀለሁ ግን ልሄድ ነው። ትቼህ ልሄድ ነው... ጠንካራ ነህ ትወጣዋለህ።

ደህና ሁን
ህያብ"

ደብዳቤውን ፅፌ ከጨረስኩ በኋላ አጥፌ ፊት ለፊት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጥኩትና ሻወር ልወስድ ገባሁ። ቢኒ ቶሎ እንደማይመጣ ስለማውቅ ዘና ብያለሁ... ታጥቤ ፎጣዬን እንዳሸረጥኩ ስወጣ ቢኒን አልጋ ላይ ቁጭ ብሎ አገኘሁት በእጁ የፃፍኩትን ደብዳቤ ይዟል።

"ምንድነው ፍቅር? ድጋሚ ወደኋላ... ለምን እኔንስ ታደክሚኛለሽ አላሳዝንሽም" አለኝ አጠገቤ መጥቶ አይን አይኔን እያየኝ

"ልጄን በህልሜ አየኋት ቢኒ... አድኚኝ እያለች ስትጮህ አየኋት... ልጄ ከመሬት ስር ተቀብራ...(ሳግ አነቀኝ) አፈር ተጭኖባት እሱ ግን እየተነፈሰ ነው። እፈልገዋለሁ እናም በእጄ እገለዋለሁ" እልሄ ልኩን አለፈ... ፎጣዬን ጥዬ ልብሴን ለባበስኩና ሻንጣዬን ይዤ ልወጣ ስል።

"ዮኒን አግኝቼዋለሁ" አለኝ። ባለሁበት ቀጥ ብዬ ቆምኩ

"ምን?"

"ይሄን በቀል የተውሽ መስሎኝ ነበር ግን ከፈለግሽ አብሬሽ እሄዳለሁ ያለበትንም አሳይሻለሁ ስትገይውም ቆሜ አይሻለሁ።"

"የት ነው ያለው ቦታውን ብቻ ንገረኝ ብቻዬን እሄዳለሁ"

"እሱን እንዳታስቢው ወይም ራስሽ ፈልገሽ አግኝው... ደግሞ አታገኝውም" አማራጭ የለኝም ሻንጣዬን ይዤ ወደኋላ ተመለስኩ።

"እሺ ውሰደኝ አሁን ውሰደኝ"

"አይ አይሆንም ነገ ነው የምንሄደው" በእሽታ አንገቴን ነቀነኩለት።

ወደቀኝ ገልመጥ ብዬ ሳይ የሰርግ ቬሎዬ ተሰቅሏል። ለራሴ ወደኋላ የለም አልኩ...

ይቀጥላል