Get Mystery Box with random crypto!

'መነጋገር ያለብን አይመስልሽም' አለኝ። ወደ ስራ ለመሄድ እየተጣደፍኩ እያለ   'አስቤበታለሁ ማው | አትሮኖስ

"መነጋገር ያለብን አይመስልሽም" አለኝ። ወደ ስራ ለመሄድ እየተጣደፍኩ እያለ   "አስቤበታለሁ ማውራት አለብን ግን አሁን አይደለም... ሆስፒታላችን የልምድ ልውውጥ ሌላ ከተማ ሊልከኝ ነው። ከአስራ አምስት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ያኔ እናወራለን" መኪናዬን አስነስቼ ወጣሁ

ሳሎን ቁጭ ብለን ከታሪኬ ሀ ጀመርኩለት
"የአስራ ሶስት አመት ልጅ እያለሁ ነው........." ሁሉንም አንድ በአንድ ዘርዝሬ ነገርኩት ከሱ ግን ያላሰብኩትን ነገር ሰማሁ

"እና ያኔ የደፈርኩት አንቺን ነበር"

"ምን? ምንድነው የምታወራው?"

"ብርቄን ታውቂያታለሽ? ጎረቤታችሁ ናት መሰለኝ"

"አዎ ብርቄን ከነ ነገሯ የማያውቅ አለ እንዴ... ግን አንተ እንዴት?"

"የዩንቨርስቲ ተማሪ እያለሁ እናቴ የማልወዳት አክስቴ ጋ መልዕክት ይዘህ ሂድ ብላ ላከችኝ... እረፍት ስለነበርንም እየተነጫነጭኩ ብርቄ ጋ መጣሁ።
በዛውም ከአክስቴ ጎረቤት ልጅ ዘመናይ ጋር ተዋወቅሁ። በሁለት ቀን ውስጥ ተዋደን ሴክስ አደረግን( አውቃታለሁ አገር ያወቃት ወንድ አሳዳጅ ናት አልገረመኝም ) የዛን እለት ግን እዛ የጭቃ ቤት ውስጥ እያለን ወደኛ የሚመጣ ሰው ድምፅ ሰማን እና እሷ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደች እኔ ግን እዛው ቀረሁ። በወሲብ ስሜት ጦዤ ስወጣ አንቺን ከሩቅ አየሁሽ እና ጠራሁሽ.... ያ ሁሉ ነገር ተፈጠረ" ከነገረኝ ታሪክ ውስጥ አንድ አስደሳች ነገር አገኘሁ... የእንቁን እውነተኛ አባት

"አክስቴ እኔ እንደደፈርኩሽ ስታውቅ... ማንም ሳያየኝ በሌሊት ሀገሩን ለቅቄ እንድሄድ ድጋሚም እንዳልመለስ አስጠንቅቃ ወደ እናቴ ላከችኝ። በሶስት ቀን ቆይታዬ ብዙ ታሪክ ፈጥሬ ተመለስኩ"
' ሳትፈልግ ማን ሊነካት' እያለች ስታወራ የነበረችውን ብርቄን አሰብኳትና ተገረምኩ ወዲያው ደግሞ ደስ የሚለውን ሁኔታ አሰብኩት

"ደስ ሲል" ሳላስበው ቃል ከአፌ ወጣ

"ምኑ ነው ደስ የሚለው የኔ አንቺን መበደል ድሮ እንደጀመረ ማወቅሽ ነው" ግራ ግብት ብሎት ያየኛል

"እንቁ እውነተኛ አባቷን ማግኘቷ"

"ማለት...? ምን እያልሽን ነው? ምናሴ የኔ ልጅ... አይ አይሆንም... ማለት ተደፍረሽ ነው የወለድሻት...? አይ ውሸትሺን ነው።"

መልስ ሳልሰጠው እየሮጥኩ እንቁ መኝታ ቤት ገባሁ ቁጭ ብላ እያነበበች ነው። ስገባ ቀና ብላ አየችኝ

" ምን ተገኘ ማሚ ፊትሽ እኮ በፈገግታ ሊፈነዳ ነው"

"የተገኘውማ አባትሽ ነው"

"የእውነት...(እንባዋ ኮለል ብሎ ወረደ ሰፍ ብላ አፍ አፌን አየችኝ) የት ነው ያለው ማሚ... የኔ አባት የት ነው?( ሳግ አነቃት) ማሚ በተለይ በዚህ ሰዓት አባቴን በጣም እፈልገዋለሁ... እማ ንገሪኛ..."

"ዮኒ እውነተኛ አባትሽ ነው" አንገቷን ወደኔ አስግጋ ሁለመናዋ ጆሮ ሆኖ በአይኗ ሳይቀር ስትማፀነኝ የነበረችው ልጄ ከኣካሏ እኩል ስብር ስትል አየኋት

"እሱ አባቴ አይደለም... ትክክለኛ አባቴን የአብራኩ ክፋይ የሆንኩትን ሰው ነው የምፈልገው" አለችኝ እንዳቀረቀረች

"አዎ የኔ እንቁ አንቺ የዮኒ የአብራኩ ክፋይ ነሽ ታሪኩን እነግርሻለሁ። የአስራ ሶስት አመት ልጅ እያለሁ..." ዝምምም ብላ ሰማችኝ... ምንም አይነት እንቅስቃሴም ሆነ ንግግር አላደረገችም... ዝምምምም.... አውርቼ ስጨርስ

"ደስ አይልም የኔ እንቁ" አልኳት እንባዋ ገደቡን ጥሶ ወረደ 'ምንድነው እንቁ ለምንድነው የምታለቅሺው'

"ደስ ብሎኝ ነው እማ... የደስታ እምባ ነው። ነይ እቀፊኝ" ተቃቀፍንና

"በቃ ይሄን ቀን ፏ አድርገን እናከብረዋለን ነይ ተነሺ" እጇን ይዤ አስነሳኋትና ወደ ሳሎን ሄድን ዮኒ የለም... መኝታ ቤት አየሁት የለም... ቤት ውስጥ የለም... ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ለሳምንታት የለም...

የሆነኛው ቀን ሌሊት ላይ ስልክ ተደውሎልኝ ዮኒ ያለበትን ቦታ ነገሩኝ... ጭፈራ ቤት ነው። ስሄድ ከሁለት ሴቶች ጋ አብሮ እያበደ ነው... ምንም ሳልል ወደቤቴ ተመለስኩ... ለራሴ ግን አንድ ውሳኔ ወስኜ ነበር 'ተመልሶ እዚህ ቤት አይረግጥም'። ብቸኝነት ተሰማኝ... ቅዝቃዜው አንዘፈዘፈኝ.. እናም ብቸኛዋ እንቁዬ ጋ ልሸሸግ ወደሷ መኝታ ቤት ሄድኩ። በሩን ከፍቼ ስገባ ግን የኔ እንቁ መሬት ላይ ተዘርራ አየኋት ጮኩ። እልፍነሽ ስትሮጥ መጣች... ከመሬት አንስተን አልጋ ላይ ካደረግናት በኋላ የልብ ምቷን አየሁት... ቆሟል... አፏን አሸተትኩት ገዳይ መርዝ ጠጥታለች። ሰውነቷን ነካሁት ከበረዶ ቀዝቅዛለች...
የኔ እንቁ የለችም... ትታኝ ሄዳለች...

ይቀጥላል