Get Mystery Box with random crypto!

#ህያብ ፡ ፡ #ክፍል_አስር ፡ ፡ #ድርሰት_በኤርሚ 'ባልሽን አሳርፊው ልንማር እንጂ ልንሸረሙጥ | አትሮኖስ

#ህያብ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በኤርሚ


"ባልሽን አሳርፊው ልንማር እንጂ ልንሸረሙጥ አልመጣንም ቴሌግራም ላይ ሙሉ መረጃውን ታገኛለሽ" ይላል። እየተጠራጠርኩ ቴሌግራም ከፈትኩ ፊት ለፊት የመጣልኝን መልዕክት ስከፍተው
ፎቶ እና አጭር ቪድዮ.....  ዮኒ ከሌላ ሴት ጋር....

እየሰሙ አለማመን ያለም የሚጠበቅም ነው። እያዩ አለማመን ግን ምን ይባላል። በአካል መጥተው ዮኒ ከእከሊት ጋር ማገጠብሽ ቢሉኝ አይደለም እሱን ልጠራጠር ከነገረኝ ሰው ጋር ልጣላ እችላለሁ። አሁን ግን እውነታ ነው ቁጭ ያለልኝ... ከምወደው ባሌ ጋር እርቃን ገላዋን አብራው የምታብድ ሴት እያየሁ ነው። የአንዷ አልበቃ ብሎ ከሌላ ሴት ጋር ደግሞ ከንፈሯ ላይ ተጣብቆ ያለ ፎቶ እያየሁ ነው... ግን አንድ ነገር ብቻ ነው የምለው። "የኔ ዮኒ አያደርገውም" አድርጎታል እኮ ...ግን ይህንን ማመን ያልፈለገ ውስጥ አለኝ... እናም እውነታውን እያየ ግግም ብሎ አላምን አለኝ። አንደኛው ውስጤ ደግሞ ፍቅርን ሳይቀር ወደጎን ብሎ በቀልን ፈለገ። ቢችል አሁን ያለበት ሄዶ ስጋውን ቢዘለዝለው ተመኘ። የማያምነው ውስጤ ገኖ ወጣና
"ዮኒ አያደርገውም" በጩኸት ቤቱን አደበላለኩት። ሰራተኛዬ እልፍነሽ መኝታ ቤቴን ከፈት አደረገችና

"ሰላም ነው ህያብ" አለችኝ

"ሰላም ነው እልፌ ወደ ስራሽ ተመለሽ" በሩን ዘግታ ተመለሰች። ረጅም ደቂቃ ዝምምም ብዬ ስልኬ ላይ አፈጠጥኩ

ሀሳቡ አደከመኝ ያየሁት እውነት አራደኝ በዛ ላይ ሰሞኑን የተለየ ኬዝ ስለነበረ ያለ እንቅልፍ ሆስፒታል ነበርኩ። ስልኬን ዘግቼ ያስቀመጥኩት መሰለኝ... ከዛ ወደ አልጋዬ ተራመድኩ.... አንድ.... ሁለት..... ጭልም አለብኝ።

"እናት ኧረ ንቂ የኔ ፍቅር" ይሄን ጥሪ ከሰማሁት ስንት አመት ሆነኝ.... ሁለት.... ሶስት... ብቻ በዛ መሀል... አሁንስ ለምንድነው እየሰማሁት ያለሁት... ሁሉም ነገር ከረፈደ... ካለፈበት በኋላ ለምን?... አይኔን ሳልገልጥ እንቅስቃሴውን እየተከታተልኩ ነው።

"ንገሪኝ እስኪ እናት ማነው ጥፋተኛ እኔ ወይስ አንቺ? በእርግጥ የኔ ጥፋት ሚዛን ይደፋል... ምክንያቱም ካየሽው ውጭ እንኳን ብዙ ጥፋቶችን ሰርቻለሁ ግን ባንቺ ጥፋት ላይ ተመርኩዤ ነው። ታውቂያለሽ ከቢኒ ጋር ድሮም እጠረጥርሽ ነበር እና ጥርጣሬዬን የሚያረጋግጥልኝ ነገር ሳገኝ እውነት አይደለም ብዬ ማመን አቃተኝ። ልታስረጅኝ ስትሞክሪ ውሸቷን ነው ብዬ አልሰማም አልኩሽ እናም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ ማገጥኩብሽ... ግን እናት ያሁኑ በደሌ በዛ..... (ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ እና ትንሽ ዝም ካለ በኋላ ቀጠለ) ከስንት ጊዜ በኋላ በአንዲት ልጅ ምክንያት ራሴን አዳመጥኩት። አብረሽኝ ካልተኛሽ ውጤትሽን አበላሸዋለሁ ብዬ አስፈራራኋት.... ብዙ ለመነችኝ... ልመናው አልሰራ ሲላት ግን ያንቺን አድራሻ ፈልጋ ሆስፒታል መጣችና አየችሽ። ስለትዳራችን ሳይቀር ብዙ መረጃ ሰበሰበች ከረፈደ ቢሆንም  ንግግሯ ከእንቅልፌ አነቃችኝ... ትልቁን በደሌን የሰራሁ እለት ከእንቅልፌ ነቃሁ

'ሚስትህ ነፍሷን ሳትሰስት ትሰጥሀለች... አንተ ማመን ባልፈለከው ውሸት ውስጥ ተደብቀህ በሀጢያት ተጨማልቀሀል... ለሷ አትገባትም ምክንያቱም ንፁህ ናት... ግን እግዜር ይቅር የማይለው የለም አምላክህንም ሚስትህንም ይቅርታ ጠይቀህ ወደራስህ ተመለስ። ለውጤቴ ስል አብሬህ ላድር አልፈልግም በተለይ ያቺ ሚስኪ ላይ ይሄን ላደርግ አልችልም። ከፈለግህ ኤፍ አድርገው ህሊናዬን አላቆሽሽም'  ብላኝ ስላንቺ እንዴት እንዳወቀች ሁሉንም ነገር አብራራችልን እና ለአመታት ከተኛሁበት እንቅልፍ ዛሬ ቀስቅሳኝ ሄደች። ያሰብኩት ለሀያ ደቂቃ ብቻ ነው። ወደራሴ ተመለስኩ... እውነታውን ማየት ቻልኩ... በንግግሮቼም ሆነ በተግባር ብዙ እንደገፋሁሽ አወቅሁ... በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን እንዴት እንደምትጠነቀቂልኝ... ምን ያክል እንደምትወጂኝ ተረዳሁ። ወደዚህ ለመምጣት እየተጣደፍኩ ስወጣ ቢሮ በር ላይ ከዚህ በፊት በውጤት አስፈራርቻት አብሪያት የተኛሁትን ልጅ አገኘኋት እናም ቪዲዮና ምስል ላንቺ እንደላከችልሽ ነገረችኝ። ምንም ሳልል ወደዚሁ መጣሁ ወድቀሽ አገኘሁሽ።
ህያቤቴ እየሰማሽኝ እንደሆነ አውቃለሁ። ይቅር በይኝ አልልሽም በተለይ በአንድ ጉዳይ ያንቺ ይቅርታ አይገባኝም... ብቻ አይንሽን ግለጪና የፈለግሺውን ቅጪኝ" አይኔን ገለጥኩ ከወገቤ ቀና አልኩና ትራስ ተደግፌ ቁጭ አልኩ። ለረጅም ደቂቃ በዝምታ አፈጠጥኩበት

"ደስ ያለሽን አድርጊኝ የፈለግሺውን ቅጪኝ " አንደበቴ ሊናገር ቢፈልግ እንኳን ውስጤ ዝምምምም ብሏል የሚያስፈራ ዝምታ

"ደግሞ አሁን እሰማሻለሁ ከቢኒ ጋር ያደረጋችሁትን ንገሪኝ እኔ እንደተናዘዝኩ ተናዘዢልኝ.... ይቅር ተባብለን  አብረን ባንቀጥልም ጥያቄዎቼን እንድትመልሽልኝ እፈልጋለሁ... የምናሴ አባት ማነው። ህያብ አንቺም እኮ ድብቅ ነሽ ከኔ የደበቅሺው ብዙ ሚስጥር አለሽ" ዝምምምም

"እንቁን አሟት ነበር ልያት" ከመኝታ ቤታችን ወጥቼ ወደሷ ስሄድ

"እወቂ ለዚህ ሁሉ ነገር ያንቺም እጅ አለበት....ወይኔ አምላኬ ምንድነው ያደረኩት" ሰማሁት ግን ባልሰማ ወደ ልጄ ክፍል ሄድኩ

በሩን ከፈት አድርጌ ሳያት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝታለች ወደ ውስጥ ገባሁና ቀስ አድርጌ ዘጋሁት። የአልጋዋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብዬ የትኛችውን እንቁዬን አየኋት ግንባሯ ላይ ቸፈፍ ያለ ላብ አለ። ፎጣ አንስቼ ስጠርግላት እጄን ለቀም አድርጋ ወረወረችውና

"እባክህ አትንካኝ እባክህ" ከእንቅልፏ ደንግጣ ነቃች

"ምንድነው ልጄ ማንን ነው አትንካኝ የምትይው"

"አይይ እእ....እ

"የምን እእ ነው ምንድነው ንገሪኝ" ለአመታት ስቃዥ የነበረው ትዝ አለኝ... አይ አይሆንም

"በህልሜ የሚያስፈራ ሰው ገደል ውስጥ ሊከተኝ ሲል አየሁ" ኡፍፍፍፍ.... እኔ ደግሞ ስንቱን አሰብኩት

"አሁን እንዴት ነው ቁርጠቱ ተሻለሽ" ዮኒ በሩን ከፍቶ ገባ

"ምን ሆነሽ ነው ምናሴ ብዙ አመመሽ እንዴ ጠዋት እኮ ረፍዶብኝ ሳላይሽ ሄድኩ" የቅድሙን የተፀፀተ ፊት ሳይሆን ፍም እሳት የሚተፋ አይኑን አየሁት... እንቁ ፊቷን አዙራ ተኛች

"ምንድነው አንቺ ባለጌ ለአባትሽ መልስ ስጪው እንጂ" ፊቷን እንዳዞረች

"ደና ነኝ ተሽሎኛል" አለችው። ተነሳሁና ትቻቸው ወጣሁ። ሳሎን ሶፋ ላይ ቁጭ ብዬ ቲቪው ላይ አፈጠጥኩ..... ሀሳቤ ግን ሩቅ ሄዶ ነበር። መች ነው ይሄን ክፍተት የፈጠርኩት... ለራሴ ደግሜ ልነግረው አልፈልግም የምለውን ያን የመደፈር ታሪኬን ከመደበቅ... አዎ ከዛ ነው የጀመርኩት... ከዛ  የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ አልኩት... ከዛ... ከዛ... ከቢኒ ጋር እንኳን ምንም ግንኙነት የለንም... እሱም እንዳስረዳው እድሉን አልሰጠኝም።

ቢዘገይም ነገሮችን አጥርቼ መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ እና ታሪኬን ከአንድ ጀምሬ እነግረዋለሁ ብዬ ወሰንኩ... ግን አሁን አይደለም።

ህያብን ምን ይጨንቃታል ብትሉ ሰውን ተጣልቶ ማኩረፍ እላችኋለሁ። በህይወቴ እንደመኮራረፍ የምጠላው ነገር የለም አኩርፌ ማደርም አልችልም... በቃ ከሰው ጋ ተጋጨሁ አይደል ወይ እዛው ጋ ችግሩን እነግረዋለሁ ወይም ዝም ብዬ አልፈዋለሁ... ብቻ ያስከፋኝም ላስከፋውም ድጋሚ ሳገኘው ያንን ሰው አዋራዋለሁ። ከዮኒጋ በአንድ ጣራ ስር... አንድ አልጋ ላይ እየተኛን በየቀኑ እያየሁት ለማኩረፍ ሞከርኩ ግን አልተሳካልኝም በደሉን ባልረሳውም ሳላስበው አዋራሁት።