Get Mystery Box with random crypto!

አወጣሁልሽ...እና ሮሪ ሁሉ ነገር እንደዛ ነው የሆነው።'አለና የመጨረሻውን የሲጋራ ቁራጭ መጠጠና | አትሮኖስ

አወጣሁልሽ...እና ሮሪ ሁሉ ነገር እንደዛ ነው የሆነው።"አለና የመጨረሻውን የሲጋራ ቁራጭ መጠጠና ጫፍን  ወለሉ ላይ በመጣል በእግሩ በማሸት እሳቱን አጠፋው።
"እና እኔስ ብጠፍ...ልክ እንደፍቅረኛህ የምትጠልቀው የማታ  ፀሀይ ብሆንስ?"ስትል ጠየቀችው።
"በፍፁም እንደዛ አይሆንም።  አንቺ  በሰማይ ላይ ዘወትር የምታንፀባርቂው ፀሀይ ነሽ።ተመልከች ገና 21 አመትሽ ነው።በጣም ስኬታማና ታዋቂ ድምፃዊ ነሽ።በዚህ ዕድሜሽ በርካት ሽልማቶችን የግልሽ አድርገሻል።ግን ይሄ በቂ አይደለም አለማቀፍ ብርሀን እንድትሆኚ ነው የምፈልገው።ከዚህ መቶ ጊዜ እጥፍ እንድታንፀባርቂ.."
"አጎቴ እኔ ግን ውስጤ በጨለማ ድቅድቅ ተውጦ የአለም ብርሀን መሆን ፈልጋለሁ እያልኩ እራሴን ማታለል ነው የሠለቸኝ ...እኔ ማንም የማያውቀኝ ተራ ግን ደግሞ ደስተኛ ሴት መሆን ነበር የምፈልገው።"
"እንደዛ ከሆነ ከእናትሽ ሞት ጋር የተያያዘ ህመምሽን ታክሞ ለመዳን ሞክሪ ፣የተሠበርሽበት ቦታ ፈራርሰሽ አትቅሪ "
"አንተ ከአሮራ ሞት ጋር የተያያዘውን ቁስልህን መርሳት ችለኸል? እኔስ የእናቴ ሞት ገና አራት አመት አልሆነውም አንተ ግን 15 አመት ሙሉ እራስህን ማከም አልቻልክም..ዛሬም ቁስልህ አዲስ ነው።"
ምን ታደርጊዎለሽ... አንዳንድ ቁስሎችን ጊዜ በቀላሉ አይፈውሳቸውም...አንቺ ግን ማድረግ ያለብሽ ቢያንስ ከእኔ ከእብድ አጎትሽ  የከሸፈ ህይወት መማር ነው... አሁን መጠጥ አማረኝ "ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ።
"አጎቴ ደግሞ...እዚሁ ምትፈልገውን መጠጥ ያምጡልህ "
"አይ የዚህ ቤት መጠጥ ውስኪ.. ቢራ ምናምን ነው ..እኔ ምፈልገው ካቲካላ ነው።"አላት።

.

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj