Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል ሠላሳ አንድ ከባባድ የሚባሉ ጉዳዮችን አለፌለው ነገሮችን ሲና | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል ሠላሳ አንድ

ከባባድ የሚባሉ ጉዳዮችን አለፌለው ነገሮችን ሲናገሩት እንደሚቀሉ ሆነው አታገኛቸውም ፡በውስጡ ማለፍ እንደመናገር ላይሆን ይችላል ፡ ነገር ግን ምን አማራጭ አለህ ፡ አልችልም አልቻልኩም ካልክ ፡ አይምሮህ በራሱ ጠላት ነው የሚሆንብህ ።
አልቻልኩም ስትለው አዎ አትችልም የሚለውን አሳብ ወስዶ ይደጋግመዋል ፡ ይበልጥ እንዳትችል ያደርግሃል። ለራስህ መንገር ያለብህ ይሄ ጉዳይ ከባድ ነው ነገርግን ፡ እወጣዋለው !በየቀኑ የመጣብኝን ችግር ለመቅረፍ አእሰራለው እታገላለው ፡ እናም ደሞ ቀስ በቀስ አሸንፈዋለው ማለት መቻል አለብህ።
    እውነት ለመናገር አልችልም አይሆንልኝም ብትልስ ቁጭብለህ አደጋዎችን ከማስተናገድ ውጪ ምን ታመጣለህ ?ምንም ! ከዛ ይልቅ እየተንቀሳቀስክ እየታገልክ በሕይወት ጎዳና ላይ  ወደፊት ብትራመድ አይሻልም።  በነገራችን ላይ ፈጣሪም በኑሮህ በግንኙነቶችህ ላይ ለውጥ እንዲመጣ እየጣርክ ስትፀልይ ነው የሚሰማህ ።
ከነገሮች ማለፍ በዋላ ዛሬ ሁላችንም እንደ ቤተሰብ ተሰብስበናል ።ቤተሰቦቼ ተሟልተዋል ማለት ይቻላል ፡እናትና አባቴ ፣አክስቴ ደግነሽ እና ፡ በችግሬ ወቅት ያገኘዋት የእናት ያህል የማያት ባዩሽ ፣  ትንሿ  ማማ ፣ሁሉም ተሰብስበው ቡና እየተፈላ ምግብ ቀርቦ እየበላን ንፁ የሆነ ጨዋታ እየተጫወትን ቅዳሜን ቀን በጥሩ መንፈስ ጀምረነዋል ፡ እንዲ አይነት የተረጋጋ ቤተሰባዊ ግንኙነት መፍጠር ቀላል አይደለም ፡ ሰላም እና ጤና ያለው ደስተኛ ቤተሰብ  ያለው ሰው እሱን መቼም እንዳይበረዝ መንከባከብ አለበት ፡ ምክንያቱም  የአገር ሰላም እራሱ የሚጀምረው ከቤት ነው ፡ ቤት የተሰራነገር ነው አንዳንዴ  ወደውጭ ወጥቶ ፡ ማህበረሰቡን ብሎም አገርን የሚረብሸው ።
እናም ለቤተሰብህ የምትሰጠውን ትኩረት ከልብህ አድርገው  እልሃለው
አቤልን በሰው ሀገር ሕይወት የራሷን ምክር ትስጠው ብለን ትተነዋል  ።እናም የማማን እናት ጭምር እናቴ እያፈላለገቻት ነው ።እናቴ እሷም ወዳ አይደለም ልጇን እኛላይ እንድትጥል የሆነችው ።አቤል ነው አላፊነቱን መውሰድ ያለበት የሚል አሳብ አምጥታለች ።እኔም ብሆን ነገሩን በተረጋጋ መንፈስ ሳስበው ልክ ናት ፡ ለዚሁሉ ጥፋት መነሻ አቤል ነው ። እሱው ነው መቀጣት ያለበት ያቺ ሴት ከልጇ ጋር የሚገባትን ቦታ እንሰጣታለን ብዬ እኔም በእናቴ ውሳኔ ተስማማው.....


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj